ደቡብ ሱዳን ውስጥ ታጣቂ ቡድኖች፣ ባለፈው ዓመት ከመንፈቅ ውስጥ ሃያ አራት የሕክምና መስጫ ጣቢያዎቻችንን ዘርፈውብናል፣ መንግሥት የተሻለ ጥበቃ ያድርግልን ሲሉ የሕክምና በጎ አድራጎት ድርጅቱ ድንበር የለሽ ሃኪሞች ዋና ኃላፊ ጠየቁ።
ሥጋት ውስጥ የወደቀው የግብፅ እስላማዊ ሕግ ዋናው ተቋም አል አዛር ዩኒቨርስቲ እስላማዊ ግዛት አልቃይዳና ሌሎች ነውጠኛ ቡድኖች ለሚከተሉት አምፅ አቀንቃኝ፣ እስላምና ዘመናዊ ለዘብተኛ ገፅታ ለመስጠት እየሠራ ነው፡፡
የቦኮሃራም ሽምቅ ተዋጊዎች ሰሜን ምሥራቅ ናይጀሪያ ውስጥ "ሰዎችን በፈንጂነት" የመጠቀማቸው ሁኔታ ባስፈሪ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መረጃ ድርጅት/ዩኒሴፍ/በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡
ከአንጎላ ሕዝብ ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የአንጎላ ህዝብ በመሪነት የሚያውቀው ፕሬዚዳንት ሆዜ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ ብቻ ነው።
በማዕከላዊ ኬንያ ገጠራማ አካባቢዎች ባለፉት ወራት ሁከቱ ተባብሶ መቆየቱ ተገለጠ።
በጦርነት ከታመሰችው ደቡብ ሱዳን ወደአጎራባች ዩጋንዳ የተሰደዱት ዜጎቿ ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን መብለጡን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።
"በኢራን የባሃይ፥ የክርስትና እና ሌሎች ሕዳጣን ማኅበረሰቦች በዕምነታቸው ሳቢያ ይሳደዳሉ። ኢራን ዕምነትን በመጣል በሚለው የተድበሰበሰ ሕጓ አማካኝነት በዜጎች ላይ የሞት ቅጣት መበየኗን ቀጥላለች።
ኬንያዊያን ባለፈው ሣምንት የተካሄደውን ምርጫ ውጤት እንዲቃወሙና ዛሬ - ሰኞ ከየቤታቸው ሳይወጡ እንዲውሉ ተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ጥሪ አስተላልፈው የነበረ ሲሆን አንዳንዶች ጥሪውን ተቀብለው ማደማቸውና ብዙዎች ደግሞ ወደ ሥራ መግባታቸው ታውቋል።
ዓለምቀፍ ታዛቢዎች ኬንያ በብሔራዊ ደረጃ በአካሄደችው ምርጫ “የመለኪያውን ፈተና አልፋለች” ብለዋል።
ሕገ ወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች ሁለት መቶ ሰማኒያ ፍልሰተኞችን በየመን ባህር ውስጥ ገፍትረው መጣላቸው ታወቀ።
የኬንያ ፕሬዘደንታዊ ምርጫ ውጤት ነገ ዓርብ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ኬንያውያን ትናንት ያካሄዱትን የምርጫ ውጤት እንዳይቀበሉ፣ ዋናው የተቃዋሚ መሪና ፕሬዚዳንት፣ ዕጩ ተወዳዳሪው ራይላ ኦዲንጋ ጥሪ አሰሙ፡፡
የኬንያ መራጮች ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ መንበረ ስልጣኑ ላይ መቆየት አለመቆየታቸውን በሚለየው በዛሬው ምርጫ፣ ከማለዳ ጀመረው ወጥተው ድምፃቸውን ሲሰጡ ውለዋል።
አፍሪካ ነክ ርዕሶች
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜ ለሦስተኛ ጊዜ ያሸንፋሉ ተብሎ በሰፊው በሚወራበት በአሁኑ ወቅት፣ ሩዋንዳ ነገ ዐርብ ወደ ድምፅ መስጫ ጣቢያ ያመራሉ።
“ክርክሩ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን መነጋገሪያ መድረክ የት ነው? እያንዳንዱ ሰው ከራሱ መንገድ ነው የሚጽፈው። በታሪክ ሞያ ውስጥ ይሄን ምንድን ነው የምንለው? መርጦ ማስታወስ እና መርጦ መርሳት። የተወሰኑ ነገሮች ተመርጠው ይታወሳሉ። ተመርጠውም ይረሳሉ። ታዲያ እነኚህ ጨርሶ እውነታ የላቸውም ማለት አይደለም። ነገር ግን ጎዶሎ እውነታዎች ነው የሚሆኑት። የራስን ፍላጎት ለማስፈጸም ነው የሚውሉት።” ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ።
የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ኃላፊ፣ ምርጫው ዘጠኝ ቀን ሲቀረው ሞተው ተገኙ፡፡
አፍሪካ በጋዜጦች - ስለ አፍሪካ የተጻፉ
የዩጋንዳ ፓርላማ የመሬት ይዞታ ጉዳዮችን በሚመለከት በሕገ መንግሥት ማሻሻያ ላይ እየተነጋገረ ነው።
ሦስት የአፍሪካ ሀገሮች አንጎላ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ በፊታችን የአውሮፓውያን ነሃሴ ወር ብሔራዊ ምርጫ ያካሄዳሉ፡፡
ሦስት የአፍሪካ ሃገሮች በነዳጅ ዘይት የበለፀገቸው አንጎላ፣ በምሥራቅ አፍሪካ ትልቅ ቦታ ያላት ኬንያና በፍጥነት እያደገች ያለችው ሩዋንዳ በመጪው ወር አቢይ ምርጫዎች ለማካሄድ ተዘጋጅተዋል።
ሁለት ትላልቅ የናይሮቢ ሆቴሎች ከኮሌራ በሽታ መቀስቀስ በተያያዘ እንዲዘጉ የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አዘዙ።
ለአሥር ዓመታት በ”ሱባዔ ቤት ቆዩ” የተባለው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሦስተኛ ፓትሪያርክ መለቀቃቸው ታውቋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ