በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

Elias Sime at the Smithsonian African Art Award

በዩናይትድ ስቴትስ ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘው ስሚዝሶኒያን ብሄራዊ የአፍሪካ ጥበብ ቤተ-መዘክር ፥ ለአራተኛ ጊዜ አፍሪካዊ የስነ-ጥበብ ባለሙያዎችን የክብር ሽልማት አበርክቷል።የዘንድሮዎቹ ተሸለሚዎች ኢትዮጵያዊው የህብረ-ጥበባት ባለሙያ ኤልያስ ስሜ እና ናይጄሪያዎ የዕይታ ጥበብ ባለሙያ ኒጂዲካ አኩኒዬ ክሮስቢ ናቸው። በስፍራው ተገኝተን ያየነውን በቀጣዩ የምስል ዘገባ እናስቃኛችኋለን።

ኤልያስ ስሜ የስሚዝሶኒያን የአፍሪካ የሥነ-ጥበብ ሽልማት ተሸላሚ ሆነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:10 0:00

የትረምፕ አስተዳደር የኢትዮጵያን፣ የግብፅንና የሱዳንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለውይይት ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ጋብዟል።

ዶ/ር ስለሺ በቀለ /ሚኒስትር/
ዶ/ር ስለሺ በቀለ /ሚኒስትር/

የትረምፕ አስተዳደር የኢትዮጵያን፣ የግብፅንና የሱዳንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለውይይት ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ጋብዟል።

የጥሪው አጀንዳ የኅዳሴ ግድብ አሞላልና በዓባይ ውኃ አጠቃቀም ላይ በካይሮና በአዲስ አበባ መካከል አለ የሚባለው አለመግባባት መሆኑ ተገልጿል።

ታላቁ ኅዳሴ ግድብ /በከፊል/
ታላቁ ኅዳሴ ግድብ /በከፊል/

ስብሰባውን እንዲጠሩ ለፕሬዚዳንት ትረምፕ ጥሪ ያቀረቡት የግብፁ አብዱልፋታህ ኤል ሲሲ ናቸው።

ጉዳዩ በቴክኒክ ባለሙያዎች የተያዘ በመሆኑ ኢትዮጵያና ሱዳን የሦስተኛ ወገን አደራዳሪ በማስገባት ሃሳብ እንደማይስማሙ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የተናገሩት የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ፕሬዚዳንት ትረምፕ የጋበዙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን መሆኑንና የድርድርም አለመሆኑን ተናግረዋል።

ለሙሉው ቃለ ምልልስ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ዓባይ፣ ኅዳሴ
please wait

No media source currently available

0:00 0:30:28 0:00


ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG