የኦሮሚያ የሰሞኑ ሁኔታ ያለፈው ሥርዓት ናፋቂዎችና ጠባቦች የፈጠሩት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ መግለጫ ሰጡ፡፡
በኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ፤ የግብፅ ዕጩ ፕሬዚዳንት አብደል-ፋታህ ኤል-ሲሲ በቅርቡ ሲቢሲ ከሚባለው ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ውይይት አባይ ወንዝን በሚመለከት በሰነዘሩት ሃሣብ ላይ ለቪኦኤ የሰጡት ቃለምልልስ ሙሉ ቃል፡፡
ኢትዮጵያ ያሉትን የማየው በጥንቃቄ ነው፤ ለማንኛውም በፀጋ እንቀበላለን ትላለች፡፡
ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ ሰሞኑን ኦሮሚያ ውስጥ ሕይወት መጥፋቱን በመቃወም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ሰልፈኞች ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደጅ ላይ ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡
ላለፉት 13 ቀናት በማእከላዊ የወንጀል ምርመራ ጣቢያ ያለምንም ግንኙነት ታስረው ከቆዩት ጋዜጠኞችና የዞን 9 ጦማር ጸሃፊዎች መካከል ስድስቱ ታሣሪዎች ዛሬ፤ ረቡዕ፣ ሚያዝያ 29/2014 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ዩናይትድ ስቴትስ በደቡብ ሱዳን ውዝግብ ውስጥ ባሉ በሁለቱም ወገኖች ላይ የመጀመርያውን ማዕቀብ ጣለች።
የኦሮሚያ ተማሪዎች እያሰሙ ስላሉት ተቃውሞና በፀጥታ ኃይሎች ስለተወሰዱ እርምጃዎች የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ “ተቃውሞ ያሰሙ አንዳንድ የኦሮሞ ተማሪዎች በመንግሥት ኃይሎች መገደላቸው ስህተት ነው” አሉ።
ዜጎች ሃሣባቸውን የመግለፅ መብት ሲኖራቸው ሃገሮች የበለጠ ጠንካራ ይሆናሉ ሲሉ የዩናይትድ ስቴስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ አስታወቁ፡፡
የኦሮሚያ ሰልፎች የዛሬ ውሎ
በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞችን በዋና ከተማይቱ ማስተር ፕላን ውስጥ አካትቶ ለማልማት በሚል የተያዘውን ዕቅድ ከተቃወሙ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በተነሣ ግጭት በሰው ይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የመንግሥት ኮመዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡
የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች የግንባር ለግንባር ንግግር ዛሬ ጀምረዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በደቡብ ሱዳንና በማዕከላዊ አፍሪቃ ሬፐብሊክ ያለው አመፅ በሚቆምበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ የአፍሪቃ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ