ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስነው ድንበር ተሻግረው ጥቃት ባደረሱ የመሪሌ ጎሳ አባላት እንደተገደሉ የታወቀው ሰዎች ቁጥር ከ140 ወደ 208 ማሻቀቡን የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ። ከብት ዘራፊ የመሪሌ ጎሳ ታጣቂዎች 102 ህጻናትን አግተው ወደ ደቡብ ሱዳን ማምራታቸውን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቀዋል።
በማሊ፣ በቡርኪና ፋሶና በአይቮሪኮስት ሆቴሎች ላይ የአሸባሪ ጥቃቶች ከተደጋገሙ ወዲህ ምዕራብ አፍሪቃ በተጠንቀቅ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። አሁን ደግሞ ሾልከው የወጡ የጸጥታ ጉዳይ ሰነዶች እንዳመለከቱት ጋናና ቶጎ ከዐል-ቓዒዳ ጋር የተሳሰረው ጽንፈኛ ቡድን ቀጣዮቹ ኢላማዎች ናቸው። የጋና ፕረዚዳንት ጆን ማሀማ የሀገሪቱ እዝብ እንዲረጋጋ መክረዋል።
የሳምንቱ መገባደጂያ የእሁድ ምሽት የእረፍት ጊዜ የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ። የቴአትርና የሙዚቃ ወጎች:- ከአምስት ተዋናዮች፤ እንዲሁም በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለየው የሙዚቃ ሰው ህይወትና ሥራ፤ ከአንጋፋ ሙዚቀኞች ጋር፤
ይሁንና ምን ዓይነት አቀባበል እንደሚደረግላቸው እና መቼ ቃለ መሃላቸውን እንደሚፈጽሙ መንግስቱና ተቃዋሚዎቹ አሁንም ከስምምነት አልደረሱም።
ተቃዋሚዎቹ ጥያቄውን ያቀረቡት ትናንት ከብዙ ዓመታት በኋላ የመጀመሪያ የሆነውን የተቃውሞ ሰልፍ ባካሄዱበት ወቅት ነው።
ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በተከፈት የሚዩኒክ የጸጥታ ጉባኤ ላይ አውሮፓውያን ከአፍሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከመሰረቱ መለወጥ እንዳለባቸውም ተጠቁሟል።
የሀገሮች ምጣኔ ሃብት ቅንጅትና ንግድን የሚያስፋፉ ፖሊሲዎች በአፍሪካ ሀገሮች በአሁኑ ወቅት አነስተኛ መሆናቸው አሳሳቢ እንደሆነ ጂም ዮንግ ኪም በዛሬውለት ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል።
የመናውያን ባልተለመደ ሁኔታ በጦርነት ከዳሸቀችው ሃገራቸው የራሱ ህዝብ ለአሰርተ-አመታት ያህል ሲካሄድ በቆየው ግጭት ምክኒያት በአለም ዙርያ ወደ ተበታተነበት የአፍሪቃ ቀንድ አከባቢ እየሸሹ ነው።
ከዚያ ወዲህ ሃምሳ ሰባቱ ልጃገረዶች ከጠላፊዎቻቸው እጅ ያመለጡ ሲሆን ሁለት መቶ አስራ ዘጠኙ እስካሁን አልተገኙም። ቦኮ ሃራም ከሁለት መቶ በላይ ልጃገረዶችን በጠለፈ በሁለት ዓመቱ ብቅ ያለ አዲስ ቪዲዮ ለወላጆቻቸው በህይወት አሉ የሚያሰኝ ተስፋ ፈንጥቋል።
ባለፈዉ እሁድ በሞያሌ ከተማ የጣለ ከባድ ዝናብ በሰዉ ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ። ዝናቡን ተከትሎ በአካባቢዉ በደረሰ ከባድ ጎርፍ ማጥለቅለቅ የሶስት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የአካባቢዉ የቀይ መስቀል ባልደረባ ለአሜርካ ድምጽ ተናግረዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ (UNICEF)የናይጀርያው ጽንፋኛ የአማጽያን ቡድን ለአጥፍቶ ጠፊነት የሚጠቀምባቸው ልጆች ቁጥር እየጨመረ እንደሄደ ገልጿል። ቡድኑ ለማጥቃት ተግባር ከሚጠቀሙባቸው ልጆች 75 ከመቶዎቹ ሴቶች እንደሆኑ ዩኒሴፍ ጠቁሟል።
እ. አ. አ. ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ያለውን ውጊያ የሸሹ ብዙ ሺህ ዜጎች ድምፅ መስጠት ያለመቻላቸውደግሞ በረፈረንደሙ ተዓማኒነት ላይ ብዙ ጥያቄዎችን አስነስቷል።
የምስራቅዋ ጊሱሩ ከተማ ነዋሪዎች ሲናገሩ ሰባት ወንጀለኞች ገበያው ውስጥ እየሮጡ ከተኮሱ በኋላ አምልጠዋል ብለዋል።
እኩለ ሌሊት ላይ በደረሱት ጥቃቶች ሶስት ሲቪሎች እና አምስት የጽንፈኛው ቡድን ተዋጊዎች መገደላቸውን የኪስማዮ ባለስልጣን እና የመንደሩዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ዩኒሴፍ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ባለፈው እ.አ. አ. 2015 ዓ. ም. አርባ አራት ልጆች በቦኮ ሃራም አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃት መሳተፋቸውን ገልጾ ይህም ከዚያ በቀደመው ዓመት ከተሳተፉት አራት ልጆች ጋር ሲነጻጸር በአስር ዕጥፍ የሚበልጥ መሆኑን አመልክቷል።
በሮም ማራቶን አሸናፊዎቹ የሁለቱን አገሮች አትሌቶች ናቸው አሞስ ኪፕሩቶ በወንዶቹ፣ ራህማ ቱሳ በሴቶቹ ቀድመው ገብተዋል። በቪየና ከተማ ማራቶን የሴቶቹን በድል ያጠናቀቀችው ኢትዮጵያዊት ናት ሹኮ ገነሞ ትባላለች።
የዳርፉር ውሳኔ-ሕዝብ (Referendum)፣ ዛሬ ተጀምሯል። በዚህ ለሦስት ቀናት በሚዘልቀው ውሳኔ-ሕዝብ ዩናይትድ ስቴትስ ስጋት እንዳላት መግለጿ ታውቋል። "ውሳኔ-ሕዝቡ ተዓማኒነት አይኖረውም፣ የወቅቱን የሰላም ሂደትም ያደናቅፋል" የሚል ስጋት ነው ዩናይትድ ስቴትስ ያሰማችው። ዛሬ የተጀመረው ይህ የዳርፉር ውሳኔ-ሕዝብ፣ የክልሉን አምስት ግዛቶች የወደፊት ዕድል ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል።
ምክትል ፕሬዘዳንቱ ዊልያም ሩቶ እና የአንድ ያካባቢው ራዲዮ ጣቢያ ዲሬክተር፥ እጃቸው አለበት ተብሎ የቀረበባቸውን ክስ በዚህ ሣምንት ውድቅ መደረጉ ይታወሳል።
ሶማሊያ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ያለው ፅንፈኛ የሁከት ቡድን አል-ሻባብ እያደረሰ ያለው አደጋ እየበዛ መምጣቱ አሜሪካ በቡድኑ ይዞታዎች ላይ የምታካሂደውን የአየር ድብደባ እንድታጠናክርና እንድታሰፋ ያስገደዳት መሆኑን ዋሺንግተን እየተናገረች ነው።
የተለያዩ የኤርትራውያን ተቃዋሚዎች ሬድዮዎችና ድረ-ገጾች ግን የሞቱት ወጣቶች ብዛት ከአራት እስከ 11 ነው ይላሉ።
የቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አላን ኒያሚትዌ መንግስታቸው በፀጥታ ሐይሎችና በደጋፊዎቹ አማካኝነት የተቃዋሚዎችን መብት ይጥሳል ተብሎ ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የቀረበውን ውንጀላ ውድቅ አድርገዋል።
በድምጽ መስጫ ጣቢያዎች አካባቢ የነበረው ድባብ ሰላማዊ እንደነበር አንዳንዶቹ ድምጽ ሰጪዎች ሲናገሩ ብዛት ያለው ወታደር አይተናል ያሉም አሉ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማርክ ቶነር ባወጡት መግለጫ በምርጫው ሂደት በስፋት የተዘባ አሰራር እንደታየበት ጠቅሰው የድምጽ አሰጣጡ በሰላማዊ መንገድ ተጀምሮ በኋላ የተቃዋሚ ደጋፊዎች መታሰራቸው ሂደቱን አጉድፎታል ብለዋል።
የድንበር ቁጥጥርን ማጥበቅ አአሸባሪዎችን እንቅስቃሴ ሊገታ እንደሚች የዩናይትድ ስቴትስ የሥጋት ቅነሳ መርኃግብሮች አስተባባሪ አምባሳደር ቦኒ ጀንኪንስ ለአሜሪካ ድምፅ ድምፅ በሰጡት ቃል መክረዋል።
እ. አ .አ. ከ 1999 ዓ .ም. ጀምሮ በሥልጣን ላይ የቆዩት ሚስተር ጉለህ (Guelleh) አሁን ለሌላ የሥልጣን ዘመን የሚወዳደሩት፥ የሀገሪቱ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ እየተነገረ ባለበት ወቅት ነው።
ተጨማሪ ይጫኑ