በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ኤርትራዊ-አሜሪካዊው የራፕ የሙዚቀኛና ዘፋኝ ኤርሚያስ አስገዶም /ኒፕሲ ሀስል/

ኤርትራዊ-አሜሪካዊው የራፕ የሙዚቀኛና ዘፋኝ ኤርሚያስ አስገዶም ለጊዜው ማንነናታቸው ባልታወቀ ሰዎች በተተኮሰበት ጥይት ተገድሏል።

"ኒፕሲ ሀስል" ተብሎ በመድረክ ስሙ በተለይ የሚታወቀው ኤርሚያስ ሎስ አንጀለስ ከተማ ውስጥ ሃይድ ፓርክ መንደር ከሚገኘው የልብስ መደብሩ ደጃፍ ላይ የተገደለው ትናንት ዕሁድ ነው።

ለተጨማሪ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኤርትራዊ-አሜሪካዊው የራፕ የሙዚቀኛና ዘፋኝ ኤርሚያስ አስገዶም ተገደለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:35 0:00

የጠ/ሚ ዐብይ አንደኛ ዓመት

ፎቶ ፋይል:- ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ

ዐብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በፓርላማ ቃለ-መሃላ የፈፀሙት በነገው ዕለት መጋቢት 24/2010 ዓ.ም. ነበር።

ከጊዜው አጭርነት አንፃር ሲታይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል ከገቧቸው ነገሮች አብዛኞቹን አሳክተዋል የሚሉ ተንታኞችና ምሁራን “ያለፈው አንድ ዓመት በኢትዮጵያ ተስፋና እፎይታ የታየበት ነው” ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።።

አንደኛ ዓመቱን አስመልክቶ እየተካሄዱ ያሉ ዝግጅቶች የተገኙ ውጤቶችንና ሥራዎችን መለስ ብሎ ለመመልከት እንደሚያስችሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ላሜሪካ ድምጽ ገልጿል።

ያሜሪካ ድምፅ ይህን አንድ ዓመት ከሚቃኝባቸው ዘገባዎች አንዱ ቀጥሎ ይቀርባል።

ለተጨማሪ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የጠ/ሚ ዐብይ አንደኛ ዓመት
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:07 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG