የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዐርብ፤ ሚያዝያ 4/2005 ዓ.ም በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሠልፎችን አካሂደዋል፡፡
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ - ሲአን “በአባሎቼ ላይ የሚፈፀመው በደል ከ2005ቱ ምርጫ እራሴን እንዳገልል አስገድዶኛል” ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ የአካባቢና የከተማ ምክር ቤት ምርጫ የፊታችን ዕሁድ፤ ሚያዝያ ስድስትና በሣምንቱ ሚያዝያ አሥራ ሦስት 2005 ዓ.ም ይካሄዳል።
ከቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች “እንዲመለሱ ጥሪ ቀረበ” ተባለ።
በአሸባሪነትና በአገር ክህደት ተከስሰው የተፈረደባቸው የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት አቶ አንዱዓለም አራጌና አቶ ናትናኤል መኮንን እንዲሁም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች አምስት ተከሣሾች የይግባኝ ጥያቄ ዛሬም ለሌላ ጊዜ ተቀጠረ።
ዋሺንግተን ዲ.ሲ. አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን-አሜሪካዊያ ዛሬ ሰኞ በዋይት ሀውስ ቤተመንግሥት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ በአማራው ተወላጆች ላይ «ያካሂዳል» ያሉትን ማፈናቀልና ማዋከብ ተቃውመዋል።
በየሣምንቱ ዓርብ ስትወጣ የቆየችው “ልዕልና” የተሰኘችው ጋዜጣ አሣታሚ የኢምፓየር አሣታሚ ድርጅት የንግድ ሥራ ፈቃድ ተሠረዘ።
የለንደን ርዕሰ-አድባራት ደብረ-ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ከተመሠረተች አርባ ዓመት ሊሞላ ነው።
ከነቀምቴ ሆስፒታል አራት ሃኪሞች ታስረው በነቀምቴው የምሥራቅ ወለጋ ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
የሚድሮክ ኢትዮጵያና ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ባለሃብት ሼህ መሃመድ ሁሴን አል አሙዲ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሦስት የመንግሥት የእርሻ ድርጅቶችን ለመረከብ ዛሬ ተፈራርመዋል።
ከዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም ጋር የተደረገ ውይይት
በምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚኖሩ የአማራ ብሄር አባል የሆኑ አርሦ አደሮች «ለዓመታት ከኖርንበት እየተፈናቀልን ነው፤ መድረሻ ግን የለንም» ሲሉ አቤቱታ እያሰሙ ነው፡፡
ሶማሊያ ውስጥ ዛሬ በሚስተዋሉ ቁልፍ እና አሳሳቢ በሆኑ የፍትሕ እና የሕግ የበላይነት ችግሮች ላይ ይመክራል የተባለ የፍትሕ ጉባዔ ዛሬ ሞቃዲሾ ላይ ተጀምሯል፡፡
በምሥራቅ እና በመካከለኛው ምሥራቅ አፍሪካ ሕፃናትን በብዙ የሚጎዳ አሽመድምድ የአካልና የጤና ችግር ትኩረት፣ ከአመጋገብና ምግብ ዓይነቶች ጋር የተያያዘ ጥንቃቄ፣ መከላከል እና እንክብካቤ ያስፈልገዋል፡፡
ጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኸኝ ከ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ በኋላ “በመንግሥት ኃይሎች ደረሰብኝ” በሚለው እሥራት፣ ወከባ፣ ድብደባና በቅልብ ውሻ የመነከስ ጥቃት በታኅሣስ 1998 ዓ.ም ለመሰደድ በቅቷል፡፡
ICG ማለት አለም አቀፍ የቀውስ አስወጋጅ ቡድን ያወጣው ዘገባ በኤርትራ እየጎላ የሄደው ያለመረጋጋት ሁኔታ ሀገሪቱን ትርምስ ውስጥ ሊከት ይችላል ይላል።
የፀረ-አፓርታይድ የነፃነት ትግል ፋና፣ የመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ፕሬዚዳንትና የሰላም የኖቤል ተሸላሚው ኔልሰን ማንዴላ ትናንት ዕኩለ ሌሊት ላይ ወደሆስፒታል ተወስደው ሕክምና ተደርጎላቸዋል፡፡
በሽብርተኝነትና በሃገር ክህደት ወንጀል ተከስሰው እስከዕድሜ ልክ እሥራት ፍርድ የተላለፈባቸው የእነአቶ አንዱዓለም አራጌ ጉዳይ ትናንት ለአራተኛ ጊዜ ተቀጥሯል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ