በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

በአይሮፕላን አደጋው ሕይወቱን ያጣው የ27 ዓመቱ ሲድራክ ጌታቸው ፎቶ ግራፍ በዘመዶቹ ተይዞ

“ይህንን ዓለም እንኑርበት አንኑርበት ዋስትና የለንም። ስለዚህ ዛሬ ያለችንን ቀን ተሳስበንና ተፋቅረን እንድንኖር እግዚያብሔር ትልቅ መልዕክት ያለው ይመስለኛል” ይህንን ያሉት በአይሮፕላን አደጋው ሕይወቱን ያጣው የ27 ዓመቱ ሲድራክ ጌታቸው እናት ወ/ሮ ሚልካ ይማም ናቸው።

የአምስት ልጆች እናቷ ወ/ሮ ሚልካ ይማም የናይሮቢ ከተማ ነዋሪ ናቸው። በዚህ አደጋ ሕይወቱን ያጣው የ27 ዓመቱ ሲድራክ ጌታቸው ሁለተኛ ልጃቸው ነበር። ልጃቸው ቅዳሜ ዕለት ወደ እርሳቸው እንዲመጣ በቆረጡለት ትኬት በማርፈዱ ምክኒያት ሳይሳፈር ቀርቶ ትኬቱ ለእሁድ እንደተላለፈና በማግሥቱ አደጋው በደረሰበት አይሮፕላን ላይ እንደተሳፈረ ገልፀዋል።

ወ/ሮ ሚሊካ “እግዚያብሔር እኔንም የኢትዮጵያ ሕዝብንም በዚህ ውስጥ አንድ ነገር ሊያስተምረን ነው ብዬ አስባለሁ” ሲሉ ደጋግመው ይናገራሉ። “ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ይሄ የኔ ነው’ ፣ ‘ያ የኔ ነው’ የምንለውን ነገር በማናስበው ደቂቃ ውስጥ ጥለነው እንሄዳለን። ይሄ ለኛ ትልቅ ማንቂያ ሊሆን ይገባል” ብለዋል።

“እንኳን ብሔር ብሔረሰቦች ቀርቶ ሁላችሁም የዓለም ሕዝቦች ይህችው ናችሁ። ከአፈር አታልፉም በሚል እግዚያብሔር ሊያስተምረ ነው የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ” ይላሉ።

ፍተሻውን ጨርሶ ወደ አይሮፕላን እየገባ መሆኑን የነገራቸውን የልጃቸውን ሁኔታ ያስታወሱት ወ/ሮ ሚልካ “ልጄ እኔን አዋርቶ ከስድስት ደቂቃ በኋላ እዚች ምድር ላይ የለም። እኛም ከዚህ የተለየን ሰዎች አይደለንም።” ብለዋል። ሐዘናቸውን ዋጥ አድርገውም የልጃቸው ሞት በሕይወት ያሉትን አስተሳስቦ በፍቅር የማስተሳሰሪያ ትምሕርት ነው ብለዋል።

(ዝርዝሩን ያዳምጡት)

በኬንያ አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ባቀረቡበት ወቅት

በኬንያ አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሲያቀርቡ በእጃቸው ስለያዟት “ጭራ” ጉዳይ ተጨዋውተዋል። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ፤ “የቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉስ አፄ ኃይለስላሴ ለአባቴ የሰጧቸው ጭራ እስከመጨረሻ የሕይወት ፍፃሜያቸው ድረስ አብሯቸው ነበር” ሲሉም ነግረዋቸዋል።

አቶ መለስ ይህን የሹመት ደብዳቤ ይዘው ወደ ኬንያ የተጓዙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውና ቢሾፍቱ አቅራቢያ የወደቀው በበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አይሮፕላን ከተነሳ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነበር። በዚህ አውሮፕላን ሳይበሩ የቀሩት ደግሞ እናታቸውን ተሰናብተው ለመውጣት ጉዟቸውን በሰዓታት በማራዘማቸው እንደሆነ ነግረውናል።

(ከአቶ መለስ ዓለም ጋር ያደረግነውን ቃለምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

“የጭራ ዲፕሎማሲ”
please wait

No media source currently available

0:00 0:18:59 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG