በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

መንግሥቱ የተዋቀረው ለረጅም ጊዜ የዘገየው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተካሂዶ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ቲሼኬዲ ካሸነፉ በኋላ መሆኑ ነው።

የኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቨስተር ኢሉንጋ ኢሉካምባ ዛሬ በሰጡት መግለጫ “ መንግሥቱ ተቋቁሟል። ፕሬዚደንቱ የማቋቋሚያውን አዋጅ ፈርመዋል፡ ባፋጣኝ ሥራ ይጀምራል” ብለዋል።

በሥልጣን ክፍፍል ስምምነቱ መሰረት ሃያ ሦስቱ አባላት ከፕሬዚዳንቱ የለውጥ ጎዳና ፓርቲ የተቀሩት አርባ ሁለቱ ደግሞ ለቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ የኮንጎ የጋራ ግንባር ፓርቲ አባላት ይወስዳሉ።

ባለፈው ታህሳስ ወር የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በበርካታ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች የአደረጃጀት መጓደል የታየበት እንደነበር ይታወሳል። የመራጭ መዝገቦች መጥፋት፣ የኤሌክትሮኒክ ድምፅ መስጫዎች ብልሽት፣ የምርጫውን ሂደት በማጓተቱ የምርጫ አስፈፃሚ ባለሥልጣናቱ በጨለማው በባትሪ ለማከናወን ተገደዋል።

በምርጫው ሂደት ሁከትም መፈጠሩ ሲታወስ በምስራቅ ኪቩ አራት ስዎች ተገድለዋል።

ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ እና ዶ/ር ዋልተንጉስ ዳርጌ

"አንድ ሰው ስለ ራሱ፣ ስለ ሌሎችና ስለ ዓለም ያለው አስተሳሰብ ሁሉን ነገር ከመጠን በላይ በችኮነት የሚያይ ከሆነ፣ ሰዎች ተነስተውብኛል ሊያጠፉኝ ነው ካለ ከፍተኛ የንዴትና የስጋት ስሜት ሊፈጥርበት ይችላል።" ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ። ".. ድንገት እንዲህ ባለ ቁጣ የሚዋጥን ሰው የሚተነኩ ነገሮች የትየለሌ ናቸው። ምክኒያታዊነት የለውም። ያን ስሜት እንደ ሱስ ማረቅ ነው የሚሻለው።.." ዶ/ር ዋልተንጉስ ዳርጌ።

በሰው ልጅ የተፈጥሮ ሥሜት ጠባይ፣ ኃይል የተቀላቀለና ጠብ አጫሪ ዝንባሌ ይልቁንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ የሚታዩ ግጭቶችን ተዛምደው የተነሱ ጥያቄዎች ናቸው ሃኪምዎን ይጠይቁ ለምሽቱ ትኩረት የሚያደርግባቸው ጭብጦች።

በዚህ ተከታታይ ዝግጅት በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የሜዮ ክሊኒክ የነርቭና የአዕምሮ ህክምና ልዩ ባለሞያ ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ እና በጀርመኑ የድሬስደን ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ት/ርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰርና የበርካታ መጻሕፍት ደራሲው ዶ/ር ዋልተንጉስ ዳርጌ ጋር ናቸው።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኃይል ጥቃት እና የጠብ አጫሪነት ዝንባሌም እንደ ጤና ሁከት
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:01 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG