በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የአውስትራልያ መንግሥት እየተስፋፋ የሚሄድ አዲስ ሰደድ እሳት እንደሚነሳ በመግለጽ ዛሬ የአስቸኳይ ጊዜ ማስጠንቀቅያ አውጥቷል።

በተለይም ትኩረት የተደረገበት፣ የሀገሪቱ ደቡብ ምሥራቅ ጠረፍ ነው። ከባድ ሙቀትና ነፋስ በተናጠል የሚነሱትን እሳቶች አደባልቆ፣ የሰዎች ህይወትንና ቤቶችን አደጋ ላይ የሚጥል፣ ከባድ እሳት ሊያስነሳ እንደሚችል ባለስለሥልጣኖቹ ገልፀዋል።

በአውስትራሊያ ትልቋ ከተማ ሜልበርን አካባቢዎች፣ አዲስ እሳቶች እየትነሱ መሆናቸውን ባለሥልጣኖች ጠቁመዋል። ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ መክረዋል።

በአውስትራሊያው በጋ ወራት ወቅት፣ በሰደድ እሳት በተጎዳው ኒው ሳውዝ ዋለስ፣ ዛሬ አንድ መቶ እሳቶች እንደተነሱ ባለስልጣኖች ገልፀዋል።

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች በእሳት ቃጠሉ እንደሞቱና ከ 1,000 በላይ የሚሆኑ መኖርያ ቤቶች እንደወደሙ ተዘግቧል።

የእስራኤል ምርጫ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እና ጊዲዮን ሳአር

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የገዢ ፓርቲያቸው ሊኩድ አመራር ለመምረጥ ትናንት ሀሙስ በተካሄደው ቅድመ ምርጫ አሸንፈዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የገዢ ፓርቲያቸው ሊኩድ አመራር ለመምረጥ ትናንት ሀሙስ በተካሄደው ቅድመ ምርጫ አሸንፈዋል፤ "ከፍተኛ ድል" ሲሉም ገልፀውታል።

የሊኩድ አባላት ከሰጡ ድምፅ ሰባ ሁለት ከመቶውን ኔታንያሁ ያገኙ ሲሆን ተቀናቃኛቸው የቀድሞ የአገር ግዛትና የትምህርት ሚኒስትር ጊዲዮን ሳአር ሃያ ስምንት ከመቶውን አግኝተዋል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG