በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የኢትዮጵያ ኤምባሲ - ዋሺንግተን ዲሲ

ከአንድ ወር ተኩል በላይ ይፈጅ የነበረው አገልግሎት ወደ ሁለት ቀናት ወርዷል፤ ክፍያውም ዝቅ ብሏል፤ የወካይና ተወካይን ዋሺንግተን ላይ በአካል መገኘትና መገናኘት አይጠይቅም።

ቪዲቸር ከሚባል የግል ኩባንያ ጋር ተባብሮ እየሠራ ያለው በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዲስና ፈጣን የውክልና አሰጣጥ አገልግሎት ካለፈው ሣምንት አንስቶ ሥራ ላይ አውሏል።

ይህ በኢንተርኔት ላይ የተመሠረተ የውክልና አሰጣጥ ቀድሞ ከአንድ ወር ተኩል በላይ ይፈጅ የነበረውን አገልግሎት ወደ ሁለት ቀናት ያወረደና ክፍያውንም ዝቅ ያደረገ፤ የወካይና ተወካይን በአካል መገኘትና መገናኘት የማይጠይቅ መሆኑን የቴክኖሎጂው ፈጣሪ አቶ ኬብሮን ደጀኔ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ውክልና ሰጭዎች ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ዌብሳይት www.ethiopianembassy.org ገብተው ማመልከቻውን መሙላት እንደሚችሉ፣ የራሳቸውን የውክልና መስጫ መልዕክት በተቀመጠው መሠረት ከእጅ ስልካቸው በቪድዮና በድምፅ መቅረፅ፣ የሚጠየቁ ሠነዶችንም ፎቶ አንስተው ማስገባት እንደሚኖርባቸው አቶ ኬብሮን አብራርተዋል።

ለሙሉው ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የውክልና አሰጣጥ ተፋጥኗል - ከአቶ ኬብሮን ደጀኔ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:27:17 0:00

Hawassa

የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጥ መቆየቱንና የህዝበ ወሳኔ ቀን አለመገለፁን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ፡፡ ሰልፉ በሲዳማ "ቀጣላ" ባህላዊ ስርዓት የተደረገ ሲሆን በሰላማዊ መንገድ ተጠናቅቋል፡፡

የሲዳማ በክልል የመደራጀትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በፖለቲካ ጣልቃ ገብነትሳይሆን በህግ መንግሥት ብቻ እንድፈታ በሰልፉ ተጠይቋል፡፡

በሰልፉ ከሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን ከሚገኙ ሁለም ወረዳዎች የመጡ በርካታ ህዝብ የተሳትፈ ሲሆን በአገሪቱ ታይቷል ያሉትን ለውጥ እንደሚደግፉም ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:52 0:00
የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:17 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG