በሊቢያ ሰሜናዊ የባሕር ወደብ፣ ቢያንስ ሰባ አራት የአፍሪካውያን ፍልሰተኞች አስከሬን ማግኘቱን፣ የሊቢያ ቀይ ጨረቃ ዛሬ ማክሰኞ አስታወቀ።
ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ታዋቂው የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት በተለይ በኢኮኖሚ ታሪክ ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ሥራ መስራታቸውን አንጋፋ ኢትዮጵያዊ ሙሑር ተናግረዋል፡፡
18ኛው የኢትዮ ሱዳን የድንበር ልማት ስብሰባ መቀሌ ከተማ ውስጥ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
“የሕጉን መሠረት ሲጥሉ ይሄው እስካሁን ድረስ ከሞላ ጎደል በዚያ ማዕቀፍ ሥር ነው ይሄ ማኅበረሰብ የሚንቀሳቀሰው። ምን ድነው መርሳት የሌለብን ያችኛዋ አሜሪካ በ1789 ሕገ መንግስት የተወለደችውን። ይሄ ኅገ-መንግስት ሲቀረጽ በጊዜው ለማን ነው የተቀረጸው? የሚለውን ነው።” ዶ/ር ብሩክ ኃይሉ የፖለቲካ ሳይንስ መምሕር
"ጆን ብራውን በጣም የተበሳጨ አሜሪካዊ ነው፡፡ ባርነት የማስወገጃው ብቸኛ መንገድ ተቋሙን በአምፅ ማሰወገድ ነው ብሎ ያምን ነበር፡፡ በጦርነት መደምሰስ" የሀርፐርስ መሪ ብሔራዊ ፓርክ ዋና የታሪክ ተመራማሪው ዴኒስ ፍራይ የባርነት መሪና ተቃዋሚው ጆን ብራውንና ጓዶቹ ያንን የአሜሪካ የፅልመት ዕድሜ ለማብቃት የጀመሩትን ትግል ያስታውሳሉ፡፡
ኬንያ ውስጥ ሰባት የሐኪሞች ማኅበር ባለሥልጣናት ለአንድ ወር በእስር እንደሚቆዩ ተገለፀ።
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዓለም እጅግ ግዙፍ የሚባለው የስደተኞች መጠለያ ሠፈር እንዳይዘጋ ማገዱን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች አሞግሰዋል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሠባት አብዛኞቹ የእስልምና ዕምነት ተከታይ በሆኑ ሀገሮች ዜጎች ላይ የጣሉት የጉዞ ገደብ እንዲፀና ያቀረቡትን ጥያቄ የዩናይትድ ስቴትስ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ትላንት ማታ ውድቅ አደረገ።
አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሞሃመድ ኣብዱላሂ የሀገራቸውን ስም ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ትረምፕ የጉዞ እገዳ ዝርዝር ላይ ለማስፋቅ ጥረት እንደሚያደርጉ አስታወቁ።
በአመዛኙ ሙስሊም ከሆኑ ሰባት ሀገሮች ፍልሰተኞችና ስደተኞች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥለውት የነበረውን የማስፈፀሚያ ትዕዛዝ ያስቆመው የሴአትል ዳኛ ውሣኔ በይግባኝ ሰሚ ችሎት ፀና፡፡
ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ መንግሥቱ የዳዳብን መጠለያ ጣቢያ እንዳይዘጋ ከለከለው።
ሶማልያ አዲስ ፕሬዚዳንት መርጣለች፤ ትናንት ነው የሶማሊያ ፓርላማ በሁለተኛ ዙር ምርጫ ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድን የመረጣቸው። አዲሱ ፕሬዚደንት የተመረጡት የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ መሃሙድን 184 ለ97 በሆነ ድምፅ ብልጫ አሸንፈዋቸው፡፡
የሶማልያ ምክር ቤት አባላት ቀጣዩን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ በሰጡት ድምጽ “ፋርማጆ” በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ የበዛ ድምፅ በማግኘት ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንትነት ሆነው ተመርጠዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የጉዞ ዕገዳ ሕግ፣ ኬንያ ውስጥ ውዥንብር ፈጥሯል።
ከሊቢያ ተነስተው በሜዲተራኒያን ባህር አቋረጠው ወደ ጣሊያን ለመግባት በጉዞ ላይ የነበሩና ባጋጠማቸው አደጋ የድረሱልኝ ጥሪ ያሰሙ 1500 ስደተኞች በጣሊያን የባህር ላይ ጠባቂዎች አማካኝነት ሕይወታቸው ተርፏል።
ዛሬ ጥር 29 በሴት የመራቢያ እና የፆታ አካላት ላይ የሚፈፀም ማንኛውም ጉዳት ይህም ማለት ግርዛት፣ መተልተል፣ መስፋት የመሳሰሉ ኢ - ሰብዓዊ አድራጎቶችን የመቃረኛ፣ የማውገዣ፣ ዓለም አቀፍ ቀን ነው፡፡
የፊታችን ረቡዕ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሚካሄድባት ሶማሊያ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለሕዝብ ተወካዮች በርካታ ገንዘብና እጅግ ውድ ስጦታዎችን እየሰጡ ይገኛሉ ሲሉ የምርጫ ታዛቢዎች ተናገሩ።
በእግር ኳስ የካሜሮን አንበሶች ጠንካራውን የግብፅ ብሔራዊ ቡድን አሸንፈው የአፍሪካን ዋንጫ ወሰዱ፤ የመጀመሪያውን ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተቀበሉ።
ኬንያ፣ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳንን አገናኝቶ ወደ ምዕራብ አፍሪካ የሚዘልቅ የትራንስፖርት መተላለፊያ መሥመር ግንባታ ተጀምሯል፡፡
በጋቦን አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየው 31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የፊታችን እሁድ ለፍፃሜ የሚጋጠሙት ሁለት ብሔራዊ ቡድኖች ዛሬ ታውቀዋል፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ የስልጣን ሽግግርና በአፍሪካ ሃገሮች ደህንነት ላይ ያተኮረ ውይይት ባለፈው ዓርብ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ተካሂዷል።
አዲሱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃሃፊ አንቶንዮ ጉተሬስ ድርጅቱ ደቡብ ሱዳን ውስጥ “የባሰ ሁኔት እንዳይፈጠር” እየጣረ ነው ብለዋል።
የአፍሪካ ሕብረት ከዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት “የመውጣት ስትራቴጂ” ባለው እርምጃ እየገፋ ነው።
"የአሜሪካ ድምጽ 75ኛ ዓመቱን ሲያከብር፤ የተቋቋመብትን ዓላማ ለማሳካት በተለያዩ የመገናኛ መንገዶች መረጃ ማሰራጨቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለመግለጽ እወዳለሁ። እውነተኛ፣ ተዓማኒ፣ ገለልተኛና የማይወግን የዜናና መረጃ ላለፉት 75ዓመታት እንዳሰራጨን ሁሉ ለቀጣይ 75 ዓመታት የምናደርገውም ይሄንኑ ነው።"አማንዳ ቤኔት የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ዳይሬክተር
አሜሪካ ወደ ሃገርዋ የሚመጡ የውጭ ሃገር ሰዎች ላይ ገደብ ስታደርግ የመጀመሪያ ጊዜያዋ አይደለም፡፡ ታዲያ በዜግነታቸው እየለየች “አትምጡብኝ፡” ብላ ታውቃለች እንዴ? “እንዴታ!”
ተጨማሪ ይጫኑ