በጦርነትና ብጥብጥ ለተዋጠችው ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወደ ሰላም መሄጃው መንገድ አጥፍቶ አለመቀጣትን መዋጋት መሆኑን የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አስታወቁ።
ኢትዮጵያ በያዝነው የአውሮፓ ዓመት በዓለም እጅግ ፈጣኗ ምጣኔ ኃብት ትሆናለች ተብሎ ተተንብይዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ አስታውቀዋል።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት፣ የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
ዓለምቀፍ የፍልሰት ድርጅት /አይኦኤም/ ከአለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ 1 ሺህ 6መቶ 66 የቡሩንዲ ስደተኞችን በፍላጎታቸው ከታንዛኒያ ወደ ሃገራቸ እንዲመለሱ ማድረጉን ገልጿል፡፡
“የ2017ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሕገ መንግስቱና በጽሁፍ በተቀመጡ የአገሪቱ የምርጫ ሕጎች ድንጋጌ መሠረት ያለመካሄዱን ነው ያጤንነው። ግልጽም፣ በማረጋገጫ ሊደገፍ የቻለም አይደለም። በዚህ የሕጉ አግባብ እና በምርጫ ሕጉ አንቀጽ 83 የሕግ ትርጓሜ ብቻ እንኳን የምርጫውን ውጤት ውድቅ ከማድረግ የተለየ አማራጭ አልነበረንም።” ፊሎሜና ምዊሉ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት ‘ውድቅ ይደረግ’ ሲሉ፤ ውሳኔ ካሳለፉት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች አንዷ ናቸው።
ናይጀርያ ውስጥ የተለቀቁት ከ100 በለይ የሚሆኑ በቦኮ ሐራም ተጠልፈው የነበሩ “የቹፖክ ሴቶች” ናይጀርያ ባለው አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ በመግባት አዲስ ህይወት ጀምረዋል።
የትራምፕ አስተዳደር ለደቡብ ሱዳን ዜጎች በጊዚያዊ መልክ በዩናይትድ ስቴትስ የመቆየት ፈቃዳቸው እንዲራዘም ወስኗል። ለሱዳን ተወላጆች የሚሰጠው ፈቃድ ግን በመጪው አመት ያበቃል።
“በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እየተወሰደ ያለው ጥቃት ይቁም። ግድያዎቹ በገለልተኛ ወገን ይጣሩ።” ኢትዮጵያውያኑ ለዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እና ምክር ቤቶች ያስገቡት ደብዳቤ።
የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ክልላዊ የልማት በይነ መንግሥታት ባለልሥልጣን (ኢጋድ) አብዛኞቹ አባል ሃገሮች፣ ዜጎቻቸው በአባል ሃገሮች ውስጥ በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ የቀረበውን ሃሳብ ይደግፋሉ፡፡ ችግሩ ደቡብ ሱዳን ነገሩ ስላልጣማት እምቢታዋን መቀጠሏ ነው።
የኬንያ ሲቪል ማኅበረሰብ ጥምረት የኬንያ የምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች ላይ ምርመራ እንዲካሄድ በመጠየቅ ትላንት ማምሻዉ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።
ቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ ውስጥ የታጠቁ ሰዎች ዛሬ ረቡዕ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ቢሮ ቅፅር ግቢ ጥሰው ገብተው ጥቃት ማድረሳቸው ተገለጠ።
የኬንያውን የምርጫ ድራማ ቀጣይነት ያመላከተ በሚመልስ ሁኔታ፣ ፕሬዚደንት ኡሑሩ ኬንያታ፣ የገዢው ፓርቲ አባላት ብቻ የተገኙበትን የምክር ቤት ስብሰባ ማካሄዳቸው ተሰማ።
የሶማልያው አሸባሪ ቡድን አልሸባብ፣ ከኬንያ ጋር በሚያገናኘው ድንበር ላይ በምትገኝ አንድ ቁልፍ ከተማ ላይ ዛሬ ሰኞ ጥቃት ማካሄዱን ነዋሪዎች ተናገሩ።
በአናሳዋ የምዕራብ አፍሪካ ሀገር ቶጎ ውስጥ ትናንት ረቡዕ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመፅ፣ ከሃምሳ ዓመታት በላይ የዘለቀው የፕሬዚደንት ፋውራ ናሲንጌ ንጉሣዊ አገዛዝ እንዲያከትም መጠየቁ ተሰማ።
ታዛቢዎች በቅርቡ የተካሄድወን የአንጎላ ምርጫ "በሥርዓት የተካሄደና ሰላማዊ" ሲሉ አዎድሰዋል
የደቡብ አፍሪካ ተቃዋሚ ድርጅቶች የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማን ከሥልጣን ለማስወገድ ቆርጠው ተነስተዋል።
የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነሐሴ 2 ቀን 2009 ዓ.ም የተካሄደውን ፕሬዘደንታዊ ምርጫ ውጤት ውድቅ አድርጎ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ባለፈው ሣምንት ማዘዙ ይታወቃል።
የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን የፊታችን ጥቅምት 7 አዲስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚያካሄድ ገልጿል፡፡
“ነውጠኛው እስላማዊ ቡድን” ቦኮ ሀራም ካለፈው ሚያዝያ ጀምሮ ናይጄሪያና ካሜሩን ውስጥ ባካሄደው ጥቃት፣ ወደ 4መቶ ሲቪሎች በአጥፍቶ ጠፊ ቡድኖች መገደላቸውን፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።
ከምዕራባውያን ሀገሮች የፖለቲካ ሰዎች መካከል ሊብያን በቅርቡ በመጎብኘት የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዣን-ኢቭ ሊድሪያን አንዱ ሲሆኑ፣ ትናንት ሰኞ ከሊብያ የተለያዩ የፖለቲካና ወታደራዊ ተቀናቃኝ መሪዎች ጋር ውይይት አካሄደዋል።
በኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ ያለው ቬሩንጋ ብሄራዊ ፓርክ ትልልቅ የንግድ ተቋማትና በህገ ወጥ ተግባር የተሰማሩ ሰዎችን ዓይን የሣባ ከፍተኛ የተፈጥሮ ሀብት አለው።
የአለፈዉ ዓርብ የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት ውሳኔ በኬንያታ ደጋፊዎች ዘንድ ቅሬታ ሲያሳድር በተቀናቃኛቸዉ በራይላ ደጋፊዎች ዘንድ ግን ልዩ ደስታን ፈጥሯል።
ቡሩንዲ ውስጥ ከሚያዝያ 2007 ዓ.ም. አንስቶ ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ በመንግሥቱ ደጋፊዎች በሰብዕና ላይ ወንጀሎች ተፈፅመው ሊሆን እንደሚችል የጠቆሙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገለልተኛ ባለሙያዎች ዓለምአቀፍ ምርመራ እንዲከፈት ጥሪ አሰምተዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ