በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ዓርብ 6 መስከረም 2019

Calendar
መስከረም 2019
ሰኞ ማክሰ ረቡዕ ሐሙስ ዓርብ ቅዳሜ እሑድ
26 27 28 29 30 31 1
2 3 4 5 6 7 8
9 10 11 12 13 14 15
16 17 18 19 20 21 22
23 24 25 26 27 28 29
30 1 2 3 4 5 6
የጠብታ አምቡላንስ መሥራች አቶ ክብረት አበበ

"ችግሮችን ስናስብ ወደ መቆም ነው የምንሄደው። .. መቆም መልስ አይደለም። ሁልግዜ ችግሮች አሉ። ችግሮችን ለመፍታት መሞከር ነው። አንዴ ተፈጥረናል በዚህ ምድር ላይ ባየነው ነገር ላይ በሁለት እግር ቆመን .. እንፈታዋለን ብለን መሞከር" አቶ ክብረት አበበ የኢትዮጵያ ማሕበራዊ ሥራ ፈጣሪዎች ማሕበር የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት።

የማሕበራዊ ሥራ ፈጣሪነት እሳቤና ሥራዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ማሕበራዊ ሥራ ፈጣሪዎች ማሕበር ፕሬዝዳንትና የጠብታ አምቡላንስ መሥራች አቶ ክብረት አበበ ጋር የተጀመረ ወግ ነው።

የማሕበራዊ ሥራ ፈጣሪነትን መሠረታዊ እሳቤዎች፣ ተጨባጭ ማሕበራዊ ፋይዳና እንዲሁም በዚሁ መንፈስ በፈጠሩት “ጠብታ - አምቡላንስ” በተሰኘው ድርጅታቸው በሚያከናውኗቸው ሥራዎች ዙሪያ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ተዋይተዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ማሕበራዊ ሥራ ፈጣሪነት በኢትዮጵያ .. “ፈተናን” እንደ “ዕድል”
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:23 0:00
ማሕበራዊ ሥራ ፈጣሪነት በኢትዮጵያ .. "ፈተናን" እንደ "ዕድል"
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:04 0:00
ማሕበራዊ ሥራ ፈጣሪነት በኢትዮጵያ .. "ፈተናን" እንደ "ዕድል"
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:03 0:00


የፌዴራሉ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን

የፌዴራሉ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን በድሬዳዋ ከተማ በሚገኙ የህክምና ተቋማት ተዘዋውረው የቺኩንጉንያ ታማሚዎችን አይተዋል።

ዶክተር አሚር አማን ከድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ጋርም ውይይት ያካሄዱ ሲሆን 80 የሚሆኑ ባለሙያዎች ከፌዴራሉ መሥሪያ ቤት ወደ ድሬዳዋ እንደሚላኩም አስታውቀዋል።

በጤና ተቋማቱ የህክምና ድጋፍ ያገኙ ታማሚዎች ቁጥር 29 ሺ 500 መድረሱ የተነገረ ሲሆን ለሕመሙ የተጋለጠው ሰው ቁጥር ግን በአጠቃላይ በእጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ድሬ ዳዋ ውስጥ በተካሄደው ውይይት ላይ ተነግሯል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ቺኩንጉንያ እያነጋገረ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:14 0:00


ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG