በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ዓርብ 10 ጥር 2020

ኅዳሴ ግድብ Nile Dam Negotiation

ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በኅዳሴ ግድብ ዙሪያ በአዲስ አበባ ያካሄዱት የሦስትዮሽ ውይይት የመጨረሻ መግባባት ላይ አልደረሰም።

የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ፣ እንደዚሁም የድርቅ አስተዳደር መርኅ፣ ያለስምምነት የቀጠሉ ጉዳዮች መሆናቸውን የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ኃይል ሚኒስትር ዶ/ር ኢኒጂነር በቀለ ለአሜሪካ ድምጽ አብራርተዋል።

ዩናይትድ ስቴትስና የዓለም ባንክ በውይይቶቹ በታዛቢነት እንዲሳተፉ መስማማት ጥቅምን አሳልፎ መስጠት እንደሆነ ተደረጎ የሚናፈሱ መረጃዎችን አጣጥለዋል ሚኒስትሩ።

የኢትዮጵያ የውሃ መስኖና ኃይል ሚኒስትር ዶ/ር ኢኒጂነር ስለሽ በቀለ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ አስገብተዋል በሚል የተናፈሱ አንዳንዱ መረጃዎችንም አስተባብለዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በኅዳሴ ግድብ ዙሪያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:05 0:00


ቭላድሚር ፑቲን እና ረጂፕ ታይፕ ኤርዶዋን

ተቀናቃኝ መንግሥታት በሚዋጉባት በሊቢያ ከፊታችን ዕሁድ ጀምሮ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የሩስያ እና የቱርክ መንግሥታት ጥሪ እያቀረቡ ናቸው።

ቭላድሚር ፑቲን እና ረጂፕ ታይፕ ኤርዶዋን ትናንት ኢስታንቡል ላይ ባወጡት የጋራ መግለጫ ሊቢያ ውስጥ ያለውን ግጭት በወታደራዊ መንገድ ለመፍታት መሞከሩ የህዝቡን ስቃይ እና ክፍፍሉንም ከማባባስ በቀር ውጤት አይኖረውም ብለዋል።

ህገወጥ ፍልሰት የጦር መሳሪያ በህገ ወጥ መንገድ ማስተላለፍ እና ሽብርተኝነት የሊቢያው ጦርነት ካስከተላቸው መዘዞች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል መሪዎቹ።

ቱርክ ትሪፖሊ ላይ ተቀማጩን በምዕራባውያን የሚደገፈውን መንግሥት ለመርዳት ወታደሮች መላክ ጀምራለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋዬዝ ሳራጅ ትናንት ረቡዕ ከአውሮፓ ህብረት ባለሥልጣናት ጋር ብረሰልስ ውስጥ ተገናኝተው ተወይይተዋል። የእርሳቸው ተቀናቃኝ ጀነራል ኻሊፋ ሃፍታር በበኩላቸው ከደጋፊያቸው የኢጣሊያ ጠ/ሚ ጁሴፔ ኮንቲ ጋር ተወይይተዋል።

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄይኮ ማስ ሁሉም ወገኖች ሊቢያን ሁለተኛ ሶሪያ ከመሆን እንዲታደጉ አሳስበው፣ የጦር መሳሪያ ማዕቀብም ይጣል፤ ፖለቲካዊ መፍትሄም ይፈለግ ሲሉ ተማጽነዋል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG