በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ

ከዓለም ግዙፍ የበይነ -መረብ ላይ የንግድ እና ቴክኖሎጂ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው «አሊባባ» መስራች እና የቀድሞ ሊቀመንበር ጃክ ማ ከሰሞኑ ወደ ኢትዮጵያ አቅንተዋል።

እሳቸው እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት አሊባባ ድርጅት እና የኢትዮጵያ መንግስት አዲስ አበባን የኤሌክትሮኒክ ዓለም ንግድ መርሃ-ግብር(eWTP) መናገሻ ለማድረግ የመግባቢያ ሰነድ ፈርመዋል።

ለመሆኑ «ከክፍለ ዘመኑ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሰዎች መካከል አንዱ» በሚል የሚታወቁት ጃክ ማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ፣በመነቃቃት ላይ ላለው የቴክኖሎጂ መስክ ምን ፋይዳ አለው?

ይሄንን እና ተያያዥ ጥያቄዎችን አንግበን ከአቶ ሰሎሞን ሙሉጌታ ካሳ ጋር አጭር ውይይት አድርገናል።

አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ፣ በኢቢኤስ ቴሌቭዥን የሚተላለፍ ቴክኖሎጂ ተኮር ትርኢት አዘጋጅ እና አቅራቢ፣ የግርምተ -ሳይቴክ መጽሃፍ ደራሲ እና የቴክ-አምባሳደር ከመሆናቸው ባሻገር ፣ በፎርቹን መጽሄት ምርጥ 500 አማካሪ ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ በተጠቀሰ ዓለም አቀፍ ተቋም ውስጥ የቴክ ስትራቴጂስት እና አማካሪ ሆነው ይሰራሉ።

ከሀብታሙ ስዩም ጋር ያደረጉትን አጭር ውይይት ያዳምጡ።

«የአሊባባ» መስራች ጉብኝት ለኢትዮጵያዊ የቴክኖሎጂ ምህዳር ምን ይፈይዳል ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:24 0:00


Oda Bultum University

በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ዋና ከተማ ጭሮ (አሰበ ተፈሪ) የሚገኘው የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ለ15 ቀናት ትምህርት መስጠት እንደሚያቆም አስታወቀ።

የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርስቲ ከዚህ ወሳኔ ላይ የደረስኩት በተማሪዎች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በተለያዩ መንገዶች ለመፍታት ሞክሬ ስላልተሳካ ነው ብሏል።

ይሁንና 15ቱን ቀናት ዩኒቨሪስቲው ውስጥ መቆዬት ለሚፈልጉ የምግብና መኝታ አገልግሎት እሰጣለሁ ብሏል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሊያቆም ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:41 0:00


ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG