በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ሐሙስ 2 ጥር 2020

ወ/ሮ አስቴር ይልማ በዩናይትድ ስቴትስ በተለያዩ ግዛቶች ፤ በተለይም በኒውዮርክ እና በኒውጀርሲ ግዛቶች የፍርድ ቤቶች ዋና አስተርጓሚ በመሆን ከ17 ዓመት በላይ አገልግላለች፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የአስተርጓሚዎች ማህበር ፣ የብሄራዊ የህግ አስተርጓሚዎች ማህበር እና የኒውዮርክ የአስተርጓሚዎች ክበብ አባል ናት፡፡

በስነ-ልቦና ጥናት (በሳይኮሎጂ) የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በቴሌቪዥን ትርኢት ዝግጅት አሶሺየት ዲግሪ እና በቤት ውስጥ የሚደርስ ጾታዊ ጥቃት ተጎጂዎችን የማማከር (አድቮከሲ) የምስክር ወረቀት አላት፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ ከሰላሳ ዓመት በላይ ከሱስ ጋር የተገናኙ ጥናቶችን አድርጋለች፡፡ የ‘ላም አለኝ’ አማርኛ ፊልም ተባባሪ አዘጋጅም ናት፡፡

ከአምስት ዓመት ወዲህ ጀምሮ የቤት ወስጥ ጾታዊ ጥቃት ተጎጂዎችን የማማከር አገልገሎት በመስጠት ላይ ትገኛለች፡፡

ወ/ሮ አስቴር ይልማ በዩናይትድ ስቴትስ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ዘንድ እየደረሱ ስላሉ የቤት ውስጥ ጾታዊ ጥቃቶችን በተመለከተ እንዲሁም በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ድምጿ ኤደን ገረመው ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርጋለች፡፡

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና የቤት ውስጥ ጾታዊ ጥቃቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:37 0:00

የእነ አሥር አለቃ መሣፍንት ዶሴ ተቀጠረ

ህገ መንግሥቱንና ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን፣ በኃይል ለማፍረስ በመሞከር ወንጀል ጠርጥሮ ፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ የመሰረተባቸውን የእነ አሥር አለቃ መሣፍንት ጥጋቡን የክስ መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ በአብዛኛው ሳይቀበለው ቀርቷል።

በቀድሞው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄነራል ሰዐረ መኮንን እና አብረዋቸው በነበሩት ሌ/ጄነራል ገዛዒ አበራ ላይ በተፈፀመው ግድያ ተጠርጥረው የተከሰሱትን አሥር አለቃ መሣፍንት ጥጋቡን የክስ መቃወሚያ ግን ዐቃቤ ህግ አሻሽሎ እንዲያቀርብ አዝዟል።

ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤት የተለያዩ አቤቱታዎችን ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ትዛዞችን ሰጥቶ ለጥር 8/2012 ዓም ቀጥሯል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የነአሥር አለቀ መሣፍንት ዶሴ ተቀጠረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:41 0:00


ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG