ከኬንያ የስደተኞች ካምፕ ተነስቶ የዩናይትድ ስቴትስ የሚኔሶታ ክፍለ ሃገር ምክር ቤት አባልነት መብቃት ዕውነት መንገዱን ሲያስቡት ዕውን የሚሆን አይመስልም።
ኬንያ ውስጥ ሊካሄድ የታቀደው የመጭው ምርጫ ዝግጅት በድምፅ መስጫ መሣሪያዎች ጉዳይ ላይ በተነሣው ውዝግብ ምክንያት ሊዘገይ እንደሚችል የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።
የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትናንት የገባውን አዲሱን የአውሮፓ 2017 ዓመተ ምህረት ምክንያት በማድረግ “በኤርትራ ላይ ቀጥሏል” ላሉት የፍትህ መዛባት በደል ዳግመኛ ትኩረት የሚስብ መልዕክት ለብዙ ሃገሮች መሪዎች ልከዋል።
የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ የፖለቲካ ፓርቲዎች እ ኤ አ 2017 ማብቂያ ሃገሪቱ ውስጥ ከሚካሄደው ምርጫ በኋላ ፕሬዘዳንት ጆሴፍ ካቢላ ሥልጣን እንዲለቁ ከስምምነት ደርሰዋል።
ሳምንታዊ የስፖርት ዝግጅት
ላለፉት ሦስት ዓመታት መረጋጋት ርቋት በቆየችው ደቡብ ሱዳን መንግሥቷ ሠላም ለማስፈን እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ላለፉት አጭር ዓመታት በዋና ፀሐፊነት ያገለገሉት ባን ኪ ሙን ዛሬ ታኅሣሥ 21/2009 ዓ.ም ተሰናብተዋል፡፡
ማሊና የአውሮፓ ህብረት በሕገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ የሚጎርፈውን ፍልሰተኛ ለማስቆምና ከደረሱ በኋላ ጥገኝነት የተከለከሉትን ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ላይ አሁንም ከስምምነት አልደረሱም።
ለኬንያ ምርጫ ማሻሻያ የተዘጋጀው አወዛጋቢ ሕግ ለመወሰኛው ምክር ቤት ቀርቧል።
ዛሬ ቃለ - መሃላ የፈፀሙት 281 የፓርላማ የሕግ መወሰኛና የሕግ መምሪያ አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ናቸው፡፡
ግጭቶችና አለመረጋጋት ከሦስት ዓመት በላይ ላልተለያት ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፖብሊክ አዲሱ 2017 የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
የአውሮፓውያኑ ዓመት 2016 ለአፍሪካ ምጣኔ ሃብት እድገት በጣም አዳጋች እንደሚሆን ተተንብዮ ነበር፡፡
በማዕከላዊ አፍሪካ ላይ ሲቪሎችን የሚገድልና የወሲብ ጥቃት የሚፈጽም አዲስ ታጣቂ ቡድን ተፈጥሯል።
የናይጀሪያ መንግሥት በሽብርና ሁከት ቡድኑ ቦኮ ሃራም ላይ ቁልፍ ነው ሊባል የሚችል ድል መቀዳጀቱን ገልጿል፡፡
ናይጀሪያ ውስጥ ሳምቢሳ ጫካ በሚባል ሥፍራ የሚገኝ የሁከቱ ቡድን ቦኮ ሃራም ይዞት የነበረ ወታደራዊ ሠፈር መቆጣጠሩን የሃገሪቱ ጦር አስታወቀ፡፡
ዌስት ባንክ ውስጥ በምትገኘው ቤተልሄም ወንድና ሴት ስካውቶች ማንጀር አደባባይ ላይ ባደረጉት የበዐል ሠልፍ ገናን አብሥረዋል፡፡
በአትሌቲክሱ የረዥም ርቀት ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያን በበርካታ ዓለምቀፍ መድረኮች በበላይነት ያስጠራው ዝነኛው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር በ72 ዓመት ዕድሜው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
የሊብያን አየር መንገድ አውሮፕላን ጠልፈው ዛሬ በሜዲተራኒያን ደሴት በማልታ ያሳረፉት ሁለት ሰዎች እጃቸውን ለፖሊስ መስጠታቸውን የማልታው ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ሙስካት አስታወቁ።
የሊቢያ አፍሪቂያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጠልፎ ማልታ አርፏል።
በ2017 ዓ.ም. ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በምታካሂደው ኬኒያ ውጥረቱ እየተባባሰ መጥቷል። በሀገሪቱ ምክር ቤት የምርጫ አፈፃፀም ሕግጋቱን ለመቀየር በቀረበ ሃሳብ ዙሪያ ክርክር በተካሂደበት ጉባዔ ላይ ድብድብ መቀስቀሱ ተዘግቧል፡፡
“በደማችን ውስጥ የሚገኝ የስኳር መጠን .. አመጋገባችን፥ የሰውነታችን ክብደት መጨመር እና የአካል እንቅስቃሴ መኖር ወይም ያለመኖር፤ ያኔ ‘የስኳር ሕመም ያዘኝ’ የሚባለው አባባል ይመጣል።” ዶ/ር ኤልያስ ሰይድ ሲራጅ የሥኳር ሕሙማን ክትትል ባለ ሞያ።
ቲቢ በድፍን ዓለም በገዳይነታቸው ቀዳሚ ከሆኑ በሽታዎች መካከል የመሆኑ ነገር እንደቀጠለ ነው፡፡ ባለፈው የአውሮፓ ዓመትም በቲቢ ምክንያት ሁለት ሚሊየን ሰው አልቋል፡፡
በኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ ኪንሻሳ ፕሬዚዳንት ካቢላ ከሥልጣን እንዲወርዱ በተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ ግጭት እስከ ሃያ የሚደርሱ ሰዎች ሳይገድሉ እንዳልቀሩ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሥልጣኖች ሲገልፁ፤ የአሜሪካ ድምፅ ‘ራድዮ አፍሪካ’ ጥቆማ ሦስት ሰዎች እንደተገደሉ አረጋግጧል።
1870 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጨው ጊቤ ሦስት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ዛሬ ተመረቀ።
በያዝነው ታህሣስ ወር የሚያበቃው 2016 ዓ.ም. “ለአፍሪካ ጋዜጠኞች፤ የጨለመ ዓመት ነው” ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ቡድን ሲፒጄ እንደሚለው፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ