በአሸባሪነትና በአገር ክህደት ተከስሰው የተፈረደባቸው የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት አቶ አንዱዓለም አራጌና አቶ ናትናኤል መኮንን እንዲሁም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች አምስት ተከሣሾች የይግባኝ ጥያቄ ዛሬም ለሌላ ጊዜ ተቀጠረ።
ዋሺንግተን ዲ.ሲ. አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን-አሜሪካዊያ ዛሬ ሰኞ በዋይት ሀውስ ቤተመንግሥት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ በአማራው ተወላጆች ላይ «ያካሂዳል» ያሉትን ማፈናቀልና ማዋከብ ተቃውመዋል።
በየሣምንቱ ዓርብ ስትወጣ የቆየችው “ልዕልና” የተሰኘችው ጋዜጣ አሣታሚ የኢምፓየር አሣታሚ ድርጅት የንግድ ሥራ ፈቃድ ተሠረዘ።
የለንደን ርዕሰ-አድባራት ደብረ-ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ከተመሠረተች አርባ ዓመት ሊሞላ ነው።
ከነቀምቴ ሆስፒታል አራት ሃኪሞች ታስረው በነቀምቴው የምሥራቅ ወለጋ ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
የሚድሮክ ኢትዮጵያና ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ባለሃብት ሼህ መሃመድ ሁሴን አል አሙዲ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሦስት የመንግሥት የእርሻ ድርጅቶችን ለመረከብ ዛሬ ተፈራርመዋል።
ከዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም ጋር የተደረገ ውይይት
በምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚኖሩ የአማራ ብሄር አባል የሆኑ አርሦ አደሮች «ለዓመታት ከኖርንበት እየተፈናቀልን ነው፤ መድረሻ ግን የለንም» ሲሉ አቤቱታ እያሰሙ ነው፡፡
ሶማሊያ ውስጥ ዛሬ በሚስተዋሉ ቁልፍ እና አሳሳቢ በሆኑ የፍትሕ እና የሕግ የበላይነት ችግሮች ላይ ይመክራል የተባለ የፍትሕ ጉባዔ ዛሬ ሞቃዲሾ ላይ ተጀምሯል፡፡
በምሥራቅ እና በመካከለኛው ምሥራቅ አፍሪካ ሕፃናትን በብዙ የሚጎዳ አሽመድምድ የአካልና የጤና ችግር ትኩረት፣ ከአመጋገብና ምግብ ዓይነቶች ጋር የተያያዘ ጥንቃቄ፣ መከላከል እና እንክብካቤ ያስፈልገዋል፡፡
ጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኸኝ ከ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ በኋላ “በመንግሥት ኃይሎች ደረሰብኝ” በሚለው እሥራት፣ ወከባ፣ ድብደባና በቅልብ ውሻ የመነከስ ጥቃት በታኅሣስ 1998 ዓ.ም ለመሰደድ በቅቷል፡፡
ICG ማለት አለም አቀፍ የቀውስ አስወጋጅ ቡድን ያወጣው ዘገባ በኤርትራ እየጎላ የሄደው ያለመረጋጋት ሁኔታ ሀገሪቱን ትርምስ ውስጥ ሊከት ይችላል ይላል።
የፀረ-አፓርታይድ የነፃነት ትግል ፋና፣ የመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ፕሬዚዳንትና የሰላም የኖቤል ተሸላሚው ኔልሰን ማንዴላ ትናንት ዕኩለ ሌሊት ላይ ወደሆስፒታል ተወስደው ሕክምና ተደርጎላቸዋል፡፡
በሽብርተኝነትና በሃገር ክህደት ወንጀል ተከስሰው እስከዕድሜ ልክ እሥራት ፍርድ የተላለፈባቸው የእነአቶ አንዱዓለም አራጌ ጉዳይ ትናንት ለአራተኛ ጊዜ ተቀጥሯል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ “አዳዲስ የፖለቲካ ሰዎች ወጥተዋል” ሲል አሶሴትድ ፕሬስ የሚባለው የዜና ወኪል ባሕርዳር ውስጥ ስለተካሄደው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር - ኢሕአዴግ ዘጠነኛ ጉባዔ ፅፏል፡፡
የድምፅ ብክለት የአየር ብክለትን ተከትሎ ያለ በዓለም ሁለተኛው ግዙፍ የአካባቢያችን ብክለት ዓይነት ነው፡፡
“ታላቁ መሪ” እየተባሉ የተወደሱት መለስ ዜናዊ ካረፉ በኋላ ኢሕአዴግ ያደረገውን የአመራር ለውጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝን ሊቀመንበሩ አድርጎ በመምረጥ አጠናቅቋል፡፡
ለአራት ቀናት በባህርዳር ከተማ የተካሄደው የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ዘጠነኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ዛሬ - ማክሰኞ ማምሻውን ተጠናቅቋል።
“በአገሪቱ እየተባባሱ መጡ - ባላቸው ችግሮች ምክኒያት - ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገዶች ላይ ናት” ሲል የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አሳሰበ፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት - ኤፍኤኦ በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ዘመናዊና ምርታማ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ይገኛል፡፡
በአፍሪካ ጉብኝት ላይ የሚገኙት የቻይናው ፕሬዚዳንት ቺ ሺንፒንግ ዛሬ ከደቡብ አፍሪካው አቻቸው ጄከብ ዙማ ጋር ፕሪቶሪያ ውስጥ ተገናኝተው በርካታ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡
ኢሕአዴግ በያዘው ዕቅድ መሠረት በ2007 ዓ.ም መጨረሻ ወይም በ2008 ዓ.ም መጀመሪያ ነባር ታጋዮች የሚባሉት ሁሉ በሌሎች እንደሚተኩ ይጠበቃል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ