ግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ አቅራቢያ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ዛሬ ዓርብ ተኩስ የከፈተው ታጣቂ ቢያንስ አራት ሰዎች ገደለ። ሌሎች አምስት ሰዎች አቁስሏል። ከሞቱት መካከል አንዱ ፖሊስ መሆኑ ታውቋል።
“ለመቀራረብ የሚረዱት ነገሮች በአገዛዙ እጅ ነው ያሉት። አንደኛ የመወያያ መስመሮችን በሙሉ ነጻነት እንዲኖሩ ማድረግ። ሁለተኛ ምንም ተጨባጭ ወንጀል ሳይኖርባቸው፤ በፖለቲካ ምክንያት ሃሳባቸውን በነጻ በመግለጻቸው ብቻ የታሰሩ ሰዎችን መልቀቅ። እነኚህ ለዜጎች በሙሉ እንደ አዲስ እንድንጀምር፤ ቂምንና ጥላቻን እንድንሰርዝ ይረዱናል። በእነኚህ በትንንሽ ነገሮች ብንጀምር ጥሩ ነው እላለሁ።” ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም
ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ ብትጥልብኝም በአደባባይ የፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር መንግሥትን ወክዬ መናገሬን አልተውም ሲሉ የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ማይክል ማኩዌ ተናገሩ።
ዩናይትድ ስቴትስ ትናንት ሶማሊያ ውስጥ ባደረሰችው የአየር ጥቃት አራት የፅንፈኛው አልሸባብ አባላት መግደሏን እና ዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ አቅራቢያ ፈንጂ ጭኖ ይጓዝ የነበረ መኪና ማውደሟን የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ ዛሬ አስታወቀ፡፡
"ከስምንታችን መሃከል አንድ እርሡ ወንድሜ ብቻ ነው የታሰረው። እንደሚመስለኝ ወንድሜ ተዋጊ ወታደር መስሏቸው ይሆናል። ነገር ግን እርሱ ተዋጊ ወታደር አይደለም።" ግሬስ ገበ ቁጥሩ 30 ሺህ የሚደርስ ስደተኛ በማስተናገድ ላይ በምትገኘው የድንበር ከተማ አባ ከተጠለሉ ደቡብ ሱዳናውያን አንዷ።
ላይቤሪያዊያን መጭውን ፕሬዚዳንታቸውን ለመምረጥ ትናንት ሲሰጡ የዋሉትን ድምፅ ውጤት በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን እየገለፁ ነው።
በኢትዮጵያ የታሪክ መዝገብ በሥነ-ጥበብ ምዕራፍ በሙዚቃው ገፅ ላይ ጎልተው ካሉ ስሞች አንዱ በረከት መንግሥትአብ ተብሎ ይነበባል።
"የፀጥታው ሁኔታ ተሻሽሏልና፣ አሁን ዓለማቀፍ ውድድሮችን ማስተናገድ ይቻለናል" ሲሉ፣ የሶማልያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት አስታወቁ።
በቅርቡ ሥልጣናቸውን የለቀቁት የዚምባብዌ ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤ ከሁዳዶቻቸው/ከመሬታቸው/ ካባረሩዋቸው ነጮቹ ገበሬዎች መካከል የመጀመሪያ ትናንት ሃሙስ ወደመሬታቸው ተመልሰዋል።
የደቡብ ሱዳን መንግሥትና የሽምቅ ተዋጊዎቹ ቡድን በ2015 ዓ.ም በከፍተኛ ደረጃ በተካሄደ ስብሰባ የተደረሰውን የሰላም ሥምምነት ለማንቀሳቀስ የሚያስችል፣ አዲስ የተኩስ አቁም ውል ተፈራረሙ።
የዩጋንዳ እንደራሴዎችና የፓርላማው ፖሊስ ትናንት ግብ ግብ ገጥመዋል። ምክንያቱ እንደራሴዎቹ የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት የዕድሜ ጣሪያ ገደብ ጉዳይ አንስተው እየተወያዩ ሣሉ ወታደሮች በፓርላማው ግቢ ውስጥ ታዩ መባሉ ነበር። “በዚያው የቃላቱ መሠናዘር ተቋርጦ የአካል ትንቅንቁ ተጀመረ” ብላለች የካምፓላ ሪፖርተራችን ሃሊማ አቱማኒ።
የደቡብ አፍሪካ ገዢው ኤኤንሲ ፓርቲ መልዕክተኞች ቀጣዩን የፓርቲው መሪ ለመምረጥ ማልደው ድምፅ መስጠት ጀምረዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ለሶማልያ ጦር የምሰጠውን ድጋፍ በአብዛኛው ልታቆም መሆኑን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለቪኦኤ አረጋገጡ። የሙስና መስፋፋትና የተጠያቂነት መጥፋት ናቸው ዋና ዋና ምክንያቶቹ ብለዋል ባለሥልጣናቱ።
የአውሮፓ ሕብረት ሀገሮች፣ ከሊብያ የሚነሱ ስደተኞችና ፍልሰተኞች የሜዲትራንያን ባሕር እንዳያቋርጡ በማድረግ፣ ለወከባና ለሰቆቃ እንዲዳረጉ ምክንያት ሆነዋል ሲል፣ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።
ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ ትናንት ሰኞ አንድ የቴሌቭዥን ጋዜጠኛ በቦምብ መገደሉ ተገለጠ።
የተመድ ዋና ጸሃፊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ውስጥ በድርጅቱ ሰላም አስከባሪዎች ላይ የተፈፀምው ጥቃት እንዳስቆጣቸው ገለፁ ።
በያዝነው ወር በሚያበቃው 2017 ምሥራቅ አፍሪካ ላይ በተከሰተው አስከፊ ድርቅና ግጭት ምክንያት ከ37 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከባድ የምግብ እጥረት ገጥሟቸዋል።
አንድ የሶማልያ ከፍተኛ ባለሥልጣን በሰጡት ገለፃ፣ ሁለት የሶማልያ ወታደሮችና አሥራ ሁለት ነውጠኞች፣ አልሻባብ ባካሄደው ጥቃት ዛሬ አርብ መገደላቸው ታውቋል።
ሊብያ ውስጥና በሌሎችም የዓለም ክፍሎች መውጫ አጥተው የሚገኙ ዜጎቻቸውን ለመመለስ የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪ ቃል ገቡ።
ከዓለም ሕዝብ ከግማሽ የሚበልጠው ማኅበራዊ ጥበቃ የማያገኝና ማለቂያ በሌለው የድኅነት ቀለበት ውስጥ የሚኖር ነው ሲል ዓለምአቀፉ የሥራ ድርጅት አስታወቀ።
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የሦስት ቀናት የአፍሪካ ጉብኝታቸውን፣ ዛሬ ማስከኞ ከቡርኪና ፋሶ በመጀመር፣ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሮቸ ማርክ ክርስቲያን ካቦረ ጋርም መገናኘታቸው ተገለፀ።
ጥቅምት 16 2010 ዓ/ም ድጋሚ የተደረገውን የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ኡሁሩ ኬንያታ ኬንያን ለሁለተኛ ጊዜ ለመምራት ቃለ መሓላ ፈጸሙ።
የዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎችና የሶማልያ መንግሥት ባካሄዱት የተቀናጀ የአየር ጥቃት፣ አንድ "አሸባሪ" መገደሉን፣ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ ዛሬ ሰኞ አስታወቁ።
ከ1985 እስከ 1987 ዓ.ም. በዩኒቨርሲቲ ኦቭ ዚምባብዌ፣ ከዚያም በደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርሲቲ ኦቭ ዊትዋተርስትራድ እና በዩናይትድ ስቴትስ ዴንቨር-ኮሎራዶ ሜትሮፖሊታን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስና የሂሣብ አያያዝ ፕሮፌሰር ሆነው አገልግለዋል፤ አሁንም እየሠሩ ያሉት ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ዚምባብዌ ባለፉ አርባ ዓመታት ያለፈችበትን ጉዞ ጠቅለል አድርገው ለቪኦኤ አጫውተዋል።
የሮበርት ሙጋቤ የ37 ዓመታት አስተዳደር ዘመን ሲያከትም ዚምባብዌ ዛሬ አዲስ ፕሬዚዳንት አግኝታለች።
ተጨማሪ ይጫኑ