በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የአፍሪካ ቀንድ ምጣኔ ኃብት

ፎቶ ፋይል

ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት ለማሻሻል ያለመው የአንድ ዓመት ፕሮጀክት እያለቀ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ተጨማሪ ዕርዳታ የሃገሪቱን ምጣኔ ሃብት ያሳድጋል፤ ከእአአ 2018 ጀምሮ ፈጣን ለውጥ እየታየ ባለበት በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ሥፍራ ያጠናክራል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ከፕሮጀክቱ ጀርባ ያለውና ተቀማጭነቱን ለንደን ያደረገው ድርጅት ባሳለፍነው ማክሰኞ መግለጫው ለሶማሊላንድ የኢኮኖሚ መሪዎች የተዘጋጀው የልምድ ልውውጥና ምክክር ፕሮግራም በቅርቡ ይፈፀማል ብሏል።

ይህ ለንግድና ለመዋዕለ ንዋይ ምደባ አስፈላጊነት የሚሠራ ድርጅት ዓላማ በዓለም ድሃ የሆኑ ሃገሮች ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው የሚችል የንግድ ግንኙነቶችን እንዲያሳድጉ መርዳት ነው።

ድርጅቱ ከእአአ 2018 ጀምሮም ከኢትዮጵያ ጋር የምጣኔ ሃብት ሥምምነቶችን ማበረታታት በሚቻልበት መንገድ ከሶማሊላንድ መሪዎች ጋር ሠርቷል። ምክክሩ በሁለቱ ወገኖች በኩል የንግድና ትራንስፖርት ሥምምነቶች ረቂቅ ሕግ እንዲዘጋጅ ማስቻሉ ተዘግቧል።

የጭላሎ ተራራ ደን በእሳት እንዲቃጠል ያደረገው ግለሰብ በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተፈረደበት መሆኑን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።

የጭላሎን ፓርክ ደን ለጊዜው ካልተያዙ ሁለት ግለሰቦች ጋር ጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም 11 ሰዓት ላይ በእሳት እንዲያያዝ ማድረጋቸውን አቃቤ ህግ በክሱ ጠቅሷል።

ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ለጊዜው ሲሰወሩ ተከሳሹ በአካባቢው ነዋሪዎች እጅ ከፍንጅ መያዙ ተገልጿል። ተከሳሹና ግብረ አበሮቹ በለኮሱት እሳት ከ800 ሄክታር በላይ ደን መውደሙን በመግለፅ አቃቤ ህግ በጢዮ ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ መመስረቱም ተገልጿል።

ለሦስት ቀናት የዘለቀውን የእሳት ቃጠሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ለማጥፋት ተረባርበዋል። እሳቱን ለማጥፋት የሰው ኃይልን ጨምሮ ከ210 ሺ ብር በላይ ወጪ ሆኗል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG