በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ

“ተቀምጠው የሰቀሉትን ቆሞ ማውረድ የሚቸግርበት ጊዜ እንዳይመጣ ሁሉም ሊጠነቀቅ ይገባል” ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በሰሞኑ የሃገሪቱ ሁኔታ ላይ ዛሬ ለፓርለማው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት አሳሰቡ።

በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የሚመጡ ኃይሎችን ብረት ይዘን እንዋጋቸዋለን” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

“ተቀምጠው የሰቀሉትን ቆሞ ማውረድ የሚቸግርበት ጊዜ እንዳይመጣ ሁሉም ሊጠነቀቅ ይገባል” ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:13 0:00

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ዦንግ ኡን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ዦንግ ኡን ጋር ያደረጉት ስብሰባ “እጅግ ውጤታማ ነበር” ካሉ በኋላ ሁለቱም ሀገሮች እንዲገፋበት ይፈልጋሉ ብለዋል።

“እነዚህ ሁሉ ሲስተካከሉ ሰሜን ኮርያን የሚጠብቀውን ብልጽግና አርቅቂያለሁ” ሲሉ ትራምፕ ደቡብ ኮርያ በሚገኘው ኦሳን የአየር ሰፈር ላሉት ወታደራዊ ሰራተኞች ተናግረዋል።

ሰሜን ኮርያ ኑክሌር ፕሮግራምዋን በሚመለከት ስምምነት ላይ ለመድረስ ከቻለች የኢኮኖሚ ጥቅም ልታገኝበት እንደምትችል ትረምፕ በተደጋግሚ ሲያስገነዝቡ ቆይተዋል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ይህን ያሉት በሰሜን ኮርያ ከወታደራዊ ሃይል ነጻ በሆነው ቀጠና ላይ ድንበርን ሻገር ብለው የሰሜን ኮርያን ምድር ለመርገጥ የመጀመሪያው ሥልጣን ላይ ያለ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኋላ ነው።

“መስመሩን አለፍ ብሎ መሻገሩ ትልቅ ክብር ነው” ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሰሜን ኮርያውን መሪ ለሌላ ሰብሰባ ዩናይትድ ስቴትስን እንዲጎበኙ ጋብዘዋቸዋል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG