“በፍርድ ቤት ‘ጥፋተኛ’ ባልተባሉ ሰዎች ላይ በመገናኛ ብዙኃን የጥፋተኝነት አስተያየት መስጠት ተገቢ አይደለም” ሲሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ተቃውመዋል።
እስከፊታችን ዓርብ በሚዘልቀው የሜልቦርኑ ጉባዔ ላይ “Living in the Shadow” – (ተደብቆ መኖር) በሚል ርዕስ በአሜሪካ ድምፅ - ቪኦኤ የተዘጋጀ ጥናታዊ ፊልም ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ ታይቷል፡፡
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ሰሞኑን ለሃገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ኢትዮጵያን ለማተራመስ ከኤርትራ ጀምሮ የተዘረጋ መረብ አለ” አሉ፡፡
ሃያኛው የዓለም የኤድስ ጉባዔ ትናንት፣ ዕሁድ - ሐምሌ 13/2006 ዓ.ም ሲከፈት ግዙፍ የተባሉ ግቦችን አስቀምጧል፡፡
ለሦስት ወራት ያህል ክስ ሳይመሠረትባቸው ታስረው በቆዩት ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት ፀሃፊዎች፤ እንዲሁም በአንድ ሌላ ተጠርጣሪ ላይ አቃቢ-ህግ ዛሬ የአሸባሪነት ክሥ ከፈተ።
የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ኢዴፓ ለነገ፣ ቅዳሜ፤ ሐምሌ 12/2006 ዓ.ም በመብራት ኃይል አዳራሽ ለማካሄድ ጠርቶት የነበረውን ሕዝባዊ ስብሰባ መሠረዙን አርብ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የመን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሣልፋ የሰጠቻቸው የግንቦት ሰባት የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ የአንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ፉሮ ከኢትዮጵያ በአንድ ቀን ውስጥ እንዲወጡ መደረጉት ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ትልቁ የተቃዋሚዎች ጥምረት የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና ባለፈው ሣምንት መጨረሻ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ በሚገኘው ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ በሚባለው ተቋም ውስጥ ለተሰበሰቡ ታዳሚዎች ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡
የእንግሊዝ የባሕር ማዶ ትብብር ኤጀንሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ሲሰጥ ከራሱ የሰብዓዊ መብቶች ፖሊሲዎች ጋር በተጣጣመ መልክ መሆንና አለመሆኑ እንዲፈተሽ አንድ የእንግሊዝ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዋች አድንቋል፡፡
ተቋርጦ የቆየውን የኅዳሴ ግድብ ግንባታ የሦስትዮሽ ውይይት እንደገና ለመጀመር ግብፅ መጠየቋን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል፡፡
ፖሊስ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬአቸዋለሁ ያላቸውን ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት አምደኞች በየቀጠሯቸው ዕለት ፍርድ ቤት ሳያቀርባቸው ቀርቷል፡፡
ፖሊስ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬአቸዋለሁ ብሎ ከያዛቸው ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት አምደኞች መካከል ስድስቱ ትናንት ቅዳሜ፤ ሐምሌ 5/2006 ዓ.ም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡
ጎ............ል! ጀርመን 1 አርጀንቲና 0 - ሃያኛው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ግጥሚያ ተጠናቀቀ፡፡ ጀርመን አርጀንቲናን በፍፃሜ ግጥሚያ ለሁለተኛ ጊዜ ድል ነሣች፡፡
የግንቦት ሰባት የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የመን ላይ ተይዞ ለኢትዮጵያ መሰጠት በስፋት እያነጋገረ ነው፡፡
የተቃዋሚዎቹ መሪዎች ዛሬም ፍርድ ቤት አልቀረቡም፡፡
በኢትዮጵያ መንግሥት የተያዙት ወንድማቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕ ያገኛሉ ብለው እንደማያምኑ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ወንድም አቶ ብዙነህ ፅጌ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ፖሊስ ሌሎች ተጨማሪ ሰዎችን ትናንት መያዙ ተሰምቷል፡፡
ባለቤታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕ ያገኛሉ ብለው እንደማያምኑ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ባለቤት ወ/ሮ የምሥራች ኃይለማርያም ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ