በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ረቡዕ 6 ህዳር 2019

Calendar
ህዳር 2019
ሰኞ ማክሰ ረቡዕ ሐሙስ ዓርብ ቅዳሜ እሑድ
28 29 30 31 1 2 3
4 5 6 7 8 9 10
11 12 13 14 15 16 17
18 19 20 21 22 23 24
25 26 27 28 29 30 1
ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ምዩሪየል ባውዘር

ዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ምዩሪየል ባውዘር ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ እንደሚገቡ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ከከንቲባዋ ጋር ከሃምሣ በላይ አሜሪካዊያን የንግድ ማህበረሰብ አባላት እንደሚጓዙ ተገልጿል።

ዋሺንግተን የመገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለልዑካን ቡድኑ ገለፃ ማድረጉን አስታውቋል።

እህትማማች ከተሞች የሆኑት አዲስ አበባና ዋሽንግተን ስምምነታቸውን በአዲስ መልክ ያድሳሉ ተብሏል።

ከንቲባዋ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ ዋሽንግተን ዲሲ በነበሩ ጊዜ ባደረጉላቸው ግብዣ መሠረት መሆኑን ኤምባሲው አክሎ ጠቁሟል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከኢትዮጵያ፣ ከግብፅና ከሱዳን ከፍተኛ ተጠሪዎች ጋር

ከኢትዮጵያ፣ ከግብፅና ከሱዳን ከፍተኛ ተጠሪዎች ጋር ዛሬ መገናኘታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባወጡት ትዊታቸው

“አሁን እየተገነባ ባለው ከዓለም እጅግ ግዙፍ ከሆኑት አንዱ በሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ለረዥም ጊዜ ለቆየ ውዝግባቸው መፍትኄ እንዲገኝ ለማገዝ ከግብፅ፣ ከኢትዮጵያና ከሱዳን ከፍተኛ ተጠሪዎች ጋር ያደረግነውን ስብሰባ አሁን ጨረስን፡፡ ስብሰባው የተካሄደው በመልካም ሁኔታ ነበር። ውይይቱ ቀኑንም ቀጥሎ ይውላል።” ብለዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከግብፅና ከሱዳን አቻዎቹ ጋር የሚያደርገው ውይይት በፕሬዚዳንት ትረምፕ ግብዣ በገንዘብ ሚኒስትሩ ስቲቭን ምኑቺን አስተባባሪነት የሚካሄድ ሲሆን የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስም እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡

የሦስቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የዋሽንግተን ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ የምትገኘው “ለምክክር እንጂ ለድርድር አይደለም” ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ ቀደም ሲል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

የስብሰባውን ሂደት በቅርብ እየተከታተልን መዘገባችንን እንቀጥላለን፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG