በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፎቶ ፋይል:- የትነበርሽ ንጉሴ

“ሁላችንንም ተሸክማን የምታድር አገራችንን እንዳናጣት አንዱ አንዱ ላይ ነግሶ ለመታየት ከሚደረግ ሩጫ ተቆጥበን፤ ሁላችንም ዝቅ ብለን አገራችንን ከፍ ማድረግ የምንችልበት፤ የጋራ ታሪክ የምንጽፍበት፤ የጋራ ሃዘን ታሪካችንን ምዕራፎች የምንዘጋባቸው መንገዶች መጀመር አለብን።” የትነበርሽ ንጉሴ - የእርቀ ሰላም ኮምሽን ምክትል ሰብሳቢ።ኮምሽን ምክትል ሰብሳቢ።

ግጭት - የኃይል ጥቃት እና የሰላም መንገዶች - ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:08 0:00

ክፍል ሁለት

የበርካታ ኢትዮጵያውያን ሕይወት በጠፋበት የሰሞኑ የተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች የተቀሰቀሰ ቀውስና ሁነኛ መላዎቹ ዙሪያ ከእርቀ ሰላም ኮምሽን ምክትል ሰብሳቢዋ የትነበርሽ ንጉሴ ጋር የተካሄደ ውይይት ነው።

የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያዳምጡ።

ግጭት - የኃይል ጥቃት እና የሰላም መንገዶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:44 0:00


የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን

ከጥቅምት 11 ክስተት ጋር ተያይዞ ግጭት በመቀስቀስ የተጠረጠሩ 407 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን መንግሥት አስታወቀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ከሰዓት በኋላ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ይህን የገለፁት።

በመግለጫቸው ላይ በወቅቱ በነበረው ግጭት የ 78 ዜጎች ህይወት ማለፉን ጠቁመዋል።

በወቅቱ በግጭቱ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ የፀጥታ መዋቅሩ በሙሉ አቅሙ መስራቱንም ገልጸዋል።

ቀውሱን ለማርገብ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ላደረጉት አስተዋፀዖ መንግሥት ምስጋና አቀርቧል።

ግጭቱ የተነሳው በአክቲቪስቱ ጁዋር ሞሐመድ ላይ በተደረገ አያያዝ ምክንያት በተነሳ ተቃውሞ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ቃል-አቀባይ ቢልለኔ ስዩም መግለፃቸውን ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ጠቅሷል።

በሀገሪቱ ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ በተፈጠሩ ተመሳሳይ ግጭቶች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት 33 ሺህ 221 ግለሰቦች መካከል ከ2 ሺህ በላይ ለህግ መቅረባቸውን አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናግርዋል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG