በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የድርጅቶቹ አርማ

በመቀሌው ጉባኤ እንድንሳተፍ ብንጋበዝም ላለመሳተፍ በመወሰናችን "አልተሳተፍንም" ይላሉ።

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር - ኦብነግ፣ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር - ኦነግ እና የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግሬስ - ኦብኮን መሪዎች በቀጥታ ጠይቀን ያገኘነው ዝርዝሩን ይዟል።

የመቀሌው ጉባኤ ያልተሳተፉት ሶስት ድርጅቶች ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:44 0:00


የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታ ማዦር ሹም ጄነራል አደም መሐመድ ማህሙዴና የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ኃይሎች ምክትል ኤታ ማዦር ሹም ጄነራል ጆን ሃይተን ዛሬ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ ተገናኝተዋል፡፡

የኢታ ማዦር ሹም ፅህፈት ቤቱ ቃል አቀባይ ሻለቃ ትሪሻ ጉይቦ ዛሬ ባወጡት ፅሁፍ ነው የሁለቱን የጦሮች አዛዦች ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ ተገናኝቶ መወያየት ያሳወቁት፡፡

ለአካባቢያዊ መረጋጋት ኢትዮጵያ ስላላት አስተዋፅዖና ቁርጠኛነት፣ በመላ አፍሪካ ላለው የተባበሩት መንግሥታት ሰላም የማስከበር ተልዕኮዎች ስላላቸው ድጋፍም ጄነራል ሃይተን ለጄነራል አደም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡ አዛዦቹ ወታደራዊ ትብብሮቻቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው መንገዶች ላይም ተወያይተዋል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስና በኢትዮጵያ መካከል ያለው አጋርነት ለምሥራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋር እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን የቃል አቀባይዋ የሻለቃ ጊዮቦ የፅሁፍ መግለጫ አመልክቷል፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG