በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

23ኛው የአድዋ ድል በዓል - በአዲስ አበባ

የአድዋን ታሪክ ለዘላለም የሚዘክር .. የታሪኩንም ያህል "ታላቅ" ይሆናል የተባለ ሃውልት አዲስ አበባ በመጭው ዓመት እንደምታቆም የከተማይቱ ከንቲባ አበሰሩ።

የጥንታዊት ኢትዮጵያ የአርበኞች ማሕበር ተወካይ በበኩላቸው አዲሱ ትውልድ አንድነቱ የተጠበቀ አገር እርሱን ለሚከተለው መጭው ትውልድ ያስተላልፍ ዘንድ ያሉበትን የአደራ ጥሪ ያሰሙበትን ንግግር ጠቅሶ የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ሪፖርት ልኳል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

23ኛው የአድዋ ድል በዓል - በአዲስ አበባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:12 0:00

አድዋ ከተማ

23ኛው የአድዋ ድል በዓል በአድዋ ከተማ በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

"በኢትዮጵያ ችግሮች ሲፈጠሩ ልዮነትን እንደ ፀጋ በመቀበልና ከአድዋ ድል የአንድነት መንፈስ በመውረስ እንወጣዋለን" ሲሉ በክብረ-በዓሉ የተገኙት የኢትዮጵያ ፌድራል ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴለሥነ ሥርዓቱ ታዳሚዎች ባሰሙት ንግግር ገልጠዋል።

የትግራይ ክልል መንግስት በበኩሉ በአድዋ ከተማ ለሚገነባው የአድዋ ፓን አፍሪካ ዮኒቨርሲቲ ግንባታ ወጭ የሚውል የ250 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማበርከት መወሰኑን ይፋ ያደረገበትን ጨምሮ የመቀሌው ዘጋቢያችን ዘግቧል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

23ኛው የአድዋ ድል በዓል በአድዋ ከተማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:14 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG