በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ከ1ሰላሣ ሚሊዮን ብር በላይ ለግንባታ፣ ለመሣሪያዎችና ለግብአቶች ወጭ አድርገው በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አጥረት ምክንያት ወደ ሥራ መግባት አለመቻላቸውን በደሴ ከተማ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሠማራት እንቅስቃሴ የጀመሩ ግለሰቦች ገልፀዋል።

ባለሃብቶቹ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በብድር ከባንክ ወስደው ሥራ ባለመጀመራቸው ለተጨማሪ ኪሣራ መዳረጋቸውንም ይናገራሉ።

የአማራ ክልል መንግሥት እንደ ኢንቨስትመንት ዘርፎቹ ዓይነት እየታየ የኃይል አቅርቦት ጥያቄውን በቅደም ተከተል ለመመለስ እንደሚጥር አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሥሪያ ቤት ግን ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እንዳለበት እየተናገረ ነው።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በደሴ ከተማ በኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:06 0:00

በከባድ የሥነ-ምግባር ግድፈት ከአመራር አባልነትና ከድርጅቱ የተሰናበቱ ግለሰቦች የሲዳማን ህዝብ ጥያቄ ለማደናቀፍ እየተንቀሳቀሱ ነው ሲል በአቶ ዱካሌ ላሚሶ የሚመራው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከስሷል።

በሌላ በኩል "ህጋዊ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ፤ ሲአን በኛ የሚመራ ነው" የሚለው የነ ዶ/ር ሚሊዮን ቱማቶ ቡድን "የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፈቃድ ያለን እኛ ነን" ቢልም ባለው ሁኔታ ለማንም እውቅና እንደማይስጥ ነገር ግን በ2010 ዓ.ም. በተካሄደ በነ ዱካሌ ላሚሶ ምርጫ ላይ አቤቱታ ቀርቦ እየታየ መሆኑን ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ አሁን ገልጿል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የሲአን የባለቤትነት ጥያቄ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:12 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG