በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በአካሄደው ስብሰባ በጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የቀረቡትን የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን፣ እንደዚሁም የዕርቅ ሰላም ኮሚሽን አባላት ሹመት አፅድቋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በአካሄደው ስብሰባ በጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የቀረቡትን የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን፣ እንደዚሁም የዕርቅ ሰላም ኮሚሽን አባላት ሹመት አፅድቋል፡፡

የሁለቱ ኮሚሽኖች መቋቋምና የአባላቱ መሾም ከአስተዳደር ወሰንና ከማንነት እንደዚሁም ከሰላም ጋር ተያይዞ የሚነሱና ሲጓተቱ የቆዩ ጉዳዮችን ለመፍታት እንደሚያግዝ በአብዛኞቹ የፓርላማ አባላት ታምኖበታል፡፡ የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ኮሚሽን መቋቋሙን ሲቃወም የቆየው ህወሓት ተወካዮች ግን፣ የአባላቱንም ሹመት ተቃውመዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያየ ሹመቶችን አፀደቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:08 0:00

በድሬዳዋ የሐይማኖት በዓል አከባበር ላይ የተፈፀመ ጥቃትን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ ላይ ተሳትፋችኋል በመባል የተያዙ 27 ተጠርጣሪዎች ላይ የአስተዳደሩ የመጀመሪያ ፍርድቤት ፈቅዶት የነበረውን ዋስትና የይግባኝ ሰሚ ፍርድቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡

በድሬዳዋ የሐይማኖት በዓል አከባበር ላይ የተፈፀመ ጥቃትን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ ላይ ተሳትፋችኋል በመባል የተያዙ 27 ተጠርጣሪዎች ላይ የአስተዳደሩ የመጀመሪያ ፍርድቤት ፈቅዶት የነበረውን ዋስትና የይግባኝ ሰሚ ፍርድቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡

አስተዳደሩ በተቃውሞ እንቅስቃሴው ላይ ረብሻ እንዲነሳ አስተባብረዋል፣ መንገድ ዘግተዋል፣ ልዩ ልዩ ጥፋቶችን ፈፅመዋል ብሎ በቁጥጥር ፕሥር ያዋላቸውን 308 ተጠርጣሪዎች በሦስት መዝገብ ከፍሎ ጉዳያቸውን እያየ ነው፤ በተጠርጣሪነት ለተያዙት በአስተዳደሩ የሚገኙ 14 የግል ጠበቆች በበጎ ፈቃደኝነት ነፃ የጥብቅና አገልግሎት እየሰጧቸው ነው፡፡

ጠበቆቹ የህግ ጥሰት እየተፈፀመ ነው ይላሉ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በድሬዳዋ የተፈፀመ ጥቃትን ተከትሎ የተነሳ ተቃውሞ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:01 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG