በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ሀዋሳ ከተማ ወደ ስላሟ እየተመለሰች ነው ሲሉ የከተማዪቱ ከንቲባ አስታውቋል።

የሲዳማ ውሳኔ ህዝብም ያለ እንከን እንዲጠናቀቅ አስተዳደሩ በቂ ዝግጀት እንዳደረገም ተናግረዋል።

በውሳኔ ህዝቡ ላይ ድምፅ ለመስጠት ሁለት ሚሊዮን ሰው መመዝገቡን ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

በሌላ በኩል በደቡብ ክልል ፀጥታ በማደፍረስና በተለያዩ ወንጀሎች የተጠርጠሩ ባለሥልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ መስተዳደር አስታውቆአል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

"ሀዋሳ ከተማ ወደ ስላሟ እየተመለሰች ነው" የከተማዪቱ ከንቲባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:51 0:00


የትረምፕ የክስ ሂደት ተጀምሯል

የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕን ኢላማ ያደረገ ታሪካዊ የክስ ሂደት ዛሬ ዋሺንግተን ዲሲ ተጀምሯል።

ትረምፕ ሥልጣናቸውን ከፖለቲካ አንፃር የራሳቸውን ጥቅም ለመጥበቅ ተጠቅመውበት እንደሆነ ለማወቅ በሚደረገው ምርመራ ወሳኝ ቦታ ያላቸው የምክር ቤት አባላት ተጻራሪ አመለካከቶችን አንፀባርቀዋል።

ዲሞክርስቶች ፕረዚዳንት ትረምፕ ላይ ክስ ለመመስረት የሚያደርጉትን ጥረት የሚመሩት የተወካዮች ምክር ቤት የሥለላ ክፍል ኮሚቴ ሊቀመንበር አዳም ሼፍ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ፕረዚዳንት ትረምፕ ዋናው ዲሞክራት የምርጫ ተወዳዳርያቸው በሆኑት ጆ ባይደን ላይ ኡክራይን ምርመር እንድትጀምር ጫና አድርገዋል ብለዋል። ኡክራይን በምስራቅ ክፍል ያሉትን የሩስያ ደጋፊ ተገንጣዮች የሚባሉትን ኃይሎች ለመዋጋት የሚያስፈልጋት $391 ሚልዮን ዶላር እንዲሰጣት ከመፍቀዳቸው በፊት ምርመራውን እንድትጀምር ተጭነዋታል ብለዋል ሼፍ ባደረጉት ንግግር።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG