አፍሪካ የካንሰር በሽታ ችግር እያደገ ሲሆን ጥራት ያለውና ውጤታማ ሕክምና የመስጠት አማራጮች ግን ውሱን ናቸው።
የቡሩንዲ መንግሥት እአአ በሚያዝያ 2015 እና በጥቅምት 2017 መካከል ባለው ጊዜ በፖለቲካ ተቃዋሚዎቹ ላይ ፈፅሟል የተባለውን የጦር ወንጀል፣ ዓቃብያነህግ ምርመራችውን መጀመር እንደሚችሉ፣ ዓለማቀፉ የወንጀል ችሎት ዛሬ ሐሙስ አስታወቀ።
የኬንያ ፖሊስ ባለፈዉ አርብ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸዉ 137 ህገ ወጥ የኢትዮጵያዉያ ፍልሰተኞች ላይ ትላንት ከሰዓት ብይን ሰጠ። በፍርዱም እያንዳንዳቸዉ 300 የአሜርካን ዶላር ወይም የ 6ወር እሥራት ተላልፎባቸዋል።
አሚሶም በሚል ምኅፃር የሚጠራው የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ኃይል ከሶማሊያ መውጣት እንደሚጀምር እዚያው የሚገኙት የተልዕኮው አዛዥ አስታወቁ።
ናይጄሪያ ውስጥ ባልፈው ወር የተጠለፉ አንድ ክርስቲያን ሚሲዮናዊ መምታቸውን እና ሌሎች ሦስት ሚስዮናውያን መለቀቃቸው የብሪታንያ መንግሥት ገለጠ።
የላይቤሪያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ ሳምንት ውስጥ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረውን ፕሬዚዳንታዊ ማጣሪያ ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፎታል። በመጀመሪያው ዙር ምርጫ የማጭበርበር ተግባር ተፈፅሙዋል የሚል ስጋት በመኖሩ መሆኑን አመልክቷል፡፡
የደቡብ ሱዳን የምግብ ችግር ይዞታ እየተባባሰ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተለያዩ የሠብዓዊ ረድዔት ድርጅቶችና የሀገሪቱ መንግሥት ያወጡት አዲስ ሪፖርት ገለጠ።
“በደርግ አባልነቴ ሰለባ ለሆኑት ሰዎች፥ በእነርሱም አማካኝነት ለመላው ኢትዮጵያውያን ተንበርክኬ ይቅርታ እጠይቃለሁ።” አቶ እሸቱ ዓለሙ። “አቶ እሸቱ፥ ዛሬም ‘ይህን በደል ፈጽሜያለሁ’ ሲሉ ወንጀሉን አላመኑም። በጸጸትም የተዋጡ ሰው አይደሉም።” አቶ ዓለሙ ጥሩነህ በጊዜው በእስር ቤት እንግልት ከደረሰባቸውና ከሞት የተረፉ ከዛሬው ሰባት ምሥክሮች አንዱ።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት፣ የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
ገጣሚ፣ መምህር፣ የፍልስፍና ሊቅ፣ ጋዜጠኛ ሰሎሞን ዴሬሳ ዛሬ ጥቅምት 23/2010 ዓ.ም. በሰማንያ ዓመት ዕድሜው አረፈ።
“የያዛችሁት የተሳሳተ ሰው ነው። “የእኔ ድርሻ የፕሮፖጋንዳ ሥራ ብቻ ነበር።” አቶ እሸቱ ዓለሙ። “ወንድሜና ሌሎች በጊዜው ታስረው የነበሩት ወጣቶች እንዲገደሉ ትዕዛዝ የሰጡት አቶ እሸቱ ስለመሆናቸው በፊርማቸው ያዘዙበትን ጨምሮ ብዙ ማስረጃ ተገኝቷል።” አቶ አብረሃም ብዙነህ ከከሳሽ አቃቤ ሕግ ምሥክሮች አንዱ።
አንድ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የጤና ድርጅት ባለሥልጣን በጦርነት ምክንያት ከሦስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለከባድ ረሃብ ስለተጋለጠባት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ደቡብ ምዕራባዊ ክፍለ ግዛት እያስጠነቀቁ ናቸው።
የጋዜጠኞች መገደል ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ምስጢር የሆነባት ሀገር ከመላው ዓለም ሶማልያ በአንደኛነት ትፈረጃለች ሲል፣ ለጋዜጠኞች መብት መጠበቅ የቆመው ኮሚቴ ሲፒጄ አስታወቀ።
“በገዢው ፓርቲ በኩል የሚሰሩትን ሥራዎች እንደ ጥሩ ነገር አይቼ ተቃዋሚው ላይ ግን ባለፉት ሁለት ዓመታት ከቆመበት የአክቲቪስት ፖለቲካ ወጥቶ፤ ማንኛውንም ብሶቶች በማራገብ ሰልፍ ግን ግብ አይደለም።” አቶ ኤልያስ ግደይ ከአዲስ አበባ። “የኢትዮጵያ ሕዝብ በያለበት ቦታ እያለ ያለው የምንፈልገው ነጻነት ነው። ስለዚህ ውስጥ ያለው መነሳሳት የሃያ ስድስት ዓመታት አገዛኣዝ አብቅቶ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መመሥረት ይችላል ነው።” አቶ ግዛው ለገሰ ከዋሽንግተን ዲሲ።
የኬንያ ምርጫ ቦርድ የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ያጣጣሉትን ምርጫ ውጤት ዛሬ ይፋ አደረገ። በምርጫው ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ 98 በመቶ ደምፅ አግኝተው ማሸነፋቸውን የኬንያ የምርጫ ቦርድ ኮሚሽነር ዋፉላ ቸቡካቲ ገልፀዋል።
ሊቢያ ቤንጋዚ ከተማ አቅራቢያ ቢያንስ ሠላሳ ሥድስት አስከሬኖች የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር ተገኘ።
ግብፅ ምዕራባዊ በረሃ ውስጥ የፀጥታ ኃይሎችዋ አሥራ ሁለት ፅንፈኛ ተዋጊዎችን ገድለዋል ስትል አስታወቀች።
ቡሩንዲ ከዓለምቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት /ICC/ በመውጣት የመጀመሪያ ሀገር ሆናለች። ቡሩንዲ ፍርድ ቤቱ በአፍሪካ ላይ ከልክ ያለፍ ትኩረት ስለሚያደርግ እወጣለሁ ብላ ካስታወቀች ዓመት ሆኗታል።
ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ፣ ለብዙ ጊዜ ሲጓተት የቆየውን ምርጫ በቀጣዩ ዓመት የማታካሂድ ከሆነ፣ በድምፅ አሰጣጡ ላይ ምንም ዓይነት ዓለምቀፍ ዕርዳታ እንደማታገኝ፣ የዩናይትድ ስቴትሷ ልዑክ ኒኪ ሄሊ አስታወቁ።
ኬንያውያን ዛሬ በሃገሪቱ ለሁለተኛ ጊዜ እንደገና በተካሄድው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ድምጽ ሰጥተዋል። ዛሬ ድምፅ ለመስጠት የወጣው ሕዝብ ቁጥር ነሐሴ 1 ቀን 2010 ዓም በተካሄደው በመጀመሪያው ምርጫ ከወጣው ያነሰ ቢሆንም ባንዳንድ የተቃዋሚው ፓርቲ ጠንካራ አካባቢዎች ግጭቶች መፈጠራቸውም ተዘግቧል።
ኬንያ ውስጥ ዛሬ የተካሄደው የፕሬዚዳንታዊ ማጣርያ ምርጫ በፖሊሶችና በተቃዋሚዎች መካከል ግጭት አስከትሏል። ተቃዋሚዎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች ደግሞ የምርጫ ጣብያዎች ሳይከፈቱ ቀርተዋል።
አፍሪካ ውስጥ ካለዕድሜያቸው በሚዳሩ ልጆች ብዛት ምዕራባዊ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሃገሮች ከፍተኛውን ቦታ የያዙ ናቸው።
ሞቃዲሾ ውስጥ እአአ ባለፈው ጥቅምት 14 ቀን በተፈጸመው ከባድ የቦምብ ጥቃት 358 ስዎች ተገድለው በመቶዎች የሚቆጥሩት ደግሞ በቆሰሉበት ወቅት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደም ለመለገስ ወደ ሆስፒታሎች እንደጎረፎ ተገልጿል።
የአውሮፓ ሕብረት $124 ሚልዮን ዶላር የሚሆን የሰብዓዊና የልማት ዕርዳታ ለሱዳን እንደሚሰጥ አስታውቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ