የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ /ፎርማጆ/ በሁለቱ ሃገሮቻቸው መካከል ያሉትን ወንድማዊ ግንኙነቶች ለማጠናከር ዛሬ ተስማምተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የግብጽን የአባይ ውሀ ድርሻን ከፍ ለማድረግ እንደሚጥሩ ለግብፃውያን ተናገሩ፤ አቶ አሕመድ ሞሐመድ የሜታልና ኢንጂኔሪንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል እንዲሆኑ ተሾሙ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የለውጥ ሃሳቦች ፍጥነት የመተግበር ችግር ሊገጥመው እንደሚችል ተገለፀ የሚሉትን ርእሶች ነው ይዘናል፡፡
በኬንያ የሚገኙ ስደተኞች የኬንያ መንግሥት በሀገሪቱ የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ላይ በይበልጥ እንዲያሳትፋቸው ጠየቁ።
በዩናይትድ ስቴይትስ ብዙ ሰዎችን ከሚያስተናግዱ የአውሮፕላን ማረፊያዎች አንዱ በሆነው ኦ-ሄይር አየር ማረፊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያደርገው በረራ በዩናይትድ ስቴይትስና ኢትዮጵያ መካከል የንግድና የምጣኔ ሀብት ትስስርን የሚያጠናክር እንደሚሆን ተገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ከ18 ዓመታት በፊት ከኤርትራ ጋር የተደረገውን የአልጀርስ ሥምምነትንና የድንበር ኮሚሽኑ ከ16 ዓመታት በፊት የሰጠውን ውሳኔ ተቀብሎ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመተግበር መወሰኑን ካስታወቀ ወዲህ የተለያዩ አመለካከቶች እየተሰሙ ናቸው።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ስድሥት ሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ላይ ሊቢያ ጠረፍ ፍልሰተኞች ላይ የብዝበዛ አድራጎት በመፈፀም ወንጅሎ ዓለምቀፍ ማዕቀብ ወስኖባቸዋል።
የግብፅ መንግሥት በመብቶች ተሟጋቾች፣ በኢንተርኔት ላይ ፀሐፍት ወይም ብሎገሮችና በጋዜጠኞች ላይ እየወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ቢሮ በብርቱ አውግዟል።
በደቡብ ሱዳን የተመደቡት አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር አሜሪካ በደቡብ ሱዳን የመንግሥት ለውጥ እንዲኖር ትፈልጋለች የሚለውን የኪር አስተዳዳር በተደጋጋሚ የሚያቀርውን ክስ አስተባብለዋል።
የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ፔር እንኩሩንዚዛ ከሁለት ዓመታት በኋላ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አልወዳደርም በማለት አስታውቀዋል።
ትላንት ማምሻውን ከቱኒሲያ የባህር ወደብ አምስት ማይል ርቀት እንደተጓዘ ነው 180 ፍልሰተኞችን የጫነው ጀልባ የሰመጠው። እስከአሁን በጀልባዋ ተሳፍረው ከነበሩት ውስጥ 68ቱ ከሞት ተርፈዋል። 60 ፍልሰተኞች አስክሬን ተገኝቷል። የተቀሩት 52 ስደተኞችን ማፈላለጉ ቀጥሏል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ የዓለም ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ምሥረታ ሰባኛ ዓመትን ለማክበር ወደ ማሊ ሄደዋል። ምዕራብ አፍሪካዊቱ ማሊ ሚኑስማ በሚል ምኅፃር የሚጠራው የመንግሥታቱ ድርጅት ኃይል የሚገኝባት ሃገር ስትሆን ተልዕኮውን ለማጠናከር እንደሚሠሩ ዋና ፀሐፊው ቃል ገብተዋል።
ሊቢያ ውስጥ በሕገወጥ የሰው አሸጋጋሪዎች ታግተው የነበሩ በደርዘኖች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ሊያመልጡ ሲሞክሩ መገደላቸውንና ሌሎች በርካቶች መጎዳታቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን አስታወቀ።
የኬንያ ሲቪል ማኅበራትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ዛሬ በናይሮቢ በኬንያ ሙስና ተንሰራፍተዋል ሲሉ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ።
ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የሻከረውን ግንኙነቴን እንደገና እየገመገመገምኩ ነኝ ስትል ፓኪስታን አስታወቀች።
በ79 ዓመቷ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ኤርትራዊቷ ታጋይና አንጋፋ ድምፃዊት ፀሐይቱ በራኺ ለአመታት ትኖርበት በነበረው ኒዘላንድስ የሙዚቃ አድናቂዎቿ በተገኙበት የፀሎትና የስንብት ስነስርዓት ትላንት ተካሄደ። ስርዓተ ቀብሯም በነገው እለት በኤርትራ ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል።
ናይጄሪያውያን በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ በአደባባዮችና በየመሥሪያ ቤቶቹ ሜዳዎች ተሰባስበው፣ የመጀመሪያውን ብሔራዊ የኃዘን ቀን እያሰቡ መሆናቸው ተነገረ።
ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ውስጥ ዳግመኛ በተቀሰቀሰ የኢቦኢላ ወረርሽኝ፣ ሰሞኑን ደግሞ ሌላ አንድ ሰው መሞቱ ተገለፀ።
“መጀመሪያ ፍቕሪ” በሚለው ዘፈኗ የምትታወቀው ኤርትራዊቷ ሙዚቀኛና ድምጿዊት ጽሃይቱ በራኺ አረፈች፡፡
በተለያዩ የምሥራቅ አፍሪካ አካባቢዎች ሰሞኑን እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ብዙ ሕይወት ማጥፋቱና በመቶዎች ሺሆች የሚቆጠር ሰው ማፈናቀሉ እየተነገረ ነው። በከበደው ዶፍ በብዛት እየተጎዱ ያሉት ኬንያ፣ ሶማሊያና ርዋንዳ መሆናቸው ታውቋል።
ከሞያሌ ተሰደው ኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በምግብ እጥረት እየተቸገሩ መሆናቸውን ተናገሩ።
የቻድ ምክር ቤት ሃገሪቱን እአአ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ የመሩት ፕሬዘዳንት ኢድሪስ ዴቢ ለተጨማሪ ሁለት የሥራ ዘመን እንዲቆዩ የሚያስችላቸውን አዲስ ሕገ መንግሥት ለማስተዋወቅ ድምፅ መስጠቱ ይታወሳል።
የአልጄሪያ መንግሥት በተለይ ከሰሃራ በታች ከሆኑ የአፍሪካ ሀገሮች በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ማባረሩን እንዲያቆም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ጥሪ አስተላልፏል።
ናይጀሪያ ውስጥ ላለፉት ሦስት ወራት ተዘግቶ የቆየ አሸባሪዎች ጥቃት ያደረሱበትና 109 ተማሪዎች የተጠለፉበት ትምህርት ቤት ተከፈተ።
ተጨማሪ ይጫኑ