በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

አቶ ወንድሙ ኢብሳ

በርካታ የፖለቲካ እና ህሊና እስረኞች ይቀርቡባቸው በነበሩባቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ 4ተኛ እና 19ኛ ምድብ ችሎቶች ቤተኛ የሆኑ አዛውንት አሉ።

ሰልባጅ ክራባት አንገታቸው ላይ ያሰሩ(በእሳቸው አነጋገር)፣ ጠብደል መዝገቦች ከእጃቸው የማይጠፉት እኒህ ሰው ወንድሙ ኢብሳ ይባላሉ።

ስራቸው ጥብቅና ነው።ያኔ ቀን ከቀን ተጠርጣሪዎች እና ፍርደኞች የልደታን ቅጽር ሲያዘወትሩ ፣ጠበቃ ይቀጥሩበት ገንዘብ የሌላቸው እስረኞች በዐይናቸው ይፈልጓቸዋል ፤ እሳቸውም ገንዘብ ያላቸውም ብለው መሸሽ የሚያውቁ አይመስሉም ።

ከ600 በላይ ለሆኑ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች “ከለውጡ በፊት” ጥብቅና ቆመውላቸዋል።ይኼን ማድረጋቸው ግን ህይወታቸውን ለአደጋ ማጋለጡ፣ የእንግልት መምዘዙ አልቀረም።

ሙሉ ጥንቅሩን ያዳምጡ።

ከ600 በላይ ለሆኑ የፖለቲካ እና ህሊና እስረኞች ጥብቅና የቆሙት ወንድሙ ኢብሳ ማን ናቸው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:23 0:00


ፎቶ ፋይል፦ የጎንደር ጥምቀት

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በተሳተፉበት የጎንደር የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ የሽብር ጥቃት ሊያደርሱ የሞከሩት በህወሓት የተላኩ ግለሰቦች ናቸው፤ ሲሉ አንድ ከፍተኛ የአማራ ክልል የፀጥታ ባለሥልጣን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ጌታቸው ብርሌ ለአሜሪካ ድምፅ እንዳብራሩት ሰለ ተጠርጣሪዎቹ ማንነት የተሟላ መረጃ አለ በቅርቡም ይፋ ይደረጋል፡፡ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኤጀንሲ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ጥቃት ሊፈፀሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የላካቸው አካል ማንነትን ይፋ እንደሚደረግ ጠቁሞ ነበር።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በጎንደር የጥምቀት በዓል የሽብር ጥቃት ሊያደርሱ የሞከሩ ግለሰቦች ማንነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:06 0:00


ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG