የይስሙላ ምርጫ ያካሄደችው ኢትዮጵያ፣ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት የጉብኝት መዝገብ ላይ መሆን እንደማትችል የስትራተጂካዊ ዓለማቀፍ ጥናቶች ማዕከል የአፍሪቃ ክፍል ድሬክተር ጄኒፈር ኩክ ገለፁ
የእግር ኳስ ሜዳዎች አሸብርቀዋል፣ መንገዶች ተፀድተዋል፣ ዘፈኖች ተቀድተው አልቀዋል፣ የደቡብ አፍሪካ ነዋሪዎችም በብዙ ቀለማት ያሸበረቁ ልብሶቻቸውን ለብሰው ወደ መንገድ ወጥተዋል።
ዋና ከተማዋ ጆሀንስበርግ፥ እንግዶቿን በሙዚቃና ልዩ ልዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች እያዝናናች ነው።
የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዘዳንት ጄኰብ ዙማ በሳምንቱ ማብቂያ ላይ በሰጡት ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ፥ አገራቸው የዓለሙን የእግር ኳስ ድግስ በአስተማማኝና ባማረ ሁኔታ ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቋን አስታውቀዋል።
«ነፃና ገለልተኛ የሆኑ የአገር ውስጥና የውጭ አገርና ታዛቢዎች፤ በተገኙበት ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ እንጠይቃለን፤» - መድረክ
ለእሁዱ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመላው ኢትዮጵያ የመጨረሻ ዙር የምረጡኝ ዘመቻቸውን አካሄዱ። እጩዎች በስብሰባዎች፣ ፖስተር በመለጠፍና ሙዚቃ በማሰማት የምረጡኝ መልእቶቻቸውን አስተላልፈዋል።
የዴሞክራሲ ጉዳይ ፈተና ከሆነባት ኢትዮጵያ ጋር ዩናይትድ ስቴትስ አስቸጋሪ፣ ግን ደግሞ ለእርሷ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ግንኙነት ውስጥ መግባት መገደዷን አሜሪካዊያን የአፍሪካ ጠቢባን እየተናገሩ ነው፡፡