በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የዓረና ትግራይና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲዎች መግለጫ

በትግራይ ክልል ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ በሚያደርጉት ጥረት በመንግሥታዊ አካላት ችግር እያጋጠመን ነው አሉ። የዓረና ትግራይና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲዎች።

የዓረና ሊቀ መንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ደግሞ ከትናንት በስትያ ታስረው እንደነበር በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የትግራይ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ በበኩሉ የክልሉ የፀጥታ አካላት ለሁሉም በፍትሐዊነት የሚያገለግል ነው ብልዋል።

"ከትናንት በስትያ የዓረና አመራሮቹ እንቅስቃሴ ያጠራጠራቸው ሰዎች ለፀጥታአካላት ጥቆማ ሰጥተው: ፖሊስም ይዞ ወደ ማረፍያ ቦታ ወስዶ የሚያስፈልግ ጥያቄ ጠይቆ ሸኝቷቸዋል" በማለት ገልፅዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዓረና ትግራይና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲዎች መግለጫ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:36 0:00

ወጣት ኢዘዲን ካሚል

በተራመዱ ቁጥር የሞባይል ስልክዎን ባትሪ የሚሞላ ኃይል ከፀሐይ ብርሃን የሚያመነጭ ጫማ፣ የዘይት ጄሪካን ላይ ስልክ ተገጥሞለት የእሳት አደጋ ቢከሰት የማንቂያ ጥሪ የሚያደርግ መሣሪያ፣ ምድጃ ለኩሰው ማጥፋት ረስተው ከቤትዎ ርቀው ቢሄዱስ! ባስታወሱ ጊዜ ከስልክዎ የሚያጠፉት ማብሰያና ሌሎች 27 የፈጠራ ሥራዎች! የወጣት ኢዘዲን ካሚል የአዕምሮ ውጤቶች ናቸው።

በተለይ ኢዘዲን ዕውቅና በከፍተኛ ደረጃ ተሰጥቶት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በራሣቸው መሸለሙ ለሃገሩ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ብዙ ጠቃሚ የአዕምሮውን ፈጠራ ውጤቶች ሊያበረክት እንዲችል እንዳነቃቃው ይናገራል።

ለዛሬው የጋቢና ዘጋቢዎቻችን መስኮት ኢዘዲን ከፀሐይ ዳምጠው ጋር ቆይታ አድርጓል።

ባለባትሪ ጫማ የፈለሰፈ ወጣት ኢትዮጵያዊ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:37 0:00


ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG