በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ማክሰኞ 7 ጥር 2020

ምዕመናን ለኢትዮጵያ ሰላም እንዲተጉ የሃይማኖት አባቶች አሳሰቡ

ኢትዮጵያዊያን የክርስትና ዕምነት አማኞች የገና በዓልን ሲያከብሩ፣ ስለሀገሪቱ እና ህዝቦቿ ሰላም እንዲያስቡ እና እንዲተጉ የሃይማኖት አባቶች መልዕክት አስተላለፉ።

መቀመጫቸውን እዚህ ዩናይት ስቴትስ ውስጥ ያደረጉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን አባቶች የእየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት አድርገው መልዕክታቸውን አጋርተዋል።

ሀብታሙ ስዩም ይሄን የተመለከተ መሰናዶ አለው።

ምዕምናን ለኢትዮጵያ ሰላም እንዲተጉ የሃይማኖት አባቶች አሳሰቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:10 0:00


በዩናይትድ ስቴትስ የድሮን ጥቃት በተገደሉት የኢራኑ ወታደራዊ አዛዥ ቃሲም ሱሌይማኒ ዛሬ ማክሰኞ በተከናወነው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ቢያንስ አርባ የሚሆኑ ሰዎች ተረጋግጠው መሞታቸውን እና ሌሎች ከሁለት መቶ በላይ መጎዳታቸውን የኢራን መንግሥት የዜና ማሰራጫዎች ዘግበዋል።

በጄነራሉ የትውልድ ከተማ ኬርማን ውስጥ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከመፈጸሙ በፊት አክብሮታቸውን ለመግለጽ በብዙ አስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተው እንደነበር ታውቋል። ቀደም ብሎ ተመሳሳይ ሥነ ሥርዓቶች ቴህራን ኮም እና አልቫዝ ከተሞች ውስጥ ተካሂዶ ነበር። የዛሬውን አደጋ ተከትሎ የጄነራሉ ቀብር ለሌላ ጊዜ እንደተላልፈ ነው ዘገባዎቹ የጠቆሙት።

በዘንተኞች በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የበቀል ዕርምጃ መወሰድ አለበት፤ ሲሉ መፈክሮች አሰምተዋል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG