አል ሻባብ የኢትዮጵያ ጦር ይገኝባት የነበረችውን ኤል ቡርን ያለውጊያ ተቆጣጠረ፡፡
በምሥራቅ አፍሪካ የተከሰተው ድርቅ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በገደለባት ሶማሌላንድ መንግሥቱ የልማት ሥራዎችን አቁሞ የገንዘብና አስተዳድራዊ ትኩረቱን ህይወት በማዳን ሥራ ላይ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
የምግብ ዋስትናን በዓለም ዙሪያ ማረጋገጥ የዩናይትድ ስቴትስ ጥቅም ጉዳይ መሆኑ ላለፉት ሁለት ቀናት መጋቢት 20 እና መጋቢት 21 / 2009 ዓ.ም. ዋሺንግተን ዲሲ ላይ በተካሄደው ዓመታዊው የዓለም የምግብ ዋስትና ጉባዔ ላይ ተገልጿል፡፡
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት፣ የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
ጆአኪም ደመር ይባላል። ስዊድናዊ የዶክሜንትሪ ወይም የዘጋቢ ፊልም ሠሪ ነው።
በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገሮችን በመጉዳት ላይ ያለውን ድርቅ “ድምጽ አልባው ቅስፈት” ሲሉ የዩናይትድ ስቴይትስ ኮንግረስ አባላት የምስክር ሰሚ ሸንጎ አስችለዋል።
የቀድሞውን ደቡብ አፍሪካ ዘረኛ ስርዓት ሲታገሉ የኖሩት አህመድ ካትራዳ በ87 ዓመት እድሜያቸው አረፉ። ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ሮብን ደሴት ላይ ለ18 ዓመታት ያህል በእስር ማቀዋል።
የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ትብብር /ኢጋድ/ ባለሥልጣን ባለፈው ቅዳሜ ባካሄደው ስብሰባ ወደ ሀገራቸው በፍላጎታቸው ለሚመለሱ የሶማልያ ተወላጆች ሁኔታዎችን ለማመቻቸትና ሶማልያ ውስጥ ስላለው የፖለቲካና የፀጥታ ሁኔታ መፍታኄ ለማበጀት ተስማምተዋል።
ከጁባ ወደ ፒቦር ሲጓዙ የነበሩ ስድስት የረድዔት ድርጅት ባልደረቦች ባለፈው ቅዳሜ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ተገድለዋል።
አዲሱ የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በትላንትናው ዕለት ሃገራቸው ወደ ቸነፈር ሊለወጥ የተቃረበውን ረሃብ ለማስወገድ በያዘችው ጥረት ይረዳ ዘንድ ዓለምቀፉን ማኅበረሠብ ተማፅነዋል።
ሱዳን፣ በኬሚካላዊ ጦር መሣሪያ ዕገዳ ድርጅት ውስጥ ወሳኝ ቁልፍ ሚና ተሰጣት፣ በአንዳንድ ተንታኞች ዘንድ ግን፣ የድርጅቱን ተዓማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ውሳኔ ነው በሚል ነቀፋ አስነስቷል።
የዓለም ሚቲኦሮሎጂ ቀን መጋቢት 14 “ደመናን መረዳት” በሚል መሪ ቃል በመላው ዓለም ታስቦ ውሏል፡፡
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በሦስት የአፍሪ ሀገሮችና በየመን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይውት ሊያጠፋ የሚችል ረሃብ ለመግባት የቀረው የአራት ወራት ጊዜ ነው ሲል አስጠንቅቋል።
በቅርቡ ወደ ጋምቤላ ክልል በመግባት ሃያ ስምንት ሰዎችን የገደሉትና ሕፃናትን ጠልፈው የወሰዱት ዶ/ር ሪያክ ማቻር ከሚመሩት አማፂያን ጋር ሕብረት የፈጠሩ ሙርሌዎች ናቸው ሲሉ በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ተናገሩ፡፡
“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ባይታወጅ ኖሮ የት ነው የሚቆመው አመጹ? የት ነው ጋብ የሚለው ነገር በጣም አጠያያቂ ነው የነበረው።” አቶ አታክልት አምባዬ። “የአስቸኳይ ጊዜውን አዋጁን ያወጁትም ሰዎች መፍትሔው እንፈልጋለን መፍትሔ አልተፈለገም። መፍትሔው ምንድ ነው? ችግሩ ምንድነው? የሚለው ነገር ላይ ውይይት አላየንም።” አቶ ፈቃደ ሸዋ ቀና።
የቆይታ ጊዜው ከአንድ ወር በኋላ የሚጠናቀቀው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ በከፊል ሊራዘም እንደሚችል ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡
“በተለያዩ ሁኔታ በፍርድ ቤት ሂደቶች አልፈው ጉዳያቸው ሳይሳካላቸው ቀርቶ ነገር ግን ወንጀል ስለሌላቸው ሊሆን ይችላል ከአገር ያልተባረሩ፤ በዓመት ወይ በስድስት ወር አንዴ ወደ ኢሚግራሽን መሥሪያ ቤት እየፈረሙ በሰላም የመሚኖሩ .. ለእነኚህና ለሌሎች አሁን አሳሳቢ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።” የሚ ጌታቸው በካሊፎኒያ የአሜሪካ የሕግ-ጠበቆች ማኅበር የሳንታክላራ ቫሊ ሊቀመንበር።
“የልብ ትርታ መረበሽ ብዙውን ጊዜ ያንን ያህል ለጤና የሚያሰጋ ነገር የለውም። ምን ሊሆን ይችላል በሚል ግለሰቡን ማሳሰቡ ነው። ነገር ግን ረዘም ላለ ጊዜ ተደጋግሞ ሲመጣ፥ ከእርሱ ጋር ተያይዞም የትንፋሽ ማጠር እና ደረት ላይ ጫና በሚሰማበት ጊዜ ግን ሌላ ክትትል ሊያስፈልገው ይችላል።” ዶ/ር ውብሸት አየነው የልብ ሕክምና ከፍተኛ አማካሪ ሃኪም ናቸው።
ጉዳዩን በውጭ ሆነው የሚከታተሉ የሟቾቹን ቁጥር 13 ያድርሱታል። ታፍነው የተወሰዱት 27 እንደሆኑ ሲናገሩ። በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል ይላሉ።
በደቡብ አፍሪካ ከሁለት ዓመት በኋላ በድጋሚ ባገረሸው በመጤዎች ጥላቻ ላይ ያነጣጠረ ዝርፊያ ፕሪቶሪያ "አትረጅቪል" በተባለች መንደር ውስጥ ሙሉ የሱቅ ንብረታቸውን እንደተሰረቁ ሁለት ኢትዮጵያውያን ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ። በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ሱቃችን ሲዘረፍ ይሄ ሁለተኛ ጊዜያቸው እንደሆነ የተናገሩት ነጋዴዎች “ሱቆቹን ያሟላነው ተበድረን ነበር። ዕዳውን ሳንከፍል ከነቤተሰቦቻችን ቧዶ እጃችንን ቀረን ብለዋል።”
የመሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ከበሬታ የተመረኮዘው የዓለም ሠላምና መረጋጋት “ደንታ ቢስ የፖለቲካ ጥቅም አግበስባሶች” በሚባሉት አደጋ ተደቅኖባቸዋል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዜይድ ራዓድ አል ሁሴን አስጠነቀቁ።
በ1ሺኽ 5 መቶ የዓለም ሻምፒዮኗ ገንዘቤ ዲባባ በዓለም አቀፉ የ ቪልላ ድ ማድሪድ አንድ ሺኽ ሜትር ሩጫ ውድድር የግልዋን ፈጣን ጊዜ አስመዝግባ አሸነፈች።
የኦሮምያና የሶማሌ ክልል አዋሳኝ በሆኑ ወረዳዎች በታጣቂዎች ለሚፈፀምው ጥቃት መፍትሄ ለማስገኘት በአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስትና በሁለቱ ክልሎች ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት አስታወቀ፡፡
ከሊብያ ወደ ጣልያን በሚወስደው የሜዲቴራኔያን ባሕር መሥመር ላይ የሚሞቱ ፍልሰተኞች ቁጥር ማሻቀቡን የሚያሳዩ ሪፖርቶች እየደረሱት መሆኑን ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤም አስታወቀ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የምግብና እርሻ ድርጅት /FAO/ በሁኔታው ቤተሰቦችና አርብቶ አደሮች እየተሰቃዩ ነው እንደሆነ አስታውቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ