በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የፈንጂ ጥቃት፣ የሰው ሕይወት አለፈ፡፡
ታንዛንያ ውስጥ ባልታወቀ ሥፍራ ታስረው የነበሩ ሁለት የሲፔጂ አባላት ዛሬ መለቀቃቸው ተገለፀ።
ትውልደ-ሶማሌዪቱ ኢላን ኦማር እና ከኮሎራዶ አንድ ጥቁር አሜሪካዊ ለኮንግረስ ሲመረጥ የመጀመሪያ የሆኑት የኤርትራ-አሜሪካዊያን ልጅ ጆዜፍ ንጉሤ የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎች ሆነው ተመርጠዋል።
ካሜሩን ውስጥ የሚገኝ የአንድ ፕሪስቢቴሪያን ባለሥልጣን እንዳስታወቁት፣ ዳይሬክተሩን ጨምሮ ከትምህርት ቤት ተጠልፈው የነበሩ 79 ተማሪዎች ተለቀቁ።
የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስጠባቂ ወታደሮች፣ አራት ሶማሊያውያን ሲቪሎችን በመግደል ተወነጀሉ፡፡ ባለሥልጣናት ሁኔታውን እየመረመሩ መሆናቸውም ተገለፀ።
ሰሜናዊ ምዕራብ ካሜሩን ውስጥ ከሚገኝ አንድ የፕሪስቢቴሪያን ትምህርት ቤት፣ ማንነታቸው የማይታወቅ ታጣቂዎች ዳይሬክተሩን ጨምሮ 78 ተማሪዎችን መጥለፋቸው ተገለፀ።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
ማንነትን ሳይገልጹ የዛቻ መልዕክት ማስተላላፍ፣ በፖሊሶች መዋከብ፣ የጠበኛ ባለሥልጣኖች ተግባር፣ ራስን ሳንሱር ማድረግ፣ ከማኅበረሰብ ማግለል፣ መሰደድና ዝቅተኛ ክፍያ የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነትን የሚገጥሙ ችግሮች ናቸው።
የደቡብ ሱዳን አማፅያን መሪ ሪያክ ማቻር በሁለት ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ በጦርነት ወደ ደቀቀቸው መዲና ተመልሰዋል።
በቅርቡ የተፈመውን የደቡብ ሱዳን የሰላም ሥምምነት ለማክበርና ለማጠናከር በመጪው ረቡዕ ጁባ ላይ ታላቅና ደማቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚካሄድ ታወቀ።
የኬንያ ሰሜን ምሥራቃዊ ክፍለ ግዛት ወረዳዎች አመራሮች በዚህ ሳምንት ስብሰባ አድርገው ላለፉት በርካታ ዓመታት አካባቢውን ሲያሸብር የኖረውን የሶማሊያ ነውጠኛ ቡድን አልሸባብ ጋር ለመዋጋት ቃል ተገባብተዋል።
በምሥራቃዊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ያለው ሁከት የኢቦላ በሽታ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የተያዘውን ጥረት እያደናቀፈ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
ሰሜናዊው የሶማሊያ ክፍለ ግዛት ሱል ውስጥ የተቀናቃኝ ነገዶች ታጣቂዎች ተጋጭተው ቢያንስ ሥልሳ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎችና ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ።
የአሜሪካ ድምፅ ለባለሞያዎቹ ሥልጠና ሲሰጥ ያገር ውስጥ ጋዜጠኞችንም ቢያካትት ፍላጎታቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታውቀዋል።
የካሜሮን ፕሬዚዳንት ፖል ቢያ በቅርቡ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸው ፀንቶላቸው ለሰባተኛ አከታታይ የሥልጣን ዘመን ሊቀጥሉ ነው።
ስለ አፍሪካ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
ኤርትራ ከቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን አጋጣሚዎችና ክስተቶች ልትማር ይገባታል የሚል መልዕክት ያለው ፅሁፍ የፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂን አትኩሮት እንዲያገኝ በቅርቡ ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ አውጥተዋል።
ናይጀርያ ውስጥ በያዝነው ዓመት ቀደም ሲል በፅንፈኛ ሙስሊም ቡድን ተጠልፋ የነበረችው ሁለተኛ የረድኤት ሰራተኛ መገደሏን የናይጀርያ መንግሥት ገልጿል።
የታንዛንያ ፖሊሶች በአፍሪካ ከሁሉም ወጣቱ ቢሊዮነር ቱጃር የሚባሉት ሰው መጠለፋቸውን ተከትሎ የዋና ከተማዋን የዳሬሰላምን እና ዙሪያዋን ድንበሮች ዘግተዋል።
ዋሺንግተንና ቤይጂንግ በአፍሪካ ከፍተኛው የምጣኔ ሃብት ተዋናይ ለመሆን ከባድ ጥረት ይዘዋል።
የሶማሊያው ፅንፈኛ ቡድን አልሸባብ አንድ የእንግሊዝ ዜጋን ጨምሮ አምስት ወንዶችን ረሸነ። ለዩናይትድ ስቴትስ ለእንግሊዝና ለሶማሊያ የደኅንነት ድርጅቶች ሥለላ ስታካሂዱ ነበር ብሎ ወንጅሏቸው መሆኑ ታውቋል።
በገንዘብ ዝውውር ላይ አዲስ የተጣለውን ህግ በመቃወም የሚወጣውን ሰልፈኛ እንደሚበትኑ፣ የዚምባብዌ ፖሊሶች አስታወቁ።
የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳማዊት እመቤት ሚሌንያ ትራምፕ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በመቀጠል ዛሬ ኬንያ ገብተዋል።
ቡሩንዲ ውስጥ ሰብአዊ መብት እየተረገጠ ነው የሚል ሥጋት በሚሰማበት በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ መንግሥት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለማገድ መወሰኑን የረድዔት ድርጅቶች እያወገዙ ነው።
የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ካለ ገደብ በሥልጣን እንዲቆዩ ባለፈው ዓመት በሀገሪቱ ህገ መንግሥት ለውጥ ከተደረገ ወዲህ ተቃውሞዎች ሀገሪቱን ሲያናጉ ቆይተዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ