ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከኔክቲከት ክፍለሃገር ውስጥ ሰሞኑን በአንድ የአንደኛ ትምህርት ቤት ሕፃናትና በመምህራኑ ላይ በአንድ ግለሰብ የተፈፀመው ግድያ ብዙ ንግግሮችንና ውይይቶችን እያጫረ ነው፡፡
የአውሮፓ ፓርላማ 16 አባላት በጋዜጠኛና የኢንተርኔት አምደኛው እስክንድር ነጋ የተራዘመ እሥር የተሰማቸውን ብርቱ ሥጋት በመግለፅ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ደብዳቤ ፅፈዋል፡፡
እስራኤል ያሉት ኢትዮጵያውያት ካለፍላጎታቸው በሚወጉት የወሊድ መቆጣጠርያ መርፌ ምክንያት የሚወልዷቸው ልጆች መጠን በ 50 ከመቶ እንደቀነሰ ተዘግቧል።
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፤ በቤንች ማጂ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ የሚኖሩ፤ ከዓመታት በፊት ከአማራ ክልል የሄዱ ሠፋሪ አርሦ አደሮች በአካባቢው ባለሥልጣናት ተገድደው ቀያቸውን ልንዲለቅቁ እየተደረጉ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ካስፈለገ አስመራ ድረስ ሄደው ከፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቁ ጋር የሰላም ድረድር ለማደረግ ዝግጁ ነኝ ማለታቸውን የዐል ጂዚራ የዜና አውታር ጠቁሟል
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአጋሮች ጉባዔ ለ18ኛ ጊዜ ዶሃ ላይ ተቀምጧል፡፡
የቪኦኤ ውይይት ከፕሬዚዳንት ግርማ ጋር
ዓለም አቀፉ የጸረ-ሙስና የአገራትን የመልካም አስተዳደር ይዞታ የሚከታተለው ተቋም Transparency International ዓመታዊውን የዓለም አገሮች የሙስና ደረጃና ሪፖርት ይፋ አደረገ።
ቪኦኤ - ከሬኔ ለፎር ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ የመጨረሻ ክፍል
የዘንድሮው የዓለም የኤድስ ቀን የታሰበውና ፀረ-ኤድስ እንቅስቃሴዎቹም የሚካሄዱት “ዜሮ ማግለል፣ ዜሮ በኤችአይቪ መያዝ፣ ዜሮ የኤድስ ሞት” በሚል መርኅ ነው፡፡
ከዋና ዋና የአፍሪቃ ቀንድ አጥኚዎችና ታዛቢዎች መካከል አንዱ የሆኑት Rene Lefort የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ “መለስ ከመቃብራቸው እየገዙ ነው። ግን ይህ እስከመቼ ይዘልቅ ይሆን?” የሚል ጽሁፍ አውጥተዋል።
ሰላሣ ሦስት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዚህ ዓመት የሚደረገው የአካባቢ ምርጫና ወደፊትም የሚካሄዱት ምርጫዎች እንደ 2002 ዓመተ ምኅረቱ ከሆኑ ለአገሪቱ ህልውናም አስጊ ናቸው አሉ።
ጂማ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ትናንት ተፈጥሯል በተባለ ችግር ከፖሊስ ጋር ግጭት እንደነበረ አንዳንድ ተማሪዎች ሲገልፁ የተፈጠረ ግጭትም ይሁን የተጎዳ ተማሪ አለመኖሩን የተማሪዎቹ ኅብረት ፕሬዚዳንት እና የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ለቪኦኤ ገለፁ፡፡
“ይቻላል” ይላሉ በትግሉ መስክ በግንባር የተሠማሩት ተዋንያን፡፡ ያንን እጅግ ከባድ የሚመስል ግብ ለመድረስ የቆረጡም ይመስላሉ፡፡
የዘንድሮው የዓለም የኤድስ ቀን እየታሰበ ያለው “ዜሮ ማግለል፣ ዜሮ በኤችአይቪ መያዝ፣ ዜሮ የኤድስ ሞት” በሚል መርኅ ነው፡፡
አዲሱ ሹመት በኢሕአዴግ የመተካካት መርኅ መሠረት የተካሄደና ወደ መንግሥቱ አመራር “አዲስ ደም” ያስገባ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ አስታውቀዋል፡፡
በአዲሱ አደረጃጀት መሠረት ካቢኔው በጠቅላይ ሚኒስትርና በሦስት ምክትሎቹ ይመራል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ