በኢቦላ ክፉኛ ከተጠቁት የምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች መካከል አንዷ የሆነችው ጊኒ ውስጥ ቫይረሱ ቀድሞ ባልደረሰባቸው አካባቢዎች አዳዲስ ሕመምተኞች እየታዩ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በኢራቅና በሶሪያ እሥላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለውን ታጣቂና ፅንፈኛ ቡድን እመታለሁ ያሉበትን ባለአራት ደረጃ ሥልት ይፋ አደረጉ፡፡
እንኳን ለአዲሱ 2007 ዓ.ም አደረሰዎ፡፡ ለወዳጅ ዘመዶችዎ የእንኳን አደረሣችሁ መልዕክት ማስተላለፍ ቢፈልጉ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በስልክ ቁጥር 202-205-9942 የውስጥ መሥመር 14 በተዘዋዋሪ ደውለው መልዕክትዎን ያኑሩ፤ ወይም በኢሜል horn@voanews.com ላይ ይላኩ፤ ወይም በፌስ ቡክ amharic@voanews.com ላይ ያስፍሩ በትዊተር voaamharic ብለው ትዊት ያድርርጉ፡፡ ከደረሰን ጊዜ ጀምሮ በመጭዎቹ ጥቂት ቀናት መልዕክትዎን ለአድማጭ እናበቃለን፡፡ አዲሱ ዓመት የጤና፣ የሰላም፣ የመግባባት፣ የተሣካ ሥራ ውጤትና የብልፅግና እንዲሆን እንመኛለን፡፡
የአፍሪካ ኅብረት ምዕራብ አፍሪካን እያመሰ ላለው የኢቦላ ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት ያስችላል የተባለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ አድርጎ በተጎዱት ሃገሮች ላይ የተጣሉት የጉዞና ሌሎቹም ዕገዳዎች ሁሉ እንዲነሱ ወስኗል፡፡
የአል-ሻባብ መሪ አህመድ አብዲ ጎዳኔ መገደሉን የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አረጋገጠ።
መላ አፍሪካ ውስጥ ሽብር ፈጠራንና ፅንኝነትን መዋጋት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ለመምከር የአፍሪካ መሪዎች ነገ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ላይ ይሰበሰባሉ፡፡ ተቃዋሚዎችን በሽብር ፈጣሪነት መፈረጅና መወንጀል አደጋ አለው ሲሉ አንድ አፍሪካዊ ባለሙያ አስጠንቅቀዋል፡፡
የሕግ ትንታኔ:- ግጭት በአሜሪካ፥ ተቃውሞን የመግለጽ ኅገ-መንግስታዊ መብትና የፖሊስ ሕግ የማስከበር ኃላፊነት፤
ተቃውሞ:- በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች፥ የኢንተርኔት አምደኞች፥ የፖለቲካ መሪዎኞችና ሌሎች ዜጎች ጉዳይና የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ዘገባዎች፤
በኢትዮጵያ ለኢቦላ የተለየ ሆስፒታል ተዘጋጅቷል
ኬንያ ተከታይዋ የኢቦላ ሥርጭት የሥጋት ቀበሌ ነች
ኢቦላን ለመከላከል የሰለጠኑ ባለሙያዎች ከዛሬ ማክሰኞ፤ ነኀሴ 6/2006 ዓ.ም ጀምሮ ቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ ተመድበው ፍተሻ እያካሄዱ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ