በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ሰኞ 6 ጥር 2020

ፎቶ ፋይል

ቡርኪና ፋሶ ላይ ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ250 በላይ የሚሆኑ ሰዎች እስላማዊ መንግሥት ነኝ በሚለው ጽንፈኛ ቡድን መገደላቸውን ሂዮመን ራይትስ ዋች የተባለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ዛሬ ባወጣው ዘገባ ገልጿል።

በምዕራብ አፍሪካቱ ሀገር ሰሜንና ምስራቅ ክፍል ጥቃቶች እየተበራከቱ መሆናቸውና ታጣቂዎች የሚቆጣጠርዋቸው ግዛቶች እየጨመሩ መሄዳቸዋን ሂዮመን ራይትስ ዋች አክሏል።

አጥቂዎቹ የሚገድልዋቸው ሰዎች ከመንግሥትና ከምዕራባውያን ጋር ግንኙነት አላቸው። ወይም ክርስትያኖች ናቸው በሚል መሆኑን እማኞች መናገራቸውን የሰብአዊው መብት ተሟጋቹ ቡድን ጠቅሷል።

አማፅያኑ አርሶ አደሮችን፣ አማንያንን፣ የማዕድን ሰራተኞችንና ነጋዴዎችን ሆን ብለው ዒላማ እንደሚያደርጉ የሂዮማን ራይትስ ዋች የምዕራብ አፍሪካ ጉዳይ ሥራ አስኪያጅ ኮሪን ዱፍካ ገልፀው፣ የጦርነት ወንጀል ነው ብለውታል።

አንሱር ዐል-ኢስላምን የመሳሰሉት ከዐል-ቓዒዳ ጋር ወይም እስላማዊ መንግስት ነኝ ከሚለው ቡድን ጋር የተሳሰሩ አማጽያን ካለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር አንስተው ቢያንስ 20 ጥቃቶች አካሄደዋል። በጥቃቶቹም ቢያስንስ 256 ስዎች ተገድለዋል ይላል የሂዮማን ራይትስ ዋች ዘገባ።

የአውስትራልያ ጠቅላይ ሚኒስትር ስካት ሞሪሰን

የአውስትራልያ ጠቅላይ ሚኒስትር ስካት ሞሪሰን በሀገሪቱ የተከሰተው አስከፊ የሰደድ እሳት ሰለባ የሆኑትን ሰዎች ለመርዳት “አስፋላጊውን ሁሉ” ለመክፈል ቃል ገብተዋል።

የሰደድ እሳቱ በሦስት ክፍላተ ሀገር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሄክታር ቦታዎችን አጋይቷል።

ሞሪሰን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የወደሙትን ከተሞችና መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት ተጨማሪ አንድ ነጥብ አራት ቢልዮን ዶላር መመደባቸውን ገልጸዋል። እንደ አስፈላጊነቱም ተጨማሪ ገንዘብ እንደሚመደብ መንግሥታቸው አስታውቋል።

ከተመደበው በላይ ካስፈለገም ይጨመራል ብለዋል ሞሪሰን።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG