ኦሮሚያ ክልል የሚካሄደው ተቃውሞ ሁለተኛ ወሩን ያዘ።
የአልሸባብ ደጋፊዎች እንደሆኑ የሚታመን ጠብመንጃ አንጋቢዎች ባለፈው ሰኞ ከማንዴራ ወደ ናይሮቢ ያመራ የነበር የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ማገታቸው ሙስሊም እና ክርስቲያን ተሣፋሪዎችን ለመለያየት ጥረት ማድረጋቸው ተዘግቧል።
አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራምን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። ብሪታንያ ተጨማሪ 30 ሚልዮን ፓውንድ ለኢትዮጵያ እንደምትሰጥ ታወቀ፣ በዎሎንኮሚ ኦሮሚያ የተፈጸመው ግድያ፣ ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር መተማመን የማዳበር ፍላጎት እንዳላት ገለጸች፣ ኬንያውያን ሙስሊሞች ክርስትያኖችን ከሞት አዳኑ የሚሉትን ርእሶች ነው በዛሬው ቅንብራችን የምንመለከተው።
እንኳን ለ1490ኛው የነብዩ መሐመድ የልደት ቀን - መውሊድ አደረሣችሁ።
ህጋዊና ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን በኃይል ለማስቆም እየተፈፀሙ ያሉ ግድያዎችና አፈናዎች ይቁሙ፤ በወንጀል የተሣተፉም ለፍርድ ይቅረቡ - ሲል ተቃዋሚው መድረክ ጥያቄ አቀረበ።
የቡሩንዲ መንግሥት የአፍሪካ ኅብረትን ሰላም አስከባሪ ጦር እንደማይቀበል በይፋ አስታውቋል፡፡
በጥቂት ቀናት ውስጥ የሚያበቃው የአውሮፓ 2015 ዓመተ ምሕረት ለአብዛኛው የአፍሪካ አህጉር የረሃብ ዓመት ሆኖ ሊያልፍ ነው።
የደቡብ ሱዳን መንግሥት ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የቆየውንና የመጀመሪያዎቹ አባላቱ ዛሬ ጁባ የሚገቡትን የአማጽያኑን ቀዳሚ ቡድን ለመቀበል በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ ።
ከአንድ ሣምንት በኋላ በሚጠናቀቀው የአውሮፓዊያኑ ዓመት 2015 አፍሪካ ምርጫዎችን፣ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎችን፣ ሕገ-መንግሥታዊ ለውጦችንና የሥልጣን በሰላማዊ መንገድ መተላለፍን አስተናግዳለች።
በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ፣ በጉጂ ዞን፣ በሃርቀሎ ወረዳና በሆሮ ጉዱሩ፤ በወለጋ ኢበንቱ ወረዳ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸውና በመከላከያ አባላት እየታሠሩ መሆናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡
በሳዑዲ አረቢያ ለሚመራው ፀረ-ሽብር ጥምረት ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጅ መሆኑን የኤርት መንግሥት አስታወቀ፡፡
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባልደረቦች የሆኑ ከመቶ በላይ ረዳት መምህራን ከሁለት ዓመታት በፊት ለጠየቁት የሥራ ዕድገት መልስ እስካሁን እንዳልተሰጣቸው እየተናገሩ ነው፡፡
እየተጠናቀቀ ባለው የአውሮፓ 2015 ዓ.ም ወደ አውሮፓ የገባው ፍልሰተኛ ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን መብለጡን ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤምና የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሺነር - ዩኤንኤችሲአር አስታውቀዋል፡፡
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አራተኛው ፓትሪያርክ አቡነ ዲዮስቆሮስ ከረዥም ጊዜ ህመም በኋላ ዛሬ ማረፋቸው ታውቋል።
ቡሩንዲ ውስጥ አሕጉራዊ አቃቤ ሰላም ኃይል እንዲሠማራ የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ወስኗል።
የፈረንሣይ አየር መንገድ አውሮፕላን፥ በሌሊት በረራ ወቅት በውስጡ ተጠርጣሪ ቦምብ በመገኘቱ፥ ሞምባሳ ኬንያ ላይ ሲደርስ መንገደኞቹ በሙሉ ወደሌላ አውሮፕላን እንዲዛወሩ ተደርገ።
የርዋንዳ ፕረዚደንት ፖል ካጋሜ ሀገሪቱ የፕረዚዳንትን የስልጣን ጊዜ የሚገድበውን ህገ-መንግስት ለመለወጥ በመወስናዋ አመስግነዋል።
ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ላይ ሲካሄድ የሰነበተው በእግሊዝኛ ስሙ ምኅፃር (WTO) እየተባለ የሚታወቀው የዓለም የንግድ ድርጅት ጉባዔ ዛሬ ማምሻውን ተጠናቀቀ። ድርጅቱ በዘንድሮው ስብሰባ የላይቤርያንና የአፍጋንስታንን የአባልነት ጥያቄ አጽድቋል።
በኦሮሚያ የሚካሄደው እንቅስቃሴ፣ ኤል ኒኖ የአፍሪቃን የኢኮኖሚ ሞተር ማቀዝቀዙ ተዘገበ፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ደቡብ አፍሪቃውያን ፕረዚዳንት ጃኮብ ዙማ ከስልጣን እንዲወርዱ ጠየቁ የሚሉትን ርእሶች ነው በዛሬው ቅንብራችን የምንመለከተው።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ባለሥልጣናት ቡሩንዲ ወደ እርስ በርስ ብጥብጥ ወደ ማዝቀጥ ጠርዝ ደርሳለች ሲሉ እያስጠነቀቁ ነው።
ሊብያ ውስጥ የሚገኙ ሁለት ተቀናቃኝ ምክር ቤቶች አዲስ የአንድነት መንግሥት ለመመስረት ተስማሙ። ምክር ቤቶቹ ከዚህ ስምምነት የደረሱት፣ በሞሮኮዋ የመዝናኛ ከተማ ስኪራት (Skhirat) ላይ ባካሄዱትና በርካታ መሰናክሎችን በድል በተወጡበት ውይይት ሲሆን፣ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር የሰየሙም መሆናቸው ታውቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ