በቅርቡ ሥልጣናቸውን የለቀቁት የዚምባብዌ ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤ ከሁዳዶቻቸው/ከመሬታቸው/ ካባረሩዋቸው ነጮቹ ገበሬዎች መካከል የመጀመሪያ ትናንት ሃሙስ ወደመሬታቸው ተመልሰዋል።
የደቡብ ሱዳን መንግሥትና የሽምቅ ተዋጊዎቹ ቡድን በ2015 ዓ.ም በከፍተኛ ደረጃ በተካሄደ ስብሰባ የተደረሰውን የሰላም ሥምምነት ለማንቀሳቀስ የሚያስችል፣ አዲስ የተኩስ አቁም ውል ተፈራረሙ።
የዩጋንዳ እንደራሴዎችና የፓርላማው ፖሊስ ትናንት ግብ ግብ ገጥመዋል። ምክንያቱ እንደራሴዎቹ የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት የዕድሜ ጣሪያ ገደብ ጉዳይ አንስተው እየተወያዩ ሣሉ ወታደሮች በፓርላማው ግቢ ውስጥ ታዩ መባሉ ነበር። “በዚያው የቃላቱ መሠናዘር ተቋርጦ የአካል ትንቅንቁ ተጀመረ” ብላለች የካምፓላ ሪፖርተራችን ሃሊማ አቱማኒ።
የደቡብ አፍሪካ ገዢው ኤኤንሲ ፓርቲ መልዕክተኞች ቀጣዩን የፓርቲው መሪ ለመምረጥ ማልደው ድምፅ መስጠት ጀምረዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ለሶማልያ ጦር የምሰጠውን ድጋፍ በአብዛኛው ልታቆም መሆኑን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለቪኦኤ አረጋገጡ። የሙስና መስፋፋትና የተጠያቂነት መጥፋት ናቸው ዋና ዋና ምክንያቶቹ ብለዋል ባለሥልጣናቱ።
የአውሮፓ ሕብረት ሀገሮች፣ ከሊብያ የሚነሱ ስደተኞችና ፍልሰተኞች የሜዲትራንያን ባሕር እንዳያቋርጡ በማድረግ፣ ለወከባና ለሰቆቃ እንዲዳረጉ ምክንያት ሆነዋል ሲል፣ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።
ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ ትናንት ሰኞ አንድ የቴሌቭዥን ጋዜጠኛ በቦምብ መገደሉ ተገለጠ።
የተመድ ዋና ጸሃፊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ውስጥ በድርጅቱ ሰላም አስከባሪዎች ላይ የተፈፀምው ጥቃት እንዳስቆጣቸው ገለፁ ።
በያዝነው ወር በሚያበቃው 2017 ምሥራቅ አፍሪካ ላይ በተከሰተው አስከፊ ድርቅና ግጭት ምክንያት ከ37 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከባድ የምግብ እጥረት ገጥሟቸዋል።
አንድ የሶማልያ ከፍተኛ ባለሥልጣን በሰጡት ገለፃ፣ ሁለት የሶማልያ ወታደሮችና አሥራ ሁለት ነውጠኞች፣ አልሻባብ ባካሄደው ጥቃት ዛሬ አርብ መገደላቸው ታውቋል።
ሊብያ ውስጥና በሌሎችም የዓለም ክፍሎች መውጫ አጥተው የሚገኙ ዜጎቻቸውን ለመመለስ የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪ ቃል ገቡ።
ከዓለም ሕዝብ ከግማሽ የሚበልጠው ማኅበራዊ ጥበቃ የማያገኝና ማለቂያ በሌለው የድኅነት ቀለበት ውስጥ የሚኖር ነው ሲል ዓለምአቀፉ የሥራ ድርጅት አስታወቀ።
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የሦስት ቀናት የአፍሪካ ጉብኝታቸውን፣ ዛሬ ማስከኞ ከቡርኪና ፋሶ በመጀመር፣ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሮቸ ማርክ ክርስቲያን ካቦረ ጋርም መገናኘታቸው ተገለፀ።
ጥቅምት 16 2010 ዓ/ም ድጋሚ የተደረገውን የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ኡሁሩ ኬንያታ ኬንያን ለሁለተኛ ጊዜ ለመምራት ቃለ መሓላ ፈጸሙ።
የዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎችና የሶማልያ መንግሥት ባካሄዱት የተቀናጀ የአየር ጥቃት፣ አንድ "አሸባሪ" መገደሉን፣ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ ዛሬ ሰኞ አስታወቁ።
ከ1985 እስከ 1987 ዓ.ም. በዩኒቨርሲቲ ኦቭ ዚምባብዌ፣ ከዚያም በደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርሲቲ ኦቭ ዊትዋተርስትራድ እና በዩናይትድ ስቴትስ ዴንቨር-ኮሎራዶ ሜትሮፖሊታን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስና የሂሣብ አያያዝ ፕሮፌሰር ሆነው አገልግለዋል፤ አሁንም እየሠሩ ያሉት ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ዚምባብዌ ባለፉ አርባ ዓመታት ያለፈችበትን ጉዞ ጠቅለል አድርገው ለቪኦኤ አጫውተዋል።
የሮበርት ሙጋቤ የ37 ዓመታት አስተዳደር ዘመን ሲያከትም ዚምባብዌ ዛሬ አዲስ ፕሬዚዳንት አግኝታለች።
ግብፅ በታወከው ሰሜናዊ ሲናይ በረሃ በሚገኝ ሕዝብ የበዛበት መስጊድ ተጠርጣሪ ታጣቂዎች ሁለት መቶ ሰላሳ አምስት ሰዎች መግደላቸውን የፀጥታ ባለሥልጣናት መናገራቸውን የመንግሥቱ ዜና ማሰራጫዎች አስታወቁ።
አፍሪካ በጋዜጦች ስለ አፍሪካ ከተፃፉት፣ የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
የዚምባብዌ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤና ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤ ያለመከሰስ ከለላ ተሰጣቸው።
ከሁለት ሣምንታት በፊት በያኔው የዚምባብዌ ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከሥልጣን ከተባረሩ በኋላ ለደኅንነታቸው በመስጋት በጎረቤት ሃገር የቆዩት የቀድሞው ምክትል ፕሬዘዳንት ኤመርሰን ናንጋግዋ ወደ ሃራሬ ተመልሰዋል።
ለሮበርት ሙጋቤ ውድቀት አንዱ ምክንያት እጅግ ለተራዘመ ጊዜ ሥልጣን የሙጥኝ ብለው መቆየታቸው መሆኑንና ቀደም ብለው አስረክበው ቢሆን ኖሮ እንደጀግና እንደተወደሱ ይኖሩ እንደነበር ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ለቪኦኤ በሰጡት ትንታኔ አብራርተዋል።
ለ37 ዓመታት ሥልጣን ላይ የነበሩት የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ሥልጣን ለቀቁ፡፡
የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥቅምት 16 በድጋሚ የተደረገውን የኬንያን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት አፀና። በዚህም ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ያሸነፉትን ምርጫ አፅድቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ