በሕገወጥ መንገድ ተታልለው ከሃገር ከወጡ በኋላ በታንዛኒያ እሥር ቤቶች ውስጥ ቆይተው እንደነበር የገለፃቸውን 435 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ወደ ሃገር እየመለሰ እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል፡፡
አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። ሉሲ ወይም ድንቅነሽ ከትገኘት አርባ አመት ሞላት፣ ዴንማርክ ለኤርትራውያን የጅምላ ጥገኝነት እንደማትሰጥ አስታወቀች፣ ሲራልዮን ውስጥ የኢቦላ መከላከያ ልብስ እጥረት ተፈጠረ የሚሉትን ርእሶች ነው ዛሬ የምንመለከተው።
የ United States ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ባለፈው ሐሙስ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ የመኖርያ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ተወላጆችን ህይወት ሊለውጥ የሚችል የ United States ን የኢሚግሬሽን ፖሊሲን የሚቀይር ውሳኔ እንደሚወስዱ ማስታወቃቸው ይታወሳል። አቶ ተመስገን ተካ የኢሞግረሽን ህግ ባለሙያ ያብራራስሉ።
ማእከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ ውስጥ ዳግም በተቀሰቀሰው ግጭት ባለፈው አንድ አመት ተመንፈቅ ጊዜ ውስጥ ብቻ በ 10 ሺህ የሚገመቱ ሕጻናት በታጣቂ ቡድኖች ለውትድርና ተመልምለዋል።
የእግርኳስ ኮከብ ተጫዋቾች የኢቦላን ቫይረስ ስርጭት ለመግታት የሚካሄደውን አለምአቀፍ ዘመቻ ተቀላቀሉ።
G20 በመባል የሚታወቁት የአለም ከበርቴ ሀገሮች መሪዎች በሳምንቱ ማብቂያ ከህዳር 6 እስከ 7 በ Brisbane ተገናኝተው በምጣኔ ሃብትና ልማት እድገት ላይ ለመነጋገር እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት፥ አፍሪካ ከዚህ ጉባኤ ተጠቃሚ ትሆናለች ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል።
ሱማልያ ውስጥ እንደገና የተፈጠረው የፖለቲካ ውጥረት የሃገሪቱን የወደፊት ጉዞ ሊገታ ወይም አሁን ከደረሰችበት የመረጋጋት ጎዳና ሊያፈናቅላት እንደሚችል ተሰግቷል።
የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።
የኢትዮጵያ አትሌቶች በተለያዩ አለምአቀፍ የማራቶን ሩጫ ውድድሮች ድል ተቀዳጅተዋል። ፍቃዱ ግርማና ሙሉሀብት ጸጋ በቤይሩት፥ ሹሜ ሀይሉ በፈረንሳይ አሸንፈዋል። ጊዜአቸውም የፍቃዱ 2 - 12 - 26 እና 2- 29 - 15 ተመዝግቧል። በፈረንሳዩ የአልፕስ ማራቶን ደግሞ የወንዶቹን ሹሜ ሃይሉ በአንደኝነት አጠናቋል።
አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። አንድ ስደስተኛውን የኢትዮጵያ መሬት የማልማት እቅድ ወጣና ብሪትናያ ለኢትዮጵያ ፖሊስ ከምትሰጠው እርዳታ ቀነሰች የሚሉ ይገኙባቸዋል።
ትውልደ-ኢትዮጵያው ፕሮፌሰር መሐመድ ጣሂሮ ለዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልነት ቴክሳስ ግዛት ላይ እየተወዳደሩ ናቸው፡፡
“በዚህ ኃላፊነት ላይ ከተቀመጥኩ ጊዜ ጀምሮ በየወሩ ማለት በሚቻል ፍጥነት ወደ አዲስ አበባ እመላለሳለሁ፡፡ ይህ ደግሞ ሁለታችንም ከፕሬዚዳንት አብዱል-ፈታህ ኤል-ሲሲና ከወንድማቸው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በየጊዜው መገናኘታችንን ጠንክረን እንድንቀጥል፣ የግንኙነታችንን መንፈስም ይዘን እንድንጓዝ በተቀበልነው መመሪያ መሠረት ነው፡፡” - ሳምሃ ሹክሪ - የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ሳምንቱን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። ኤርትራ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ድምጽ ተሰማና ኢቦላን በሚመለከት ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ ሊኖር እንሚችል ተገለጸ የሚሉ ዘገቦች ይገኙባቸዋል።፣
“አንድ ሰው በፖሊስም ሆነ በሌላ የሕግ አስፈጻሚ አካል ለሚቀርብለት ጥያቄ፤ ካልፈቀደ በስተቀር መልስ ያለመስጠት መብት አለው።” አቶ ደረጀ ሰምሴ ቡልቶ፤ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሞያ።
በአሜሪካ እና ኢትዮዽያ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግኑኝነት እንደሚያስደስታተው፥ በኢትዮዽያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ፐትርሽያ ሃስላክ ገለፁ።
ተጨማሪ ይጫኑ