ቻይና ለአፍሪካ ልማት ማፋጠኛ የሚውል ስድሳ ቢሊዮን ዶላር በብድርና በዕርዳታ መልክ ልትሰጥ መሆኑ ታወቀ።
በምእራብ ወለጋ ጨሊያ ከተማ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም ትላንት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና የአካባቢዉ ህዝብ ባደረጉት ሰልፍ ላይ አንድ ተማሪ መገደሉ ሌላ በጽኑ መቁሰሉና ታዉቋል።
“ቀድሞ የአምስት ሜትሮች ጥልቀት የነበረው የቻድ ሃይቅ ዛሬ ከአንድ እስከ አንድ ነጥብ አምስት ሜትር ጥልቀት ብቻ ነው ያለው። የሰው ልጆች አንዳች ሁነኛ እርምጃ በአፋጣኝ ተግባር ላይ እንዲያውሉ የሚጠይቅ የክፍለ ዘመኑ የከፋ ውድመት እየደረሰ ያለው።” የቻዱ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ናቸው። የዓየር ንብረት መዛባት ባስከተለው ጉዳት ክፉኛ እየተራቆተ ስላለው የቻድ ሃይቅ ከተናገሩት የተወሰደ።
የዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል (Amnesty International) ባወጣው መግለጫ ኤርትራ ከሕዝቧ እየተራቆተች መሆንዋን ገልጿል።
ዋና መሰረቱ ሶሪያ የሆነው ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው ቡድን ዋና እንቅስቃሴውን ወደኣፍሪካ ኣህጉር በማስፋት ከናይጄሪያ ኣንስቶ ሶማሊያ ድረስ እስልምና ኣክራሪዎችን ለመሳብ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉ ኣንድ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ወታደራዊ ዕዝ አዛዥ ለቪኦኤ ገለጡ ።
ዩናትድ ስቴትስ (United States) የቡርኪና ፋሶ ህዝብና መንግስት የሀገሪቱን አንድነት ለመጠበቅና የሀገሪቱን ተቋማት ለማጠናከር በሚያደርጉት ጥረት ከነሱ ጋር በአጋርነት መስራቱን ለመቀጠል በጉጉት እንደምትጠብቅ በመግለጫ አስታወቀች።
የካሜሩን ወታደራዊ ሃይሎች 100 የቦኮ ሐራም አማጽያንን እንደገደሉና በጽንፈኛው ቡድን ተይዘው የነበሩ 900 ሰዎችን እንዳስለቀቁ ካሜሩን ገልጻለች።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ከኤርትራ ከሚመጡ ስደተኞች መካከል ከ81,000 በላይ የሚሆኑ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ገብተው እንደሚኖሩ ቢገመትም አድራሻዎቻቸው በትክክል እንደማይታወቅ ገልጿል።
የጸረ ሙስና ቡድን ወይም ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል (Transparency International) ባወጣው ዘገባ ባለፈው አመት 75 ሚልዮን የሚሆኑ አፍሪቃውያን ጉቦ እንደሰጡ ይገመታል ይላል። አብዛኞቹ አፍሪቃውያን ሙስና እየተባባሰ ሄዷል እንደሚሉም ዘገባው ጠቁሟል።
የቀውድሞ የቡርኪና ፋሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮች ማርክ ክርስትያን ካቦሬ (Roche Marc Christian Kabore) የሀገሪቱን ፕረዚዳንታዊ ምርጫ አሸነፉ።
ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪቃ አገሮች የተመዘገበዉ የኢኮኖሚ እድገት ድህነትን በሚፈለገዉ መጠን አልቀነሰም ሲሉ አንድ የዓለም ባንክ ባለሙያ ተናገሩ።
የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ከፍተኛ ተደራዳሪዎች በሕግ ገዥ የሚሆን ስምምነት ዛሬ ፈረንሣይ ዋና ከተማ ፓሪስ ላይ ከተከፈተው የዓለም የአየር ንብረት ጉባዔ ይወጣል ብለው እንደሚያምኑ እየተናገሩ ነው።
የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ ሶስት ሃገሮች የጎበኙበትን የመጀመሪያ የኣፍሪካ ጉዞኣቸውን አጠናቀው ወደ ቫቲካን እየተመለሱ ናቸው።።
የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕረዚዳንት ሪያኸ ማቻር ደጋፊ አማጽያን ወደ 550 የሚሆኑ ሰዎችን ያጠቃለለ መርማሪ ቡድን ወደ 10 የሃገሪቱ ክፍላተ-ሃገር ሊልኩ ነው።
ኢትዮጵያ የመጀመርያውን ሰባት የአፍሪካ ሀገሮች የሚሳተፉበትን የሰርከስ ትርዒት እያስተናገደች ነው። በትርዒቱ ላይ ሚዛን መጠበቅ፥ ጂምናስቲክ፥ ኳስና ዱላ የመሳሰሉትን ወደ ሰማይ እያፈራረቁ በመወርወር መቅለብና ሌሎች ጨዋታዎች ቀርበዋል።
ገንዘቤ ዲባባ የዓመቱ የዓለም ምርጥ አትሌት ተባለች
በኦሮሚያ - ጊንጪ ከተማ ህዳር ዘጠኝ ቀን የጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም በምዕራብ ወለጋ ሁለት ከተሞች መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ሁለተኛ ጉባዔ ዛሬ ተፈፅሟል።
የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ የናይሮቢ ጉብኝታቸውን ያጠቃለሉት አንድ የተጎሣቆለ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች መኖሪያ ሠፈር ተመልክተው ነው።
በአንዳንድ የምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞች ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ሰላማዊ ሠልፎች እየተካሄዱ ናቸው፡፡
የመረጃ ነፃነት የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መረጋገጥና ሌሎች መብቶች መከበር መሣሪያ እንደሆነ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ አሳስበዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ