በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በዐቃቤ ሕግና በአቶ ኢሣያስ ዳኛው መካከል ባለው ክርክር፣ የዕግድ ትዕዛዙን አነሳ፡፡

የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በዐቃቤ ሕግና በአቶ ኢሣያስ ዳኛው መካከል ባለው ክርክር፣ የዕግድ ትዕዛዙን አነሳ፡፡ ጉዳዩን ሲመለከት ለቆየው የበታች ፍ/ቤት ውሳኔ እንዲሰጥበትም ልኳል፡፡

ከፍተኛው ፍ/ቤት ጉዳዩን ለማየት ቀጠሮ ቆርጧል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በዐቃቤ ሕግና በአቶ ኢሣያስ ዳኛው መካከል ያለው ክርክር
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:00 0:00

የዩናይትድ ስቴትሱ የሰሜን ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ ስቴፈን ቢገን

በፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕና በሰሜው ኮርያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን መካከል የሚካሄደውን የሁለተኛ ዙር ውይይት ዝግጅት ለማጠናቀቅ፣ የዩናይትድ ስቴትሱ የሰሜን ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ በዚህ ሳምንት ወደ ፕዮንግያንግ እንደሚጓዙ ተገለፀ።

የዩናይትድ ስቴትሱ የሰሜን ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ በዚህ ሳምንት ወደ ፕዮንግያንግ እንደሚጓዙ ሲገልፅ፣ ልዩ መልዕክተኛው ስቴፈን ቢገን ከሰሜን ኮሪያ አቻቸው ኪም ሀይክ ቾል ጋር ነገ ረቡዕ ይገናኙሉ፣ ባለፈው ሰኔ ወር ሁለቱ መሪዎች ሲንጋፖር ውስጥ ባካሄዱት አንደኛ ዙር ውይይት የተገኘውን ውጤት እንደሚገመግሙና በቀጣይነቱም ላይ እንደሚነጋገሩ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ባለፈው ዕሑድ ሶል ደቡብ ኮሪያ ከገቡት ዩናይትድ ስቴትሱ ልዩ ልዑክ ከዚያው ከሶል ነው ወደ ፕዮንግያንግ ይጓዛሉ።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG