የአልጄሪያ መንግሥት በተለይ ከሰሃራ በታች ከሆኑ የአፍሪካ ሀገሮች በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ማባረሩን እንዲያቆም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ጥሪ አስተላልፏል።
ናይጀሪያ ውስጥ ላለፉት ሦስት ወራት ተዘግቶ የቆየ አሸባሪዎች ጥቃት ያደረሱበትና 109 ተማሪዎች የተጠለፉበት ትምህርት ቤት ተከፈተ።
የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን ባለፉት ሁለት ቀናት የመታው እጅግ የከበደ ዝናብ ያስከተለው የሃሩር አውራጃ ማዕበልና ውሽንፍር ለሰላሣ ሰው ሞት ምክንያት ሆኗል። ቅዳሜና ዕሁድ የጣለው “ሳይክሎን ሳጋር” የሚል ስያሜ የተሰጠው የውቅያኖስ ማዕበል ኃይል በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢዎች ላይ እስከአሁን ከተመዘገቡት ሁሉ እጅግ የበረታው እንደሆነ ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።
የዓለም የጤና ድርጅት በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በሕዝብ ላይ በብሄራዊ ደረጃ ሊያደርስ የሚችለውን አደጋ አስመልክቶ የደረሰበትን ግምገማ “ከከፍተኛ ወደ በጣም ከፍተኛ” አሳድጎታል።
የኬንያዉ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በኮምፒዩተርና በኢተርኔት አማካኝነት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር የሳይበር ደህንነት ዐዋጅ አፀደቁ። ዐዋጁ ተጨባጭ ያልሆነ መረጃ’ን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶችን 5 ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ ወይም ሁለት ዓመት እሥራት እንደሚቀጡ ይደነግጋል።
”ታይቶ የማይታወቅ ነገር ነው የሆነው። ታሰረች ከአርባ ደቂቃ በኋላ ተገደለች።”
በሶማሊያ ፑንትላንድ አስተዳደሮች ባጨቃጫቂው የሰሜን ሡል ግዛት እንደገና የጀመሩትን ውጊያ እንዲያቆሙ የሶማሊያ መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አስተላልፏል።
ዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ ውስጥ የኢቦላ ወረርሽኝ ዳግም ተከስቶ ለ19 ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን፣ የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ አደረገ።
“ .. አንዴ ብቻ የምናገኛትን ሕይወትን መውደድ ያስፈልጋል። .. ይህን መጽሃፍ መጻፍ የሕይወትን ዋጋ ያጠናሁበት ነው። .. እያንዳንዷ ሰከንድ ብዙ ዋጋ ያላት ነገር ናት። ..”ዶ/ር ዋልተንጉስ ዳርጌ
በኬንያ የባሕር ሸለቆ የሚገኝ ግድብ ባለፈው ረቡዕ ምሽት ተደርምሶ ከአርባ ሰዎች በላይ ሲሞቱ ሌሎች በርካታ መቁሰላቸው ተገለፀ።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
በኬንያ ኃይለኛ ዝናብ ባስከተለው የግድብ መደርመስ ቢያንስ ከ47 በላይ ሰዎች ሕይወት ሲጠፋ፣ የንግድ መደብሮችን ጠራርጎ ወስዷል። ከናይሮቢ ሰሜን ምዕራብ 150 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ሶላይ ከተማ በደረሰው አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡
የኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ የጤና ጥበቃ ባለሥልጣኖች በያዝነው ሳምንት ይፋ ስለተደረገው የኢቦላ በሽታ መግባትን ለመግታት እየተሯሯጡ ናቸው።
የሶማልያ ባለሥልጣኖች እንደሚሉት አንድ አጥፍቶ ጠፊ በታችኛው ሸበሌ ክልል በሚገኝ ገበያ ላይ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ አሥራ አራት ሰዎች ተገድለው 15 ቆስለዋል። ክልሉ ከሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ 90 ኪሎሜትር ርቆ ይገኛል።
ፍልሰተኞች የሜዲትራኒያንን ባሕር እንዳያቋርጡ ለማስቆም ጣሊያን ከሊቢያ ጋር በምታደርገው ትብብር በሕግ ልትጠይቅ ነው፡፡
ባለፈው ቅዳሜ በሰሜን ምሥርቅ ናይጀርያ በታጠቁ ሽፍቶችና በመንደር ነዋሪዎች መካከል በተካሄደ ግጭት 45 ሰዎች ተገድለዋል።
የረዥም ጊዜ የሞዛምቢክ ሽምቅ ተዋጊና የተቃዋሚ መሪ ድንገኛ ሞት፤ በሀገሪቱ ከፍተኛ ድንጋጤና ሥጋት መፍጠሩን ተንታኞች አመለከቱ።
የአምስት ዓመታት የዘለቀው የደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ብዙ ዜጎቿዋ ወላጅ የሌላችው ልጆች ጭመር ወደ ጎረቤት ኡጋንዳ እንዲሰደዱ አስገድዷል፡፡
በዓለምቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የምትሰራ ነርስ በሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ ውስጥ መጠለፍዋን ድርጅቱ አረጋገጠ።
የቻድ ምክር ቤት በያዝነው ሳምንት የፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢን የሥልጣን ጊዜ ሊያራዝም የሚችል አዲስ ህገ መንግሥት ለማውጣት ተስማምቷል። ፕሬዚዳንቱ እአአ ከ1990 አንስቶ ለ28 ዓመታት ሀገሪቱን ሲመሩ ቆይተዋል። እአአ ከ2005 ጀመሮ ደግሞ በፕሬዚዳንትነት አገልግለዋል።
የሊቢያ ባለሥልጣናት በሰጡት መግለጫ፣ ዋና ከተማዋ ትሪፖሊ ውስጥ በሚገኘው በሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ላይ በተካሄደ ጥቃት፣ አሥራ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን አስታወቁ።
የናይጀርያ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ የቦኮ ሃራም አማፅያን የሚደቅኑት አደጋ እየቀነሰ ሄዶ ሰዎች ወደ ቀያቸውና ወደ እርሸቸው እየተመለሱ በመሆናቸው በሀገሪቱ ሰሜን ምሥራቅ ኑሮ እየተሻሻለ ሄዷል ብለዋል።
በሞያሌ አሁንም የፀጥታ ሁኔታ ባለመሻሻሉ እየተቸገሩ መሆናቸዉን ነዋሪዎች ተናገሩ። ሰሞኑን በከተማዋ በነዋሪዎች ላይ የእጅ ቦምብ ሊወረዉሩ የነበሩ ሰዎች ላይ ቦምቡ ፈንድቶ በራሳቸዉ ላይ ጉዳት እንዳደረሱ በአካባቢዉ የነበሩ የዐይን ምሥክሮች ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል።
ደቡብ ሱዳን ውስጥ ባለፈው ሣምንት ውስጥ በአንድ ታጣቂ ቡድን ተጠልፈው የነበሩ አሥር የእርዳታ ሠራተኞች መለቀቃቸውን ዓለምአቀፍ የቀይመስቀል ኮሚቴ አስታወቀ።
ተጨማሪ ይጫኑ