በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፎቶ ፋይል

ሰሜን ኮርያ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በመጪው ቅዳሜ በኒኩሌር ጉዳይ ላይ ንግግር ለማድረግ እንደተስማማች አንድ የሰሜን ኮርያ ዲፕሎማት በመንግሥት ሚድያ መናገራቸው ተጠቅሷል።

የሰሜን ኮርያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺኦስ ሰን ሁይ ፕዮንግ ያንግና ዋሺንግተን በመጪው ቅዳሜ ተገናኝተው ለመነጋገር ተስማምተዋል ብለዋል። በዋዜማው “ቀዳሚ ግንኙነት” ይደረጋል ሲሉ አክለዋል። የስብሰባው ቦታ የት እንደሆነ ግልፅ አይደልም።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ዦንግ ኡን፣ ሁለቱን ኮርያዎች በሚለየው ከወታደራዊ ህልውና ነፃ በሆነው ቀጠና ተገናኝተው ከተነጋገሩ ሦስት ወራት በኋላ ነው በመጪው ቅዳሜም እንደሚገናኙ የተገልፀው።

ባህር ዳር

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮምሽን የኢንፎርሜሽን እና ሚዲያ ልማት ዋና መምሪያ ሃላፊ ረዳት ኮምሺነር ሰይድ አህመድ ባለፈው ዓርብ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተውቋል።

መስሪያ ቤታቸው በፌስቡክ ገፁ ላይ እስራታቸው ከሰኔ አስራ አምስቱ ጥቃት ጋር የተያያዘ መሆኑን ይጠቁማል። ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ግን ምክንያቱን ከመናገር ተቆጥበዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ረዳት ኮምሺነር ሰይድ አህመድ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:20 0:00


ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG