በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ዓርብ 19 ሚያዚያ 2019

Calendar
ጥር የካቲት መጋቢት ሚያዚያ ግንቦት ሰኔ ሐምሌ ነሐሴ መስከረም ጥቅምት ህዳር ታህሳስ
ሚያዚያ 2019
ሰኞ ማክሰ ረቡዕ ሐሙስ ዓርብ ቅዳሜ እሑድ
1 2 3 4 5 6 7
8 9 10 11 12 13 14
15 16 17 18 19 20 21
22 23 24 25 26 27 28
29 30 1 2 3 4 5
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሶማሌ ክልል ተፈናቃዮች ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ለገሰ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሶማሌ ክልል ተፈናቃዮች ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ለገሰ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሶማሌ ክልል መንግስት ተፈናቃዮች 35 ሚሊዮን 167ሺ ብር ለገሰ፡፡ ትላንት በጂጂጋ ከተማ የፕሬዚደንት ፅ/ቤት አዳራሽ በተካሄደው ስነስርዓት ላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ባጫ ጊና ለሶማሌ ክልል ርእሰመስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ አስረክበዋል፡፡

በወቅቱ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ ክልላቸው ሩብ ሚሊዮን ገደማ ተፈናቃዮችን ወደቀያቸው መመለሱን ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተፈናቃዮች ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ለገሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:28 0:00

የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን እና የሩሲያ አቻቸው ቭላዲሚር ፑቲን

የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን እና የሩሲያ አቻቸው ቭላዲሚር ፑቲን በያዝነው የአውሮፓ ወር መጨረሻ ሞስኮ ላይ ለመገናኘት አቅደዋል።

የሁለቱ መሪዎች ስብሰባ ዕቅድ ከክሬምሊን የወጣው ፒዮንግያንግ እጅግ ኃይለኛ የተባለ አረር አዘል ሥልታዊ የጦር መሣሪያ መሞከሯን ካሳወቀች በኋላ ነው።

ስለሁለቱ መሪዎች መነጋገሪያ ጉዳዮች ከሞስኮ የወጣ ዝርዝር ማብራሪያ ባይኖርም ስብሰባው ግን ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ሲታሰብሰበት የቆየ መሆኑን ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል።

ሰሜን ኮሪያን ኒኩሌር ትጥቋን ለማስፈታት በሚል በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና በኪም ጆንግ ኡን መካከል ሁለት ዙር ስብሰባ የተካሄደ ቢሆንም ጉዳዩ እስከ አሁን ያለመፍትኄ እንደተንጠለጠለ ነው።

ሁለቱም መሪዎች ለሦስተኛ ጊዜ የመገናኘት ሃሣብ አንፀባርቀዋል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG