የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ የዓለም ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ምሥረታ ሰባኛ ዓመትን ለማክበር ወደ ማሊ ሄደዋል። ምዕራብ አፍሪካዊቱ ማሊ ሚኑስማ በሚል ምኅፃር የሚጠራው የመንግሥታቱ ድርጅት ኃይል የሚገኝባት ሃገር ስትሆን ተልዕኮውን ለማጠናከር እንደሚሠሩ ዋና ፀሐፊው ቃል ገብተዋል።
ሊቢያ ውስጥ በሕገወጥ የሰው አሸጋጋሪዎች ታግተው የነበሩ በደርዘኖች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ሊያመልጡ ሲሞክሩ መገደላቸውንና ሌሎች በርካቶች መጎዳታቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን አስታወቀ።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
የኬንያ ሲቪል ማኅበራትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ዛሬ በናይሮቢ በኬንያ ሙስና ተንሰራፍተዋል ሲሉ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ።
ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የሻከረውን ግንኙነቴን እንደገና እየገመገመገምኩ ነኝ ስትል ፓኪስታን አስታወቀች።
በ79 ዓመቷ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ኤርትራዊቷ ታጋይና አንጋፋ ድምፃዊት ፀሐይቱ በራኺ ለአመታት ትኖርበት በነበረው ኒዘላንድስ የሙዚቃ አድናቂዎቿ በተገኙበት የፀሎትና የስንብት ስነስርዓት ትላንት ተካሄደ። ስርዓተ ቀብሯም በነገው እለት በኤርትራ ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል።
ናይጄሪያውያን በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ በአደባባዮችና በየመሥሪያ ቤቶቹ ሜዳዎች ተሰባስበው፣ የመጀመሪያውን ብሔራዊ የኃዘን ቀን እያሰቡ መሆናቸው ተነገረ።
ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ውስጥ ዳግመኛ በተቀሰቀሰ የኢቦኢላ ወረርሽኝ፣ ሰሞኑን ደግሞ ሌላ አንድ ሰው መሞቱ ተገለፀ።
“መጀመሪያ ፍቕሪ” በሚለው ዘፈኗ የምትታወቀው ኤርትራዊቷ ሙዚቀኛና ድምጿዊት ጽሃይቱ በራኺ አረፈች፡፡
በተለያዩ የምሥራቅ አፍሪካ አካባቢዎች ሰሞኑን እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ብዙ ሕይወት ማጥፋቱና በመቶዎች ሺሆች የሚቆጠር ሰው ማፈናቀሉ እየተነገረ ነው። በከበደው ዶፍ በብዛት እየተጎዱ ያሉት ኬንያ፣ ሶማሊያና ርዋንዳ መሆናቸው ታውቋል።
ከሞያሌ ተሰደው ኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በምግብ እጥረት እየተቸገሩ መሆናቸውን ተናገሩ።
የቻድ ምክር ቤት ሃገሪቱን እአአ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ የመሩት ፕሬዘዳንት ኢድሪስ ዴቢ ለተጨማሪ ሁለት የሥራ ዘመን እንዲቆዩ የሚያስችላቸውን አዲስ ሕገ መንግሥት ለማስተዋወቅ ድምፅ መስጠቱ ይታወሳል።
የአልጄሪያ መንግሥት በተለይ ከሰሃራ በታች ከሆኑ የአፍሪካ ሀገሮች በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ማባረሩን እንዲያቆም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ጥሪ አስተላልፏል።
ናይጀሪያ ውስጥ ላለፉት ሦስት ወራት ተዘግቶ የቆየ አሸባሪዎች ጥቃት ያደረሱበትና 109 ተማሪዎች የተጠለፉበት ትምህርት ቤት ተከፈተ።
የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን ባለፉት ሁለት ቀናት የመታው እጅግ የከበደ ዝናብ ያስከተለው የሃሩር አውራጃ ማዕበልና ውሽንፍር ለሰላሣ ሰው ሞት ምክንያት ሆኗል። ቅዳሜና ዕሁድ የጣለው “ሳይክሎን ሳጋር” የሚል ስያሜ የተሰጠው የውቅያኖስ ማዕበል ኃይል በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢዎች ላይ እስከአሁን ከተመዘገቡት ሁሉ እጅግ የበረታው እንደሆነ ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።
የዓለም የጤና ድርጅት በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በሕዝብ ላይ በብሄራዊ ደረጃ ሊያደርስ የሚችለውን አደጋ አስመልክቶ የደረሰበትን ግምገማ “ከከፍተኛ ወደ በጣም ከፍተኛ” አሳድጎታል።
የኬንያዉ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በኮምፒዩተርና በኢተርኔት አማካኝነት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር የሳይበር ደህንነት ዐዋጅ አፀደቁ። ዐዋጁ ተጨባጭ ያልሆነ መረጃ’ን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶችን 5 ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ ወይም ሁለት ዓመት እሥራት እንደሚቀጡ ይደነግጋል።
”ታይቶ የማይታወቅ ነገር ነው የሆነው። ታሰረች ከአርባ ደቂቃ በኋላ ተገደለች።”
በሶማሊያ ፑንትላንድ አስተዳደሮች ባጨቃጫቂው የሰሜን ሡል ግዛት እንደገና የጀመሩትን ውጊያ እንዲያቆሙ የሶማሊያ መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አስተላልፏል።
ዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ ውስጥ የኢቦላ ወረርሽኝ ዳግም ተከስቶ ለ19 ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን፣ የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ አደረገ።
“ .. አንዴ ብቻ የምናገኛትን ሕይወትን መውደድ ያስፈልጋል። .. ይህን መጽሃፍ መጻፍ የሕይወትን ዋጋ ያጠናሁበት ነው። .. እያንዳንዷ ሰከንድ ብዙ ዋጋ ያላት ነገር ናት። ..”ዶ/ር ዋልተንጉስ ዳርጌ
በኬንያ የባሕር ሸለቆ የሚገኝ ግድብ ባለፈው ረቡዕ ምሽት ተደርምሶ ከአርባ ሰዎች በላይ ሲሞቱ ሌሎች በርካታ መቁሰላቸው ተገለፀ።
በኬንያ ኃይለኛ ዝናብ ባስከተለው የግድብ መደርመስ ቢያንስ ከ47 በላይ ሰዎች ሕይወት ሲጠፋ፣ የንግድ መደብሮችን ጠራርጎ ወስዷል። ከናይሮቢ ሰሜን ምዕራብ 150 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ሶላይ ከተማ በደረሰው አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡
የኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ የጤና ጥበቃ ባለሥልጣኖች በያዝነው ሳምንት ይፋ ስለተደረገው የኢቦላ በሽታ መግባትን ለመግታት እየተሯሯጡ ናቸው።
ተጨማሪ ይጫኑ