ከካንሰር አጠቃላይ የሞት መጠን አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ለመከላከልና ለማስቀረት የሚቻል መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡
ቤዴኩዊላይን በሙከራ ላይ የሚገኝ ባለፉት ሃምሣ ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ አዲስ መድኃኒት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለሕክምና አገልግሎት እንዲውል የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ይሁንታ ቸሮታል፡፡
«ከአርባ ስድስት ዓመታት በፊት የአሜሪካ የሰላም ጓድ ሆኜ ወደ ኢትዮጵያ በተጓዝኩበት ጊዜ በኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ስማረክ የተዋወቅኩት ተሥፋዬ ለማ ለኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ከፍተኛ አስተዋጽ ያደረገ ሰው ነው።» ቻርልስ ሳተን።
በሲናይ በረሀ በስደተኞች ላይ የሚፈጸመው ወንጀል እንዲቆም የኤርትራ ህዝባዊ ዲሞክራስያዊ ፓርቲ ለግብጽ ፕረዚዳንት ደብዳቤ ላከ።
እስራኤል ከኢትዮጵያውያን አይሁዶች ጋር በተያያዘ አዲስ የወሊድ ቁጥጥር መመርያ አውጣች
ኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ሕጓን በጋዜጠኞች ላይ አስከፊ በሆነ መንገድ ስለምትጠቀም የጋዜጠኞች አያያዝ ደረጃዋ ቀደም ሲል ከነበረችበት በአሥር መውረዱን ዓለምአቀፉ ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የሚባለው ድርጅት አስታወቀ፡፡
ኢህአደግ በስልጣን ላይ የሚቆይ ከሆን የሊቀምንበርነቱ ስልጣን በአራቱ ድርጅቶች መካከል መዘዋወር አለበት ይላሉ ዶክተር አሰፋ ፍሰሀ
አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ኦልባና ሌሊሣና ሌሎችም ሰባት ሰዎች እንዲፈቱ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ጫና እንዲያሣድር በመጠየቅ የኦሮሞ ብሔር አባላት የሆኑ ሰልፈኞች ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደጅ ላይ ተገኝተው ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡
የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርት ተቀድዶ መጣል ያለበት ሠነድ ነው ሲሉ በአፍሪካ ሕብረትና በመንግሥታቱ ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን የኤርትራ አምባሣደር ግርማ አስመሮም ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡
“በሂደቱ፥ መጀመሪያ ካገኘናቸው ልጆች ጋር ቅርርብ ፈጥረን ስለነበር፥ ሁኔታው ሲሰናከል በእጅጉ ብናዝንም፤ የተለየ አቀራረብ መከተል መረጥን እንጂ፤ ተስፋ አልቆረጥንም።” አቶ ሰለሞን ለማ።
ኤርትራ ውስጥ “በማዕድን ልማት ላይ የግዳጅ ሥራ ይሠማራል፤ በሃገሪቱ ውስጥ የከፋ አፈና አለ” ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ባለፈው ሣምንት ያወጣውን ክስ ኤርትራ አስተባብላለች፡፡
ወደ አንድ መቶ የሚሆኑ የኤርትራ ወታደሮች ሰሞኑን ባካሄዱት አመፅ የማስታወቂያ ሚኒስቴሩን ይዘውት ውለዋል፡፡ ምሽት ላይ ለቅቀው ወጥተዋል፡፡ ነገሩ ምንድነው? ሰዎቹስ እንዴት ናቸው? ወደፊትስ?
ያመፁ የኤርትራ ወታደሮች የማስታወቂያ ሚኒስቴሩን ለአንድ ቀን ከተቆጣጠሩ በኋላ ለቅቀው መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለሁለተኛ የአስተዳደር ዘመናቸው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል፡፡
በጃን ሜዳ ብፁዕ አቡነ ናትናዔል፤ በሎስ አንጀለስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ቡራኬ ሰጡ፡፡
“ድምፃችን ይሰማ” በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት ለመንግሥት ጥያቄ ያቀረቡበትን አንደኛ ዓመት በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሰሞኑን አስበዋል፡፡
በሶማሊ ክልል በርካታ የሰብአዊ መብት ረገጣዎችና ግድያዎች ፈጽመዋል በሚል የሚከሰሱትን ልዩ የጸጥታ ሀይሎችን ለማሰልጠን ብሪታንያ በሚልዮኖች የሚቆጠር ፓውንድ እንደምታወጣ ተገለጸ
በኢትዮጵያ ዘንድሮ ያካባቢና የከተማ ምክር ቤቶች ምርጫ በቅርቡ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
በፈጣን ሁኔታ እያበበ ባለው የኤርትራ የማዕድን ዘርፍ ላይ መዋዕለ ነዋይ የሚያፈስሱ ዓለምአቀፍ ኩባንያዎች የጥንቃቄ እርምጃ ካልወሰዱ በሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ውስጥ ተሣታፊ የመሆን አደጋ እንደሚጠብቃቸው ሂዩማን ራይትስ ዋች አስታውቋል፡፡ በማዕድን ልማት ሥራው ላይ የተሠማራው የውጭ ኩባንያ “የግዳጅ ሥራ አይፈቀድም” ብሏል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ